በጉራጌ ዞን በእኖር ወረዳ ቤት ንብረታቸው በእሳት ቃጠሎ ለወደመባቸው የህብረተሰቡ ክፍሎች በበጎ ፈቃደኞች ከ184 ሺ ብር በላይ የቤት መስሪያ እና የአልባሳት ድጋፍ ተደረገ።

ነሐሴ 11/2014 ዓ.ም

በጉራጌ ዞን በእኖር ወረዳ ቤት ንብረታቸው በእሳት ቃጠሎ ለወደመባቸው የህብረተሰቡ ክፍሎች በበጎ ፈቃደኞች ከ184 ሺ ብር በላይ የቤት መስሪያ እና የአልባሳት ድጋፍ ተደረገ።

ድጋፉ የተገኘው በአርቲስት ነስሩ ሙክታር አስተባባሪነት በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር ከሚኖሩ መልካም በጎ ፈቃደኞች አማካኝነት ነው፡፡

የተደረገው ድጋፍም በጥሬ ገንዘብ 184 ሺ 437ብር እና የተለያዩ አልባሳት ያካተተ ሲሆን ይህም 11 ለሚሆኑ ቤት ንብረታቸው በእሳት አደጋ ለወደመባቸው ግለሰቦች ተከፋፍሏል፡፡

በድጋፍ መርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ያዕቆብ ግርማ ጉዳት ለደረሰባቸው የህብረተሰቡ ክፍሎች በበጎ ፈቃደኞች በኩል ለተደረገው የገንዘብና የአልባሳት ድጋፍ ከፍተኛ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

እንደ ዋና አስተዳዳሪው ገለጻ የማህበረሰቡ የቆየ የመረዳዳት እሴቶች አጠናክሮ በማስቀጠል ለተቸገሩ ወገኖች መርዳት እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡

ድጋፍ የተደረገላቸው ወገኖች ያገኙትን ገንዘብ ያለብክነት ለቤት መስሪያነት እንዲያውሉትም አስተዳዳሪው አስገንዝበዋል፡፡

ካነጋገርናቸው ግለሰቦች መካከል አንዳንዶቹ በሰጡት አስተያየት በተደረገለቸው የገንዘብና የአልባሳት ድጋፍ መነሻ በማድረግ ኑሮዋቸዉን የሚያቋቁሙ መሆኑን ጠቁመው ለበጎ ፈቃደኞቹ ልባዊ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

በዚህ መልካም ተግባር ላይ የወረዳው የመንግስ ረዳት ተጠሪ አቶ ሽኩረታ አ/ከሪም እና የወጣቶችና ስፓርት ጽ/ቤት ሐላፊ አቶ ቸሩ ተካ ጨምሮ የበጎ ፈቃድ ኮሚቴው አስተባባሪ አባላት(አርቲስት ነስሩ ሙክታር፣አቶ ከሊፋ ዑስማን፣ፀጋዬ ተክሌ፣ ሙሌ፣ መቅደስ አስራት፣ፀሐይ ብዛኒ እና ወርቃለም አረጋ) ተገኝቷል ሲል የወረዳው የመ/ኮ/ጉ/ጽ/ቤት ዘግቧል፡፡

እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub:- https://youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36CxQ
Twitter:- https://4pvf.short.gy/bTJNNn

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *