በጉራጌ ዞን ቡታጅራ ከተማ ይካሄዳል ተብሎ በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የኬሮድ የ10 ኪሎ ሜትር ሩጫ ተጀመረ!

ሩጫውን ለመሳተፍ በርካታ አትሌቶች ውቢት ቡታጅራ በመግባት በሩጫው በመሳተፍ ከተማዋን በስፖርት አድምቀዋታል።

ህብረተሰቡም ከተማዋን ለሩጫው አመቺ እንድትሆንና እንግዶችን ሲቀበሉ ቆይተው ዛሬ ደግሞ በሩጫው እየተሳተፉ ይገኛል።

በዚህ ፕሮግራም የማህበረሰብ ሁሉ አቀፍ ስፖርት በመካሄድ ላይ ይገኛል።

የሁልጊዜ ውቢት ቡታጅራ ዛሬም ከንጋቱ ጀምሮ በስፖርቱ ድባብ የበለጠ አሸብርቃ ዝግጅቱን እያስተናገደች ነው።

የኬሮድ ስፖርትና ልማት ማህበር
ለተወዳዳሪዎች እንደየደረጃቸው ሽልማት ያዘጋጀ ሲሆን አሸናፊዎቹም ይህን ለማግኘት ጥብቅ ፉክክር ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል።

በፕሮግራሙ የተገኙት ኮማንደር አትሌት ጌጤ ዌሜ ሩጫውን አስጀምረውታል።

በፕሮግራሙ የፌደራል፣የክልል የዞን፣ የቡታጅራና መስቃን ዙሪያ ያሉ የህብረተሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል።

” ኑ ለኢትዮጵያ ሰላምና ልማት እንሩጥ!”

በመረጃ ምንጭነት ገፃችን ምርጫዎ ስላደረጉ እናመሰግናለን!
= ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!
በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub:- https://youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36CxQ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *