በጌታ ወረዳ በበጋ ወቅት የለሙ የመደበኛ መስኖ፣የበጋ መስኖ ስንዴና የተፈጥሮ ሀብት እንክብካቤ እንዲሁም የመኖ ስራዎች የመስክ ምልከታ ተካሄደ።
የጉራጌ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና የግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ አበራ ወንድሙ በመስክ ምልከታ ወቅት እንደተናገሩት በዞኑ በበጋ መስኖ ስንዴ ከለማው 1 ሺህ 224 ሄክታር መሬት በአሁን ወቅት በ450 ሄክታር መሬት ላይ የሚገኘው ምርት መሰብሰብ ተችሏል።
የበጋ መስኖ ስንዴ ምርታማና የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ጉልህ ሚና እንደሚጫወት የገለጹት ምክትል አስተዳዳሪው ከመደበኛው የስንዴ ምርት በበለጠ የበጋ መስኖ ስንዴ በሄክታር እስከ 55 በኩንታል ምርት እንደሚያስገኝ አስገንዝበዋል።
በዞኑ የበልግ ወቅት ተግባር ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን ከ82 ሺህ በላይ ሄክታር መሬት በተለያዩ ሰብሎች ለማልማት እየተሰራ መሆኑን አቶ አበራ ገልጸዋል።
እስካሁን 75 ሺህ ሄክታር መሬት መታረሱን የተናገሩት ኃላፊው ከታረሰው መሬት ውስጥ 17 ሺህ ሄክታር መሬት በድንች ሰብል የተሸፈነ ሲሆን ቀሪዎቹ ደግሞ በበቆሎና በሌሎች ሰብሎች ለመሸፈን እርብርብ እየተደረገ መሆኑን አስረድተዋል።
በጌታ ወረዳ በተለያዩ ቀበሌዎች የተከናወኑ የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራዎች፣ የበጋ መስኖ ስንዴ፣ የመደበኛ መስኖ፣ የበልግ ስራዎች እንቅስቃሴ አበረታች በመሆናቸው በመስክ ምልከታ የተገኙ ምርጥ ተሞክሮዎች ቀምሮ ማስፋት ይገባል ብለዋል።
የጌታ ወረዳ ግብርና ጽህፈት ቤት ኃላፊና የወረዳው ምክትል አስተዳዳሪ አቶ በየነ ጠንክር በበኩላቸው በወረዳው ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ለአርሶ አደሩ ድጋፍና ክትትል እየተደረገለት በመሆኑ ተጠቃሚነቱን እያደገ ይገኛል ብለዋል።
ከዚህ ቀደም በወረዳው በሄክታር ይገኝ የነበረው 40 ኩንታል የስንዴ ምርት ወደ 55 ኮንታል ለማሳደግ ለአካባቢው ስነምህዳር ተስማሚና የተሻሻለ ዝርያ ያላቸው የስንዴ ዘር ማቅረብ መቻሉን አስረድተዋል።
የስንዴ ማሳን ማስፋፋት ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ እንዳለው የተናገሩት አቶ በየነ አርሶ አደሩ የሚፈጠርለት ግንዛቤ እና የሚቀርብለት ቴክኖሎጂ ተጠቅሞ ምርትና ምርታማነቱን በማሳደግ ከራሱ ፍጆታ ባለፈ ለገበያ ማቅረብ እንዲችል ይሰራል ብለዋል።
አቶ ሱልጣን ሱለይማን በወርኮ ቀበሌ አርሶ አደር ሲሆኑ አቶ በድሩ መሀመድ በፉቻሬ ቀበሌ አርሶ አደር ናቸው።አርሶ አደሮቹ በሰጡት አስተያየት የባለሙያዎች ምክረሀሳብ ተግባራዊ በማድረጋቸው ተጠቃሚ ሆነዋል።
የበጋ መስኖ ስንዴ ለአካባቢያቸው አዲስና ያልተለመደ በመሆኑ ውጤታማ እንደሚያደርጋቸው እምነት እንዳልነበራቸው የተናገሩት አርሶ አደሮቹ መንግስት ባደረገላቸው ሁሉአቀፍ ድጋፍ ከመደበኛ የስንዴ ምርት የተሻለ ውጤት እንደሚያስገኝላቸው አረጋግጠዋል።
በመሆኑም በዚህ አመት ያገኙትን ልምድ ተጠቅመው በቀጣይ የበጋ መስኖ ስንዴ በስፋት በማምረት ከራሳቸው አልፎ ለገበያ ማቅረብ እንዲችሉ ትኩረት ሰጥተው እንደሚሰሩ ገልጸዋል።
በመረጃ ምንጭነት ገፃችን ምርጫዎ ስላደረጉ እናመሰግናለን!
= ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!
በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN