በጉራጌ ዞን በእዣ ወረዳ በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት ከ1ሺህ 8 መቶ 45 ኩንታል በላይ ምርት ለመሰብሰብ እየተሰራ እንደሚገኝ የወረዳው አስተዳደር አስታወቀ።

በእዣ ወረዳ በአጓይተረህ ቀበሌ ወጣቶች ተደራጅተው በ13 ሄክታር መሬት ያለሙት የበጋ መስኖ ስንዴ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ተጎብኝቷል።

በጉራጌ ዞን የእዣ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ክብሩ ፈቀደ በጉብኙቱ ወቅት እንደገለፁት ከውጭ በእርዳታ የሚገባው ስንዴ በሀገር ውስጥ ለመተካትና የኑሮ ውድነቱ ለማረጋጋት በወረዳው ያሉ የውሃ፣የመሬትና የሰው ኃይል ምቹ ሁኔታዋችን በመጠቀም የበጋ ስንዴ እየለማ ይገኛል ።

በዘንድሮ አመት በወረዳው በ5 ቀበሌዎች በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት 41 ሄክታር መሬት እየለማ እንደሚገኝ የገለፁት አቶ ክብሩ ፈቀደ ከ1ሺህ 8 መቶ 45 ኩንታል በላይ ምርት ለመሰብሰብ ርብርብ እየተደረገ መሆኑንም ጠቁመዋል።

በዛሬው እለትም በአጓይተረህ ቀበሌ በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የታየው ውጤታማነት በቀጣይ በሌሎችም ቀበሌዎች ለማስፋት እንደሚሰራ አመላክተዋል። ለዚህም አመራሩ፣ ባለሙያዎችና አርሶ አደሮች ተቀናጅተው መስራት ይኖርባቸዋል ብለዋል።

የወረዳው መንግስትና ባለሙያዎች በበጀት፣ ቴክኖሎጂ በማቅረብ፣ ወጣቶችን በማደራጀትና አስፈላጊውን ድጋፍ በማድረግ እገዛ እንዳደረገላቸውም አስረድተዋል።

የእዣ ወረዳ ግብርና ፅህፈት ቤት ኃላፊና የወረዳው ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ዘውዱ ዱላ በበኩላቸው የጉብኝቱ አላማ በአጓይተረህ ቀበሌ የለማው የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት በማየት አርሶ አደሮቹ ተነሳሽነት እንዲፈጥርላቸውና በቀጣይ በየቀበሌያቸው ወስደው እንዲተገብሩ ያለመ ነው ብለዋል።

ይህም ለወጣቱ የስራ እድል ከመፍጠር በተጨማሪ ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ የኢኮኖሚ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ትልቅ እድል እንደሚፈጥርም ጠቁመዋል።

በዘንድሮው የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የተገኘው ምርጥ ተሞክሮ ለማስፋትና የታዩ ክፍተቶችን በቀጣይ ለማረም ያስችላል ያሉት ኃላፊው አቶ ዘውዱ የግብርናው ክፍለ ኢኮኖሚ በማዘመን የአርሶ አደሩ ውጤታማነት ለማሳደግ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ለዘርፉ ልዩ ትኩረት እንዲሰጡትም ጠይቀዋል።

አቶ ዚያዱ ዲኖ የአጓይተረህ ቀበሌ የግብርና ባለሙያ እንዳሉት ለወጣት አርሶ አደሮቹ ከማሳ ዝግጅት ጀምሮ አስፈላጊውን ሙያዊ ድጋፍ እያደረጉላቸው እንደሆነ ተናግረዋል።

አርሶ አደር ኮርማ ይርጋ የቆጠር ቀበሌ ነዋሪና የጉብኝቱ ተሳታፊ ሲሆኑ በአይጓተረህ ቀበሌ የበጋ መስኖ የለማው ስንዴ ያዩትን ምርጥ ተሞክሮ በቀጣይ በቀበሌያቸው ወስደው ለመስራት መነሳሳትና ቁጭት እንደፈጠረባቸውም ተናግረዋል።

የበጋ መስኖ ስንዴ በ13 ሄክታር መሬት ላይ እያለሙ ከሚገኙ ወጣት አርሶ አደሮች መካከል አቶ ብላቱ በረካ፣ አቶ እንዳለ በረዳ በጋራ በሰጡት አስተያየት አርሶ አደሩ በበጋ መስኖ ስንዴ ራሳቸውን በምግብ ከመቻል በተጨማሪ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚ እንዲሆኑ እንደሚያስችላቸው ገልፀዋል። ከዚህም 5 መቶ 85 ኩንታል ስንዴ እንደሚጠብቁ ተናግረዋል።

የጠቅላይ ሚኒስተሩ ጥሪ ተከትሎ ከውጭ በእርዳታ የሚገባው ስንዴ ለማስቀረትና የኑሮ ውድነት ለመቀነስ የበኩላቸውን ርብርብ እያደረጉ እንደሚገኙ ጠቁመው የተጀመረው የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት በዘንድሮ አመት የታየው ድክመት በመቅረፍ በቀጣይ በማስፋት እንደሚሰሩም ገልፀዋል።

የበጋ መስኖ ስንዴ ውጤታማነት የወረዳው አስተዳደር፣ የሚመለከታቸው አካላትና የባለሙያዎቹ ድጋፍ ትልቅ እንደነበር ጠቁመዋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።

= ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!
በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡

Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36C

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *