በጉራጌ ዞን በገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ሙስሊም ኤይድ USA የተሰኘ ግብረ ሰናይ ድርጅት በ17 ሚሊየን ብር ወጪ የተለያዩ የህክምና ቁሳቁሶችን ለወረዳው የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ድጋፍ አደረገ።

በጉራጌ ዞን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒል ሙስሊም ኤይድ USA የተሰኘ ግብረ ሰናይ ድርጅት በዋርካ ኢትዮጵያ ዴቨሎፕመንት ኦርጋናይዜሽን አስተባባሪነት 17 ሚሊየን ብር የሚገመት የተለያዩ የህክምና ቁሳቁስ ዛሬ ለሆስፒታሉ አስረክበዋል።

የዋርካ ኢትዮጵያ ዴቨሎፕመንት ኦርጋናይዜሽን ቦርድ ሰብሳቢ ዶክተር ሪያድ ኢብራሂም በርክብክቡ ወቅት እንደገለፁት ግብረሰናይ ድርጅቱ በዞናችን በትምህርት፣ በጤና እንዲሁም በተለያዩ ማህበራዊ ችግሮች ላይ እየሰራ ያለ ድርጅት ነው።

እስካሁን እየሰራቸው ካሉ ስራዎች ባሻገር ወደፊትም በዞኑ ላሉ ወረዳዎችና የጤና ተቋማት ላይ የተለያዩ የህክምና ቁሳቁስና የህክምና አገልግሎቶች ለመስጠት አቅዶ እየሰራ ነው ብለዋል።

የህክምና ቁሳቁሶቹ አልትራሳውንድ፣ለተኝቶ መታከሚያ ዘመናዊ አልጋ፣የጨቅላ ህፃናት ማሞቂያ ማሽን፣ስትራላይዘርና ሌሎችም ቁሳቁሶች ጨምሮ በገንዘብ ሲተመን 17 ሚሊየን ብር ወጪ የተደረገባቸው መሆኑ በመጥቀስ ድርጅቱ ከአሁን በፊት የአይን ሞራ ግሮዶሽ ገፈፋ፣የትምህርት ቤቶች ግንባታ እንዲሁም የውሃ ጉድጓድ መቆፈር ተግባራትን ማከናወኑን ዶክተር ሪያድ አክለው ገልፀዋል።

የጉራጌ ዞን ጤና መምሪያ ሀላፊ አቶ ሸምሱ አማን በርክብክቡ ወቅት እንደተናገሩት አሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታ 17 ሚሊየን ብር ድጋፍ ለዞኑ መንግስትና ለሆስፒታሉ በርካታ ጉድለት የሚሞላ እገዛ በመሆኑ ለተደገው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል ።

ከአሁን በፊት ሆስፒታሉ በነበረው የግብአት እጥረት በቂ የህክምና አገልግሎት ለህብረተሰቡ አለመስጠቱን ጠቅሰው አሁን በተደረገው ድጋፍ የሆስፒታሉ አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ከፍተኛ መሻሻል የሚያመጣ መሆኑ ገልጸዋል።

የተደረገውን ድጋፍ የተቋሙ ባለሙያዎች እና የወረዳው ማህበረሰብ በባለቤትነት ሊጠብቀውና ሊጠቀምበት ይገባል በማለት አሳስበዋል።

የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሙራድ ረሻድ እንደተናገሩት ለተደረገላቸው ድጋፍ በማመስገን በድጋፉ የመጡ የህክምና ግብአቶች በቀጣይ የተቋሙ አገልግሎት በማሻሻል ረገድ የጎላ አስተዋጽኦ አላቸው ብለዋል።

አስተዳዳሪው አክለውም 17 ሚሊየን ብር የሚገመት የህክምና ቁሳቁስ ለወረዳቸው እንዲደርስ አስተዋፅኦ ላበረከቱት አካላትና ድርጅት የምስጋና የምስክር ወረቀት አበርክተዋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።

በመረጃ ምንጭነት ገፃችን ምርጫዎ ስላደረጉ እናመሰግናለን!

= ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!
በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *