በጉራጌ ዞን በወልቂጤ ከተማ በርካታ ታዳሚዎች በተገኙበት የሞተር ሳይክል ሰርከስና የማርሻል አርት ትርኢት ተካሄደ።

በሞተር ሳይክል ትሪኢት ስፖርት ሀገሩን ኢትዮጵያና አፍርካን ለማስጠራት ትልቅ ፍላጎት እንዳለዉ ማስተር አብነት ከበደ አስታወቀ።

የዞኑ ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ ፣ አዉታር ኤቨንትና ከመባ ፕሮሞሽን ጋር በመተባበር በተዘጋጀዉ የሞተር ሳይክል ሰርከስ ትርኢትና የማርሻል አርት ትርኢት በርካታ ተመልካቾች ታድመዉበታል።

በጉራጌ ዞን ስፖርት መምሪያ የስፖርት ዘርፍ ሀላፊ አቶ አደም ሽኩር በእለቱ ተገኝተዉ ባደረጉት ንግግር የሞተር ሳይክል ሰርከስ በሀገራችን ብዙም ያልተለመደ እንደሆነና የማርሻል አርት ስፖርት በሀገር አቀፍ እና በክልል ደረጃ የተለመደና በስፋት እየተሰራበት ይገኛል።

በመሆኑም በዘርፉ የተሰማሩ አካላት ለወልቂጤ ከተማ ነዋሪዎች ትርኢቱን ለማሳየት የነበራቸው ፍላጎት ከፍተኛ በመሆኑ መምሪያዉ የሜዳና የተለያዩ ድጋፎች አመቻችቷል ብለዋል።

የሞተር ሳይክል ሰርከስ ትርኢት የጂምላስቲክ ስፖርት አካል ሲሆን ይህንንም ለማጠናከርና አንዱ የስፖርት አካል ለማድረግ በፕሮጀክት የተጀማመሩ ስራዎች መኖራቸዉ አስታዉሰዉ ይህም አጠናክረዉ እንደሚያስቀጥሉም አብራርተዋል።

የሞተር ሳይክል ሰርከስ ትርኢት ስፖርት በወጣቶችና በማህበረሰቡ ዘንድይበልጥ ተወዳጅ ስፖርት እንዲሆን በቀጣይ በትኩረት እንደሚሰራበት አብራርተዋል።

የሞተር ሳይክል ሰርከስ ትሪኢትና የማርሻል አርት ስፖርት በርካታ ታደሚዎች ትሪኢቱን ለማየት ስቴዲየም እንደተገኘና በዝግጅቱም ከፍተኛ ሞራል ሲሰጡም እንደነበረም ተናረዋል።

በወልቂጤ ከተማ ሁለገብ ስቴዲየም የሞተር ሳይክል የሰርከስ ትሪኢት ለታዳሚዎች ያቀረበዉ ወጣት ማስተር አብነት ከበደ እንዳለዉ ሀገራችን በተለያዩ የስፖርት አይነቶች በአለም አቀፍ ደረጃ እንደምትታወቅና የሞተር ሳይክል ሰርከስ ትርኢት እንደ ሀገራችን ያልተለመደ እንደሆነም ተናግሯል።

ወደ ዚህ ስፖርት ሲገባ በራሱ ተነሳሽነት ማንም አሰልጣኝ እንኳን ሳይቀጠርለት የጀመረዉ የሞተር ሳይክል የሰርከስ ትሪኢት አዳዲስ ፈጠራዎች በመፍጠር ዛሬ ለደረሰበት ደረጃ እንደበቃም ተናግሯል።

በሞተር ሳይክል ትሪኢት ስፖርት ሀገሩን ኢትዮጵያና አፍርካን ለማስጠራት ትልቅ ፍላጎት እንዳለዉና ወደዚህ ስፖርታዊ ስራ ከገባ ወደ አስራ አንድ አመት አካባቢ እንደሆነዉም ያስታዉሳል።

ይህ በሀገራችን ያልተለመደ ስፖርት ህብረተሰቡ ስፖርቱን ይወዳል ያለዉ ማስተር አብነት የራሱ የማህበራዊ ሚዲያ በመጠቀም የሚሰራቸዉ የተለያዩ ትሪኢቶች በዩቲዩብ ፣ በፌስ ቡክና በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያ በመልቀቅ ሰዎች እንዲያምኑት በማድረግ በደቡብ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች እየተጠራ የፈጠራ ትሪኢት እያሳየ እንደሆነም አብራርቷል።

ማህበረሰቡ የሚሰራቸዉ የተለያዩ የሞተር ሳይክል የሰርከስ ትሪኢቶች ካዩ በኋላ ሞራል፣ ምክርና የተለያዩ ድጋፎችም እያደረጉለት እንደሆነም አስረድቷል።

በራሱ ጥረትና ጥንካሬ ዛሬ ላለበት ደረጃ የደረሰዉ ማስተር አብነት ከበደ በቀላል መንገድ ስፖርቱ ሌሎች ተተኪ ወጣት ስፖርተኞች ለማፍራት እዉቀቱና ልምዱ ለማስተላለፍ ጥረት እያደረገ እንደሆነም አመላክቶ ከኦሎፒክ ኮሚቴ ጋር በአንዳንድ ጉዳዮች ላይ መነጋገሩና ይህም ቀጣይነት አግኝቶ ሌሎች ተተኪ ስፖርተኞች ለማፍራት በአካዳሚ ደረጃ ለማሰልጠንና ከሀገር ዉጭ በመወዳደር ኢትዮጵያን ለማስጠራት ትልቅ አላማ አንግቦ እየሰራ እንደሆነም አስረድቷል።

በወልቂጤ ከተማ ሁለገብ ስታዲየም በሞተር ሳይክል ሰርከስ ትሪኢት እጅግ አስደናቂና ድንቅ ብቃት ያለዉ ማስተር አብነት ከበደ የተለያዩ ትሪኢቶች በማሳየት እና በሳቦም ፉአድ የማርሻል አርት አባላቶችን ጥበብ የታከለበት ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ተመልካቾችን አዝናንቷል ሲል የዘገበዉ የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን መምሪያ ነዉ።

በመረጃ ምንጭነት ገፃችን ምርጫዎ ስላደረጉ እናመሰግናለን!

=ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!
በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *