በጉራጌ ዞን በእኖር ወረዳ የመስኖ ልማትና የበልግ እርሻ ተጠናክሮ በመቀጠል ላይ ይገኛል።

በወረዳው በአትክልት ብቻ 756 ሄ/ር መሬት በመስኖ ማልማት እንደተቻለ የወረዳው ግብርና ጽ/ቤት ገልጿል።

የጽ/ቤቱ ሐላፊ አቶ አብድልመጅድ ጀማል በመስኖ ልማትና በበልግ እርሻ ሂደት ዙሪያ የመስክ ምልከታ ባደረጉበት ወቅት እንደተናገሩት በወረዳው በ1ኛው ዙር በአትክልት ብቻ 784 ሄ/ር መሬት በመስኖ ለማልማት ታቅዶ እስካሁን 756ሄ/ር መሬት ማልማት እንደተቻለ ገልጿል።

በአፈጻጸሙ ላይ በቀጣይ ለተሞክሮ የሚወሰድ አበረታች ውጤት የተገኘበት እንደሆነም ጠቁሟል።

የወረዳው መንግስት ለተግባሩ በሰጠው ልዩ ትኩረት አመራሩ ከአርሶ አደሩና ከባለሙያው ጎን ሳይለይ ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ላይ እንደሚገኝም ጠቅሰዋል።156 ሄ/ር መሬት በበጋ መስኖ ስንዴ በመልማት ላይ እንደሚገኝም ሐላፊው አክለው ገልጿል።

በአሁኑ ወቅት በስራው ላይ የተሰማሩ አርሶ አደሮች ማሳቸውን በመንከባከብና ከመሥኖ ትሩፋቱ ለአካባቢ ገበያ በተመጣጣኝ ዋጋ በማቅረብ የኑሮ ውድነቱን በማረጋጋት ላይ እንደሚገኙም አቶ አብድልመጅድ ተናግሯል።የወረዳው መ/ኮ/ጉ/ጽ/ቤትም በማሳቸው ላይ አግኝቶ ያነጋገራቸው አ/አደሮች ይህንኑ አስተያየት ነው የሰጡት።

የሚመለከታቸው ባለድርሻ ተቋማትም ከወረዳው ግብርና ጽ/ቤት ጋር ተቀናጅተው የገበያ ትስስር በመፍጠር ሐላፊነታቸውን እየተወጡ ይገኛሉ ብለዋል።

በወረዳው በ5ሺ ሄ/ር መሬት ላይ በቆሎና ድንች የመሳሰሉት የበልግ ሰብሎችን ለማልማት ታቅዶ የእርሻ ስራው ተጠናክሮ መቀጠሉን አቶ አብድልመጅድ ገልጿል።ዘገባው የወረዳው መ/ኮ/ጉ/ጽ/ቤት ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *