በጉራጌ ዞን አበሽጌ ወረዳ በተያዘው የክረምት ወራት የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ከ21 ሺህ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች ተጠቃሚ ለማድረግ እንደሚሰራ የወረዳው አስተዳደር አስታወቀ።

የወረዳው የ2016 የበጎ ፍቃድ አገልግሎት በሆሌ ከተማ መዘጋጃ ቤት የአንድ አቅመ ደካማ እናት አዲስ ቤት በመገንባት ተጀመረ።

በዘንድሮ ክረምት ከ21 ሺህ በላይ የማህበረሰብ ክፍሎች በበጎ ፍቃድ አገልግሎት በማሳተፍ ከ45 ሺህ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የተለያዩ የልማት ስራዎች ለማከናወን ታቅዶ እየተሰራ ነዉ።

በወረዳዉ በ30 ቀበሌዎች የአዲስ ቤት ግንባታና የጥገና ስራዎች ይሰራሉ።

የጉራጌ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ ሀላፊ አቶ ፈይሰል ሀሰን በአበሽጌ ወረዳ የክረምት በጎ ፍቃድ ማስጀመሪያ ላይ ተገኝተዉ እንዳሉት በዞኑ በሁሉም ወረዳዎችና ከተማ መስተዳደሮች ማህበረሰቡንና ባለሀብቱን በማስተባበር በበጋዉ ወቅት በርካታ ማህበረሰቡን የሚጥቅሙ የልማት ሰራዎች ማከናወን መቻሉና በዚህም ተጨባጭ ዉጤት ማምጣት መቻሉም አስታዉሰዋል።

የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ስራ ትልቅ የህሊና እርካታ የሚገኝበት እንደሆነም አስረድተዉ በዚህ የክረምት ወቅት በዞኑ በ14 የልማት ዘርፎች 4 መቶ 21 ሺህ 59 የማህበረሰብ ክፍሎችን በማሳተፍ ከ6 መቶ 60 ሺህ 225 የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ስራም እንደሚሰራና በዚህም በጎ ስራ ከመንግስት ይወጣ የነበረዉ 238 ሚሊየን 398 ሺህ 994 ብር ለማዳን ታቅዶ እየተሰራ መሆኑም አስረድተዋል።

የአበሽጌ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ካሱ ጁሀር በሆሌ ከተማ የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት የአዲስ ቤት ግንባታ በአስጀመሩበት ወቅት እንዳሉት የወረዳዉና የቀበሌ መላዉ አመራር እንዲሁም ከማህበረሰቡ ጋር የክረምት በጎ ፍቃድ አስመልክቶ በቂ ዉይይት በማድረግ ወደ ስራ መገባቱም ተናግረዋል።

በወረዳዉ በ30 ቀበሌዎች ዉስጥ አንድ አዲስ ቤት የመገንባትና አንድ ቤት የጥገና ስራ ለመስራት በእቅድ ተይዞ ከዛሬ ጀምሮ ወደ ተግባር መገባቱም አብራርተዋል።

በዛሬዉ ዕለት በሆሌ ከተማ ወይዘሮ መስቀሌ አጉዝ ቤት ግንባታ ሙሉ ለሙሉ በወረዳዉ የሚሸፈን እንደሆነም አመላክተዉ ከነገ ጀምሮ በሁሉም ቀበሌዎች የሚጀመር መሆኑም ተናግረዋል።

ወጣቶችና ማህበረሰቡ ከቤት ግንባታና ጥገና ጎን ለጎን ሌሎች በርካታ ማህበረሰቡን የሚጠቅሙ የልማት ስራዎች እንደሚሰሩም አስረድተዋል።

ሰኔ 30/2016 ዓመተ ምህረት ከወረዳዉ አጠቃላይ ሙህራኖች ጋር መድረክ በመፍጠር ተገቢዉን ዉይይት በማድረግ በሀይስኩሎች አካባቢ ለመምህራን የተወሰነ በጀት ተሸፍኖላቸዉ ተማሪዎች የክረምት ትምህርት እንዲማሩ የማድረግ ስራ እንደሚሰራም አስረድተዋል።

ወጣቱ በየአካባቢዉ በሰላሙ ጉዳይና በተለያዩ የልማት ስራዎች ላይ የራሱ አሻራ ማኖር አለበት ያሉት አስተዳዳሪዉ በወረዳዉ በዘንድሮ የክረምት ወቅት የተያዙ ግቦች ስኬታማ ለማድረግ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች የበኩላቸዉ ሊወጡ እንደሚገባም ጥሪ አቅርበዋል።

የአበሽጌ ወረዳ ወጣቶችና ስፖርት ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ቴድሮስ አካሉ እንዳሉት በወረዳዉ በበጋ ወቅት ከ25 ሺህ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች በማሳተፍ ከ50 ሺህ በላይ የሚሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎችን የሚጠቅሙ ልማቶች ማከናወን ተችሏል ብለዉ በዚህም ከ11 ሚሊየን በላይ ብር ከመንግስት ይወጣ የነቀረዉ ሀብት ማዳን መቻሉም አስታዉሰዋል።

በዚህ ክረምት በወረዳዉ በበጎ ፍቃድ አገልግሎት የታያዙ እቅዶችን ለማሳካት በሁሉም አካባቢዎች የንቅናቄ መድረክ ተፈጥሯል ብለዉ በሁሉም አካባቢዎች አረጋዉያንና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ለመደገፍ ይሰራል ብለዋል።

በዚህ የክረምት ወቅት ከ21 ሺህ በላይ የማህበረሰብ ክፍሎች በበጎ ፍቃድ አገልግሎት በማሳተፍ ከ45 ሺህ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የልማት ስራዎች እንደሚከናወንም አብራርተዋል።

በአበሽጌ ወረዳ በሆሌ ከተማ የሚኖሩ አቅመ ደካማ እናት ወይዘሮ መስቀሌ አጉዝ እንዳሉት ይኖሩበት የነበረዉ ቤት በላያቸዉ ላይ ሊወድቅ የደረሰና ክረምት ሲመጣ በጎርፍና ብርድ ይሰቃዩ እንደነበረም ተናግረዉ ይህንንም ችግር ለመቅረፍ የወረዳዉ መንግስት ሙሉ ወጪ አዉጥቶ ስለሚገነባላቸዉ መደሰታቸዉም ተናግረዋል።

One Comment:

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *