የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንገዶች ባለ ስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ምስጋናዉ ማቲዮስ፣ የቢሮው የየዘርፉ ኃላፊዎች፣ የጉብሬ ዲስትሪክት ስራ አስኪያጅ፣ የእኖር ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ መብራቱ ተክሌን ጨምሮ ሌሎች የወረዳዉ አመራሮች የአሞገራ አፍጥር የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት የሳይት ምልከታ አካሄደዋል።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንገዶች ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ምስጋናዉ ማቲዮስ በመስክ ምልከታዉ ወቅት እንዳሉት ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ሶስት ዋና ዋና ተግባራትን አንግቦ የሚሰራ ሲሆን እነዚህም የጥናትና ዲዛይን ፣ የመንገድ ግንባታ ፣የድልድይ ግንባታ እንሰራለን ብለዉ በዚህ በጀት አመት ከ1ሺህ በላይ ኪሎ ሜትር የመንገድ ግንባታ ለማከናወን አቅደዉ እየሰሩ እንደሆነም ተናግረዋል።
በክልሉ 1ሺህ 688 ኪሎ ሜትር መንገዶችና ድልድዮች ደረጃቸው በጠበቀ መልኩ እንደሚጠገኑ አስረድተዋል።
የተቋሙ ሬጉላቶሪ የስራ ክፍል የመንገዶች ግንባታ ጥራት የሚቆጣጠር ሲሆን የመንገድ ጥገና ስራዎች የዉጪ አማካሪዎች ጭምር በማካተት ጥራትና ቁጥጥር እያደረገ ነዉ ብለዋል።
በድልድይና በመንገድ ግንባታና ጥገና ዘርፍ የምንጠቀማቸዉ ማቴሪያሎች በላብራቶሪ ያለፉ እንደሆነም ጠቁመዉ የትኛዉም የመንገድ ፕሮጀክት በፍጥነት ተጀምረዉ እንዲያልቁና ለማህበረሰቡ አገልግሎት እንዲሰጡ በትኩረት እየተሰራ ነዉ ብለዋል።
ተጀምረዉ ረጅም ጊዜ ሳይሰሩ የሚቆዩ ፕሮጀክቶች ማህበረሰቡ ላይ ሌላ ችግር እየፈጠሩ እንደሆነም ያመላከቱት ዋና ስራ አስኪያጁ ያፈር ስራ ብቻ የሰሩበት አካባቢ በጎርፍ አደጋ እየተጎዳ ማህበረሰቡ ላይ ትልቅ እንግልት እየፈጠሩ እንደሆነም ተናግረዉ ፕሮጀክቶች ተጀምረዉ በጊዜ ማለቅ እንዲችሉ በዚህ አመት አቅደዉ ሰፊ ርብርብ እየተደረገ እንደሆነም አብራርተዋል።
በአዲስ የተገነቡና የተጠገኑ መንገዶች ዘላቂ አገልግሎት መስጠት እንዲችሉ ማህበረሰቡ ጥበቃ ሊያደርግላቸው ይገባል ብለዋል።
በበጀት አመቱ ለማጠናቀቅ ግብ ከተጣለላቸው የመንገድ ፕሮጀክቶች አንዱ የአሞገራ አስጥር 21 ነጥብ 5 ኪሎ ሜትር ሲሆን የመንገድ ግንባታ ስራው ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት እንዲችል ርብርብ እየተደረገ እንደሚገኝ ስራ አስኪያጁ አስረድተዋል።
የእኖር ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ መብራቱ ተክሌ እንዳሉት በወረዳዉ በመንገድ ልማት በመንግስትና በማህበረሰቡ ተሳትፎ በርካታ ስራዎች እየሰራን ነዉ ብለዋል።
በአምና ደረጃ በማህበረሰቡ ተሳትፎ ከ89 ኪሎ ሜትር በላይ የአፈር ስራና ከ59 ኪሎ ሜትር በላይ ጠጠር ማልበስ የተቻለ እንደሆነም አስታዉሰዉ በመንግስት በኩል የተጀመሩ የመንገድ ስራዎች መኖራቸዉም ተናግረዉ የፌዴራል መንገድ በፍጥነት እየተሰራም እንደሆነም አብራርተዋል።
በክልሉና በዩራፕ እየተሰሩ ያሉ ዪንገድ ፕሮጀክቶች የግንባታ ሂደታቸዉ በጥሩ ሁኔታ እንዳሉም አመላክተዉ የክልሉ መንገዶች ባለስልጣን በወረዳዉ የጀመራቸዉ ከሶስት በላይ የመንገድ ፕሮጀክቶች ያሉ ሲሆን ከነዚህም ዉስጥ 15 ቀበሌዎች የሚያገናኝ 65 ኪሎ ሜትር የመንገድ ግንባታ ያለ ሲሆን ይህም በዚህ አመት የሚጠናቀቅ እንደሆነም ተናገረዋል።
ከአሞገራ አስጥር ቀበሌ የሚገነባዉ የመንገድ ፕሮጀክት ግንባታ እየተካሄደ ሲሆን በዚህም የቆንጨ ድልድይ የተጠናቀቀና የጢቆ ድልድይ ግንባታ እየተጠናቀቀም እንደሆነም ተናግረዋል።
ከአሞገራ አስጥር መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ብሩክ ሽከታ እንዳሉት መንገዱ በ2010 ዓመተ ምህረት ግንባታ የተጀመረ ሲሆን ነገር ግን በአንዳንድ ሀገራዊና አለም አቀፋዊ በተከሰቱ በኮቪድ ፣ በኮንስትራክሽ ቁሳቁስ መወደድና በሌሎች ሁኔታዎች አማካኝነት ፕሮጀክቱ ተስተጓጉሎ እንደነበርና አምና ክልሉና ዲስትሪክቱ እንዲሁም ሁለቱም ወረዳዎች ባደረጉት ጥረት የግንባታ ስራ ማስቀጠል ተችሏል ብሏል።
ከአሞገራ አስጥር የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት የ21 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለዉ እንደሆነና የቆረጨ ድልድይ አልቆለት ለትራፊክ ክፍት የማድረግ ስራና ሌሎችም ድልድዬች በግንባታ ሂደት ላይ መሆናቸዉም አብራርተዋል።
የጉብሬ ዲስትሪክት ሀላፊ ተወካ አቶ ገብረማሪያም በቸኒ በበኩላቸዉ እንዳሉት ዲስትሪክቱ በመንገድ ልማት ግንባታና ጥገና ላይ በትኩረት እየሰራ ይገኛል።
ባለፈዉ አመት በርካታ መንገዶች የጥገና ስራ መሰራቱም አብራርተዉ የአሞገራ አስጥር የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት በክልሉ ድጋፍ እየሰራ እንደሆነም አመላክተዋል ሲል የዘገበዉ የጉራጌ ዞን መንግስት ኮሚኒኬሽን መምሪያ ነዉ።