በጉራጌ ዞን እኖር ወረዳ በደረሰው የእሳት አደጋ 7 መኖርያ ቤቶች መውደማቸውን የወረዳው ግብርና ልማት ጽ/ቤት ገለፀ።

ጳጉሜ 3/2014 ዓ.ም

በጉራጌ ዞን እኖር ወረዳ በደረሰው የእሳት አደጋ 7 መኖርያ ቤቶች መውደማቸውን የወረዳው ግብርና ልማት ጽ/ቤት ገለፀ።

የእሳት አደጋው የተከሰተው በወረዳው ሆርበት ዚዞ ቀበሌ ሲሆን ከቤት እና ንብረት ባለፈ በሰብል ላይ ከፍተኛ ውድመት ማድረሱን ተገልጿል።

በዛሬው ዕለት የጽ/ቤቱ የአደጋ ስጋት አመራር ሠራተኞች የደረሰውን ጉዳት በአካል ተገኝተው ተመልክቷል።

በእሳት አደጋው የደረሰው ጉዳት ከ2 ሚሊየን 930 ሺ 5 መቶ ብር በላይ የሚገመት መሆኑን የገለጹት በጽ/ቤቱ የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ባለሙያ ወ/ሮ ፈቲሀ ደንዲ የአደጋው መንስኤ በውል አለመታወቁንም ጠቁመዋል፡፡

በዚህም 39 የቤተሰብ አባላት ችግር ላይ መውደቃቸውን ገልጸዋል፡፡

በእሳት አደጋው ቤት ንብረታቸውን ከወደመባቸው ተጎጂዎች መካከል አንዳንዶቹ በሰጡት አስተያየት በአደጋው ምክንያት ለችግር መጋለጣቸውና ሜዳ ላይ መዉደቃቸውን ጠቅሰው የወገን ደራሽ ወገን ነው በማለት ህብረተሰቡ፣ መንግስትና ግብረሰናይ ድርጅቶች ድጋፍ እንዲያደርጉላቸውም ጥሪ አቅርቧል ሲል የዘገበው የወረዳው መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነው።
ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!
በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub:- https://youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36CxQ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *