በጉራጌ ዞን እንደጋኝ ወረዳ 6ተኛ ዙር ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ በሠላም እንዲጠናቀቅ አስተዋፅኦ ላበረከቱ አካላት የምሥጋናና እውቅና ፕሮግራም ተካሄደ።

በወረዳው 6ተኛ ዙር ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ ሠላማዊና ዴሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ላደረጉ አካላት የምስጋና ፕሮግራም በእንደጋኝ ወረዳ ድንቁላ ከተማ ተካሒዷል።

በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የእንደጋኝ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ሠሙ ዳዊት እንደገለፁት መስከረም 20/2014 ዓ.ም የተካሔደው የ6ተኛ ዙር ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ ፍፁም ሠላማዊና ዴሞክራሢያዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የመላው ህዝብና የተፎካካሪ ፓርቲዎች ሚና የጎላ ነበር ብለዋል።

በመሆኑም ምርጫው ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ አስተዋፅኦ ያደረጉ አካላት ሁሉ ምስጋና ይገባቸዋል ብለዋል ሲል መረጃው ያደረሰን የእንደጋኝ ወረዳ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ነው።

በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36Cx

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *