በጉራጌ ዞን በገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ በ63 ሚሊዮን ብር ወጪ የተገነባው የጅማ ወለኔ የከንተዋት ዘቢደር የ38 ኪሎሜት መንገድ ግንባታ ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት መደረጉን የደቡብ ክልል መንገዶች ባለስልጣን ገለፀ።


የጉራጌ ብሔር በመንገድ ልማት ያለው የቆየ ልምድ በቀጣይም ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አስታወቀ ።
የደቡብ ክልል መንገድ ልማት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር አበባየሁ ታደሰ እንደገለጹት በክልሉ በተያዘው በጀት ዓመት ከ420 ኪ/ሜ በላይ በመደበኛ መንገድ ግንባታ ለማጠናቀቅ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል።
የጉራጌ ዞን ህዝብ ሠላሙንና አንድነቱን ከመቼውም ጊዜ በላቀ ሆኔታ አጠናክሮ በመቀጠሉ በቀደምት አባቶች የወረሰውን የመንገድና የሌሎች መሰረተ ልማት የማስፋፋት ልምድ ማስቀል ይገባል ብለዋል።
በዕለቱ ለምረቃ የበቃው መንገድ የህብረተሰቡን የእርስ በርስ ትስስር ከማጠናከር ባለፈ እንደ ሀገር ለተጀመሩ ለሌሎች የልማት ስራዎች የጎላ ሚና እንዳለው አውስተዋል።
በደቡብ ክልል መንገዶች ባለስልጣን በጉብሬ ዲስትሪክት ጅማ ወለኔ ከንተዋት ዘቢዳር ተገንብቶ የተመረቀው የ38 ኪሎ ሜትር መንገድ የ5 ወረዳ ህዝቦችንና በርካታ ቀበሌዎችን በማስተሳሰር ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው ብለዋል።
የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ በምርቃቱ ላይ እንደገለጹት የጉራጌ ማህበረሰብ ከጥንትም ጀምሮ የመንገድን ልማት ጠቀሜታን በአግባቡ በመረዳት ራስ አገዝ የመንገድ ልማት ድርጅት በማቋቋም በአርዓያነት የሚጠቀሱ ስራዎችን ሰርቶ ያሳየ መሆኑን አስተውሰዋል።
የዞኑ መንግስት ማህበረሰቡን የመንገድ ልማት ተጠቃሚ እንዲሆን ለማስቻል ከሚመለከታቸውን የመንግሥት ተቋማት ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በበመተባበር ሰፊ ስራ እየሰራ ነው ብለዋል ።
የመንገድ ልማት ሌሎች በርካታ የልማት ስራዎቻችን ውጤታማ ለማድረግ ድርሻው የጎላ ነው ያሉት ዋና አስተዳዳሪ በዘርፉ ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በቅንጅት መስራት ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።
የደቡብ ክልሉ መንገዶች ባለስልጣን ዋና ስራስኪያጅ አቶ ዘብዲዮስ ኤካ እንደገለፁት በ63 ሚሊዮ ብር ወጪ ተገንብቶ ለምርቃት የበቃው የወለኔ ከንተዋት ዘቢደር መንገድ ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳን ከሙህር አክሊልና ከሌሎች አጎራባች ወረዳ ህዝብ ጋር በማስተሳሰር ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጠቀሜታ ይኖረዋል ብለዋል።
የመንገዱ ተጠቃሚ ማህበረሰብ ይህ ምቹ ሁኔታውን በመጠቀም የአከባቢ ሠላም በመጠበቅ፣ የግብርና ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ የራሳችውንና የቤተሰባቸው የኑሮ ሁኔታ በማሻሻል እንደ ሀገር ለሚደረገው ሁለንትናዊ የብልጽግና ጉዞ የድርሻቸውን ሊወጡ ይገባል ብለዋል ።
በደቡብ ክልል መንገዶች ባለስልጣን የጉብሬ ዲስትሪክት ስራአስኪያጅ አቶ አሰፋ አካሉ በበኩላቸው ለአንድ አካባቢ የመንገድ መሠረተ ልማት አገልግሎት መሟላት ለሁሉም ኢኮኖሚያዊናማህበራዊ የልማት ዘርፎች መሳካት የሚያበረክተው አስተዋፅኦ ከፍተኛ ነው ብለዋል።
በጉብሬ ዲስትሪክት 2015 በጀት አመት የ13 መንገዶች ፕሮጀክት ግንባታ፣ የ22ጥገና እና የ7 ድልድይ ግንባታን በተደራጀ መንገድ ርብርብ አየተደረገ ነው ያሉት አቶ አሰፋ የጅማ ወለኔ የከንተዋት ዘቢደር የ38ኪሎሜትር መንገድ ፕሮጀክት ትልቁና ብዙ ዋጋ የተከፈለበት ነው ብለዋል።
የዲስትሪክቱ ባለሞያዎች ”በእኔ ምክንያት አንድም ስራ አይስተጓጎልም ”በሚል መርህ ለከፈሉት ከፍተኛ መስዕትነትና በየደረጃው አስተዋጽኦ ላበረከቱ ባለድርሻ ሁሉ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
በሰው ኃይል አደረጃጀት በትኩረት በመስራት በስራ ባህላችን ለውጥ ማምጣት እንደሚቻል በተግባር የታየበትና ለሌሎች ፕሮጀክቶች መልካም ተሞክሮ የተቀሰመበት ነው ብለዋል።
መንገዱ ለረጅም ጊዜ አገልግሎት መስጠት እንዲችል መስጠት እንዲችል ህበረሰብ አንደ አይኑ ብሌን መጠበቅና መንከባከ እንዳለበት አሳስበዋል።
ከአነጋገርናቸው የአካባቢው ነዋሪዎች መካከል ወ/ሮ ሀዋ አህመድ ወ/ሮ ሰኒያ ሱልጣንና አቶ አጥራ አህመድ በሰጡት አሰተያየት መንገዱ ሳይሰራ በፊት ለተለያዩ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጫና ይደርስባቸው እንደነበረ ተናግረዋል።
አሁን ላይ መንገድ ግንባታ ተጠናቆ በመመረቁ ደሰታቸው ወደር የሌለው ተናግረዋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *