በጉራጌ ዞን እኖር ኤነር መገር ወረዳ በሁሉም ዘርፎች የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየተከናወኑ ያሉ ስራዎች አበረታች መሆኑን ተገለጸ።


በጉራጌ ዞን እኖር ኤነር መገር ወረዳ በሁሉም ዘርፎች የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየተከናወኑ ያሉ ስራዎች አበረታች መሆኑን ተገለጸ።

በወረዳው በተለያዩ ዘርፎች ህብረተሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የልማት ስራዎች የመስክ ምልከታ ተካሂዷል።

የጉራጌ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና የግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ አበራ ወንድሙ በወረዳው በሁሉም ዘርፎች እየተከናወኑ ያሉ የልማት ስራዎችን አበረታች ናቸው።

በዞኑ በግብርናው በዘርፍ የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ከ4ሺህ 5 መቶ ሄክታር በላይ ያልታረሱ መሬቶችን ለማረስ እየተሰራ እንደሚገኝ አመላክተዋል።

በዞኑ የ30-40-30 የፍራፍሬ ስራ በስፋት እየተሰራ እንደሚገኝና በወረዳው በሙዝ፣ በአቮካዶ እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን አበረታች መሆኑና ይህም በቀጣይም አጠናክሮ በመስራት አርሶ አደሩ ተጠቃሚ ማድረግ ይገባል ብለዋል።

በዞኑ በቡና ዘርፍ እምቅ አቅም መኖሩንና በዚህም በዘንድሮው አመት ከ14 ሚሊዮን በላይ ችግኝ ለመትከል እቅድ መያዙን ያነሱት ኃላፊው ከዚህም ባሻገር በዘንድሮ አመት 69 ሚሊዮን ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኝ ለመትከል መታቀዱና ለዚህም 74 ሚሊዮን ችግኝ በችግኝ ጣቢያ መዘጋጀቱንም ተናግረዋል።

የሌማት ትሩፋት ስራ በተጠናከረ መልኩ በመስራት አርሶ አደሩ ተጠቃሚ ከማድረግ ጎን ለጎን ለወጣቶች የስራ ዕድል እየፈጠረ ይገኛል ያሉት አቶ አበራ በዚህም የዶሮ፣ የስጋ፣ የወተት፣ የንብ መንደር አስፍቶ በመስራት ህብረተሰቡ ራሱን በምግብ ከመቻል ባለፈ የገበያ ንረት ለማረጋጋት ሁሉም በቅንጅት በትኩረት መስራት እንደሚገባ ገልጸዋል።

በዘርፍ ውጤታማ ስራ ለመስራት አርሶ አደሩ በትራክተር እንዲያርስ ሞዴል አርሶ አደሮችን በማስተባበርና የዞንና የወረዳ መንግስት በመቀናጀት አቅርቦት ላይ እንደሚሰራ ተናግረዋል።

የጉራጌ ዞን የመንግስት ረዳት ተጠሪ አቶ አለማየሁ ገብረመስቀል እንዳሉት በወረዳው በጥምር ግብርናና በካፒታል ፕሮጀክት እየተሰሩ ያሉ ስራዎች አድንቁው በቀጣይም ህብረተሰቡ በሁሉም ዘርፍ ተጠቃሚ ለማድረግ አጠናክረው መስራት ይገባል።

በወረዳው አዲስ ከዚህ በፊት ያልታረሱ መሬቶች እንዲታረሱ ማድረግ፣ በአትክልትና ፍራፍሬ፣ በችግኝ ዝግጅትና በሌሎችም እየተሰሩ ያሉ ስራዎች አበረታች መሆኑን ገልጸዋል።

የእኖር ኤነር መገር ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሸምሱ ሸሀቡ በወረዳው በግብርናው ዘርፍ ያልታረሱ መሬቶች ወደ እርሻ ማስገባት ባለፈ በ30-40-30 ፍራፍሬ በትኩረት እየተሰራ መሆኑ ጠቁመው የሙዝ ችግኝ በወረዳው በማዘጋጀት ለአርሶ አደሩ ማሰራጨትና በቡና ዘርፍ ከ50 ሺህ በላይ ችግኝ መዘጋጀቱን ተናግረዋል።

በወረዳው ከ2ሺህ 5መቶ በላይ አዲስ ማሳ በማረስ በሰብል፣ በ30-40-30 በጥምር ግብርና በትኩረት እየተሰራ ይገኛል።

በወረዳው በካፒታል ፕሮጀክት ያለውን ውስን በጀት በመጠቀም የአስተዳደርና የፍርድ ቤት ህንጻዎችን እየተገነቡ መሆኑንና በተለይም የህንጻዎቹ ተገንብቶ መጠናቀቅ ወረዳው ለቢሮ ኪራይ ያወጣው የነበረውን ሀብት በማስቀረት በጀቱ ህብረተሰቡ ተጠቃሚ የሚያደርጉ ልማት ላይ እንዲውል ፍይዳው ትልቅ መሆኑን ተናግረዋል።

በወረዳው በግብርና ዘርፍ በሁሉም ዘርፍ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ስራዎችን በማጠናከር የህብረተሰቡ ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ መስራት እንዳለበትም አመላክተዋል።

የወረዳው ምክትል አስተዳዳሪና የግብርና ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ መላኩ ሳህሌ በወረዳው በአርሶ አደር ማሰልጠኛ ማዕከል በቡና፣ በ30-40-30 ፍራፍሬ፣ ቡና ችግኝ ዝግጅት እየተሰራ መሆኑን ገልጸው ይህም ለአርሶ አደሩ በማሰራጨት አርሶ አደሩ ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑንም ተናግረዋል።

በወረዳው ከዚህ በፊት ያልታረሱ 780 ሄክታር መሬት መታረሱን ገልጸው ይህም በሰብልና በፍራፍሬና በሌሎችም ለመሸፈን እንደሚሰራ ተናግረዋል።

በቡና ዘርፍ ወረዳው እምቅ አቅም እንዳለው የገለጹት ኃላፊው ለዚህም 2ሚሊዮን 5 መቶ የቡና ችግኝ መዘጋጀቱን ጠቁመው በሌማት ትሩፋት በዶሮ፣ በወተት፣ የማር፣ የስጋ መንደር በመመስረት ስራዎች በመስራት አርሶ ተጠቃሚ ለማድረግ አጠናክረው እንዲሚሰሩ ጠቁመዋል።

አቶ ሚስባህ ኢብራሂምና አቶ ወንድሙ ጭረታ በእኖር ኤነር መገር ወረዳ ኬኤዲና ሹሞሮ ቀበሌ አርሶ አደሮች ሲሆኑ በወረዳው ሙዝ፣ ቡናና እንሰት በስፋት በማምረታቸው ከራሳቸው ፍጆታ ባለፈ ለገበያ በማቅረብ ተጠቃሚ መሆናቸውን ተናግረዋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *