በጉራጌ ዞን ቸሃ ወረዳ ከመንግስት በተመቻቸላቸው ብድር ወስደው በከተማ ስራ እድል ፈጠራ የተሰማሩ ወጣቶች በኑሯቸው ላይ ለውጥ ማምጣት መቻላቸውን ገለጹ፡፡


በወረዳው ከ89 በላይ ማህበራት በከተማ ስራ እድል ፈጠራ ዘርፍ ተደራጅተው ወደ ስራ መግባታቸውን የወረዳው ስራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዞች ልማት ጽ/ቤት አስታውቋል፡፡

በጉራጌ ዞን ቸሃ ወረዳ ካነጋገርናቸው በማህበር ተደራጅተው እየሰሩ ከሚገኙ ወጣቶች መካከል ኑርበገን መሃመድ፣ ፈርሁ ታጁና መሃመድ አወል ይገኙበታል።

ወጣቶቹ ከዚህ ቀደም ስራ እንዳልነበራቸው በመግለጽ አሁን ላይ በብረታ ብረት፣ በእንጨትና ግንባታ ስራ ላይ በመሰማራት እየሰሩ እንደሚገኙ ተናግረዋል።

ወረዳው ባመቻቸላቸው የብድር አቅርቦት በመጠቀም ወደ ስራ መግባታቸውን ወጣቶቹ አውስተው አሁን ላይ ውጤታማ መሆን በመቻላቸው ገቢያቸውን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱን አስረድተዋል፡፡

በዚህም ኢኮኖሚያቸው እያደገ በመምጣቱ በኑሮአቸው ላይ ተጨባጭ ለውጥ ማምጣት መቻላቸውን ገልጸዋል፡፡ ይሁን እንጂ መንግስት በቀጣይ የመስሪያ ቦታና ሌሎችም የሚያደርጋቸው የድጋፍና ክትትል ስራዎች ማጠናከር እንዳለበት ተናግረዋል፡፡

ወ/ሮ አጃኢባት የሱፍ በቸሃ ወረዳ ስራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዞች ልማት ጽ/ቤት የማዕከል አስተባባሪ ናቸው፡፡ በወረዳው በከተማ ስራ እድል ፈጠራ ዘርፍ በ3ቱም ማዘጋጃ ቤቶች በርካታ ማህበራት ወደ ስራ ገብተዋል ብለዋል፡፡

እንደ ጽ/ቤት ለማህበራቱ በወር 2 ጊዜ ድጋፍና ክትትል እንደሚደረግላቸዉ የገለፁት አስተባባሪዋ ከተቋማት ጋር በመተባበርም የክህሎት ስልጠና እንደሚሰጣቸው ገልጸዋል፡፡

የቸሃ ወረዳ ስራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዞች ልማት ጽ ቤት ኃላፊ አቶ ሻፊ ቃዲ በበኩላቸው በወረዳው ስራ አጥ ወጣቶችን በመለየት ወደ ስራ እንዲገቡ ለማድረግ በተሰራው ስራ 89 ማህበራት በማደራጀት በከተማ ስራ እድል ፈጠራ በተለያዩ የስራዘርፎች እንዲሰማሩ ተደርጓል ብለዋል፡፡

ወጣቶቹ ወደ ስራ ከገቡ በኋላም ውጤታማ እንዲሆኑ ድጋፍና ክትትል ከማድረግ በተጨማሪ የገበያ አማራጮች እንዲመቻችላቸዉም እየተሰራ እንደሚገኝም ወልቂጤ ኤፍ ኤም ሬድዮ ዘግቦታል።

= ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!

በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36Cx

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *