በጉራጌ ዞን በ2015 የትምህርት ዘመን ከ63 ሺህ በላይ የ8ኛ እና 6ተኛ ክፍል ተማሪዎች ለመመዘን ያሚያስችሉ ቅድመ ዝግጅቶች መደረጋቸው ተገለጸ።

ሰኔ 18/2015

በጉራጌ ዞን በ2015 የትምህርት ዘመን ከ63 ሺህ በላይ የ8ኛ እና 6ተኛ ክፍል ተማሪዎች ለመመዘን ያሚያስችሉ ቅድመ ዝግጅቶች መደረጋቸው ተገለጸ።

በዞኑ በ8ተኛ ክፍል ክልል አቀፍና በ6ተኛ ክፍል ዞን አቀፍ የዕርከን ማጠናቀቂያ ፈተናዎች አሰጣጥና አስተዳደር ላይ ከፈተና አስፈጻሚዎች እና ከትምህርት ባለድርሻ አካላት ጋር የኦረንቴሽን እና የምክክር መድረክ በወልቂጤ ከተማ ተካሂዷል ።

የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ በምክክር መድረኩ ላይ እንደተናገሩት በትምህርቱ ዘርፍ ያጋጠሙ ችግሮች ለመፍታት ባለድርሻ አካላት በትኩረት ሊሰሩ ይገባል ብለዋል።

ከዚህ በፊት ተማሪዎች በየደረጃው ማግኘት ያለባቸው እውቅትና ክህሎት ባለማግኘታቸውና በተገቢው ባለመመዘናቸው በትምህርት ጥራት ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ማሳደሩ ገልጸዋል ።

ትክክለኛና ብቃት ያለው ተማሪ ለማፍራት በትክክለኛ ምዘና ስርአት እንዲያልፉ ማድረግ ይገባል ያሉት ዋና አስተዳዳሪው ተማሪዎች ወደሚቀጥለው የክፍል ደረጃ በማሻገር የትምህርት ስርአቱን ማሻሻል እንደሚገባ አስገንዝበዋል ።

እንደ አቶ ላጫ ጋሩማ ገለጻ በየደረጃው ተገቢ የሆነ ትምህርት በመስጠት ተማሪዎችን በጥራት በማሳለፍ ኩርጃ የማይታሰብ በማድረግ የነገ ሀገር ተረካቢ ዜጋ ለማፍራት በቅንጅት መሰራት እንዳለበት ተናግረዋል።

ተማሪዎች ኩረጃ አገርና ራሳቸው የሚጎዳ ተግባር መሆኑን ተረድተው የነገ ህይወታቸውን የተሻለና እንዲሆን ራሳቸውን በንባብ በማጎልበት በቂ እውቀቱና ክህሎት እንዲያገኙ መስራት ይጠበቅባቸዋል።

በቀጣይ የትምህርት ዘመን ያልተሟሉ መጽሐፍቶችን ለማሟላት በትኩረት እንደሚሰሩና ማህበረሰቡም ማገዝ እንዳለበት ተናግረዋል ።

የጉራጌ ዞን ትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ አስከብር ወልዴ በበኩላቸው በ2015 የትምህርት ዘመን 32 ሺህ 1 መቶ 32 የ8ኛ ክፍልና 31 ሺህ 1 መቶ 65 የ 6ኛ ክፍል ተማሪዎች ለመመዘን ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁን ገልጸዋል ።

በፈተና አሰጣጥ ሂደት ላይ ኩረጃ ለመከላከልና ለማስቀረት እየተሰራ መሆኑን የተናገሩት አቶ አስከብር ወልዴ የፈተና አስፈጻሚዎችና የትምህርት ባለድርሻ አካላት ተማሪዎች በራሳቸው እንዲተማመኑና ኩረጃን እንዲጸየፉ በትኩረት መስራት እንደሚጠበቅባቸው አስረድተዋል ።

የዘንድሮው የ8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና እና የ6ተኛ ክፍል ዞን አቀፍ የዕርከን ማጠቃለያ ፈተናዎች የሚሰጡት ተፈታኞቹ ከሚማሩባቸው ትምህርት ቤቶች በተለየ በክላስተር እንደሚፈተኑ የተደረገ ሲሆን ፈተናው ከሰኔ 26/2015 ጀምሮ ፈተናው እንደሚሰጥ አቶ አስከብር ገልጸዋል። በመሆኑም ተማሪዎና ወላጆች የደህንነት ስጋት እንዳይሰማቸው እንክብካቤና ጥበቃ እንደሚደረግላቸው በመግለፅ።

ማንናቸውም መደበኛ፣ የማታና የግል ተፈታኝ ተማሪዎች ተማሪዎች ወደ መፈተኛ አዳራሽ ሲገቡ የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎችን እና የተከለከሉ ቁሳቁሶች ይዘው መግባት እንደሌለባቸው ጠቁመው
ወደ ፈተና ቅጥር ግቢም ሆነ አዳራሽ ቢገቡ ከፈተና አዳራሹም ሆነ ከግቢ ወዲያውኑ እንዲወጡ ይደረጋል ። ተማሪዎች ሳይጨናነቁ እንዲፈተኑ ለአንድ ተማሪ አንድ ምቹ ወንበርና ለ30 ተማሪ በአንድ ክፍል ለመፈተን መሰራቱን ገልጸዋል ።

የፈተና ደንብና ሥነ-ሥርዓት ጥሰው የተገኙ ተማሪዎች ውጤት በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የሚሰረዝ መሆኑን አቶ አስከብር አስረድተዋል ።

የኦረንቴሽን መድረኩ ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት ተማሪዎች ከአካባቢያቸው ተነስተው ወደሚፈተኑበት አከባቢ እስኪድርሱና ፈተናቸውን ጨረሰው እስኪመለሱ ድረስ አስፈላጊውን እንክብካቤና ጥበቃ ለማድረግ ዝግጅት ማጠናቀቃቸውን ተናግረዋል ።

እንዲሁም ለተማሪዎችም ለፈተና የሚሆን በቂ የትምህርት ዝግጅት እንዲያገኙ መባደረጉት የተናገሩት ተሳታፊዎቹ ፈተናዎችን ከኩረጃ ነጻ በሆነ መልኩ ለመፈተን እና ሌሎችንም አስፈላጊ የሆኑ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ማጠናቀቃቸውን ተናግረዋል ።

በእለቱም በወልቂጤ ያበሩስ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የችግኝ ተከላ መርሀ ግብር ተካሂዷል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *