በጉራጌ ዞን በግብርና ዘርፍ የሚታየው ውጤት ከውጭ ሀገር እርዳታና ድጋፍ ማስቀረት እንደምንችል ማሳያ ነው ሲሉ የኢ.ፌ.ድ.ሪ የቆላማ አካባቢዎችና የመስኖ ሚኒስተር ኢንጂነር አይሻ መሀመድ ገለጹ።

መስከረም 13/2015 ዓ.ም

በጉራጌ ዞን በግብርና ዘርፍ የሚታየው ውጤት ከውጭ ሀገር እርዳታና ድጋፍ ማስቀረት እንደምንችል ማሳያ ነው ሲሉ የኢ.ፌ.ድ.ሪ የቆላማ አካባቢዎችና የመስኖ ሚኒስተር ኢንጂነር አይሻ መሀመድ ገለጹ።

የፌደራል የተለያዩ ሚኒስተሮችና የክልሉ አመራሮች በጉራጌ ዞን ሶዶ ወረዳ በመኸር የለማ የግብርና ማሳ በዛሬው እለት ጎብኝቷል።

የቆላማ አካባቢዎችና የመስኖ ሚኒስቴር ሚኒስተር ኢንጂነር አይሻ መሀመድ እንዳሉት በጉራጌ ዞን በግብርናው ዘርፍ የሚታየው ውጤት እንደሀገር ምግብን በራሳችን እንደምንችልና የውጭ ሀገር እርዳታና ድጋፍ ማሳያ ነው ሲሉ ገልጸዋል።

የጉራጌ ማህበረሰብ የስራ ታታሪነቱን በመጠቀም ክፍት መሬቶችን ጾማቸው እንዳያድሩ መስራት ይጠበቃል ያሉ ሲሆን እንደ ሀገር የገጠመው የማዳበርያ እጥረት ችግር ለማካካስ የተፈጥሮ ማዳበርያ መጠቀም እንደሚያስፈልግ መክረዋል።

አክለውም አርሶ አደሮች በአመት 1 ጊዜ ከማምረትና ከዝናብ ጥገኝነት ወጥተው በአመት 3 ጊዜ እንዲያመርቱ በአካባቢው ያሉ የውሃና የመስኖ አማራጮችን ጥናት በማድረግ የበለጠ እንደሚሰራበት ተናግሯል።

የኢፌድሪ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስተር ወ/ሮ ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) ሴቶች በልማቱ ግንባር ቀደም ሆነው በመስራታቸው እንደዚህ አይነት ውጤት በማሳየታቸው ቀጣይም በሴቶች ላይ ብዙ መስራት እንደሚያስፈልግ አመላካች ነው።

ሴቶች የኢኮኖሚ አቅማቸው ለማሳደግ ከወንዶች ጋር በማደራጀት በአንድነት በመስራታቸው እንደ ሀገር አንድ ሆነን ውጤት ማምጣት እንደምንችል ማሳያ ተግባር ነው ብለዋል።

የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ በንግግራቸው እንደገለጹት በወረዳው በተሰሩ የመኸር ስራዎች ለሌላ አካባቢ ማስተማርያ የሚሆኑ ተግባራት ናቸው ሲሉ ተናግሯል።

በገጠር ላይ የሚሰሩ መሰረታዊ የኢኮኖሚ ስራዎች ሲጠናከሩ ከተሜነት እንዲስፋፋ የሚያደርጉ በመሆኑ የአርሶ አደሩ ኢኮኖሚ እንዲያድግ በትኩረት ይሰራበታል ብለዋል።

በመሆኑም በአካባቢው ያሉ አምራች አርሶ አደሮች የሚያመርቱት ምርት ያለ ደላላ በቀላሉ ለሚፈለገው አላማ እንዲደርሱ ቀጥተኛ ድጋፍ እንደሚደረግ አስታውቀው በአካባቢው የሚነሱ የመሰረተ ልማት ጥያቄዎች ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን ይሰራበታል ነው ያሉት።

የደቡብ ክልል ግብርና ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ አድማሱ አወቀ የምግብ ዋስትናችንን ለማረጋገጥ በተሰሩ ስራዎች እስካሁን 8መቶ 87 ሺህ ሄክታር መሬት በተለያዩ ሰብሎች የተሸፈነ ሲሆን 7 መቶ 50 ሺህ ኩንታል ማዳበርያ ለአርሶ አደሩ መሰራጨቱ አስታውቋል።

በዚህም 1መቶ 80 ሺህ መሬት በስንዴ ማሳ መሸፈኑ ገልጸዋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *