በጉራጌ ዞን በዘንድሮ በክረምት ወራት 108 ሚሊዮን ችግኞችን ለመትከል ታቅዶ እየተሰራ መሆኑን የጉራጌ ዞን ደን አካባቢ ጥበቃ ልማት ጽ/ቤት አስታውቋል።

እስከአሁን ድረስ ከ55 ሚሊዮን ችግኞች በላይ መተከላቸውን ጽ/ቤት አስታውቋል።

የጉራጌ ዞን ደንና አካባቢ ጥበቃ ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ምህረት ወንበርጋ በየ አመቱ በተተከሉ ችግኞች በአየር ንብረት ለውጥና በመሬት አጠባበቅ ለውጦች ተመዝግበዋል።

በ2008 የዞኑ የደን ሽፋን 19 በመቶ ከነበረበት አሁን 24 በመቶ ደርሷል ተብለዋል ።

የተመዘገበው ውጤት በቀጣይም አጠናክሮ ለማስቀጠል በተያዘው ክረምት 108 ሚሊዮን ችግኞችን ለመትከል ታቅዶ እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።

በበጋው ወራት ችግኞችን በመንግስት፣በግለሰብ፣የችግኝ ፍራፍሬ ማህበራት አድራጅቶች ችግኝ የማፍላት ስራ እየተሰራበት እንደ ነበር አስታውሰው 13ሺ ኪሎ ግራም የደን የዘር ችግኝ ተሰራጭቷል።

እንደ ኃላፊው ገለጻ ችግኞችን ለመትከል 23 ሺ ሄክታር መሬት የተከላ ቦታ መዘጋጀቱ ገልጸው 91 ሚሊየን ጉድጓዶችን ተቆፍሯል ብለዋል።

ችግኞቹ የሚተከሉት በትምህርት ቤቶች፣በወል መሬቶች፣በመንግስትና በሀይማኖት ተቋማት፣በተጎዱ መሬቶች ላይ መሆኑን ተናግረዋል።

በአጠቃላይ በዘንድሮው የችግኝ ተከላ ከ4 መቶ 17 ሺ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳታፊ እንደሚሆኑ ያስታወቁት ኃላፊው በ2013 ዓ.ም ከተተከሉት ችግኞች 84 ፐርሰንቱ መጽደቃቸው የተናገሩት አቶ ምህረት ። ዘንድሮም የሚተከሉ ችግኞች የአካባቢ ህግ በማዉጣትና የከለላ ስራ እንደሚሰራ በመጠቆም።

በዚህ በክረምት የችግኝ ተከላ ፕሮግራም የፍራፍሬ፣ለአካባቢ ውበት፣ለኮንስትራክሽን፣ለአየር ንብረት ለውጥ፣ለፈርኒቸር የሚያገለግሉና ዘርፈ ብዙ ጥቅም ያላቸው ችግኞች እንደሚተከሉ ገልጸዋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።

በመረጃ ምንጭነት ገፃችን ምርጫዎ ስላደረጉ እናመሰግናለን!
= ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!
በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub:- https://youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36CxQ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *