በጉራጌ ዞን በኢንቨስትመንትና በተቀናጀ የግብርና ልማት እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን አበረታች መሆናቸውን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እንዳሻው ጣሰው ገለጹ።


በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር በአቶ እንዳሻው ጣሰው የተመራው የክልሉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችና የዞኑ አመራሮች በጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ በኢንቨስትመንት ዘርፍና በቸሃ ወረዳ በተቀናጀ የግብርና ልማት እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን የመስክ ምልከታ አድርገዋል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እንዳሻው ጣሰው በጉራጌ ዞን ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት እንዳሉት በዞኑ በኢንዱስትሪና በተቀናጀ የግብርና ልማት እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን አበረታች መሆናቸውን ተናግረዋል።

በመስክ ምልከታው በእዣ ወረዳ የፍቅር ውሃ ፋብሪካ፣ የቲናው አበባ ልማት እንዲሁም በቸሃ ወረዳ በወጣቶች እየለማ ያለው የተቀናጀ የግብርና ልማት ስራ፣ የቹፑድ ፋብሪካን መገብኘታቸውን ተመልክቷል።

እንደ ርዕሰ መስተዳድሩ መግለጫ መንግስት በዘርፉ የሚታዩ ችግሮችን ለመፍታት አስፈላጊውን እገዛ እንደሚያደርግላቸው ተናግረዋል።

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የገጠር ክላስተር አስተባባሪና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ኡስማን ሱሩር በክልሉ እየተከናወኑ ያሉ የተቀናጀ የግብርና ልማት ስራዎች ውጤታማ መሆናቸው ገልጸዋል።

የተቀናጀ የግብርና ልማት ስራዎች የአርሶ አደሩን የምግብ ዋስትናና የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ከማረጋገጡ ባለፈ ለወጣቶች የስራ ዕድል ፈጥሯል።

ይህም እንደ አብነት ያነሱት በጉራጌ ዞን ቸሃ ወረዳ ወጣቶች ተደራጅተው በ30 ሄክታር መሬት የአትክልትና የበጋ መስኖ ስንዴ እየሰሩት ያለው ስራ አድንቀዋል።

ወጣቶቹ በዘርፉ የኢኮኖሚ ተጠቃሚ መሆናቸውና ከ1መቶ በላይ ዜጎች የስራ ዕድል ከመፍጠራቸውም በተጨማሪ በቀጣይ ወደ ሌላ ኢንቨስትመንት እንዲያመሩ እያደረጋቸው ይገኛል ብለዋል።

በክልሉ አትክልቶችና ፍራፍሬዎች በስፋት በማምረት ወደ ገበያ በማቅረብ የአትክልትና ፍራፍሬ የዋጋ ንረቱ ዝቅ እንዲል እንዳደረገውም ገልጸዋል።

በዞኑ እዣ ወረዳ የቲናው አበባ ልማት ስራ አስኪያጅ አቶ ሙሉቀን ለማ እንዳሉት ቲናው አበባ ልማት በጠቅላላ 47 ሄክታር ስፋት ያለው ሲሆን ከዚህም 32 ሄክታር መሬት መልማቱን ተናግረዋል።

በአመት ውስጥ ከ30ሚሊዮን ስቲም ኤክስፖርት የሚያደረግ ሲሆን በባለፈው አመት 7ነጥብ 5 ሚሊዮን ዩሮ አመታዊ ገቢው እንደነበር አንስተው በዚህ አመት 8ሚሊዮን ዩሮ ለማግኘት እየሰሩ እንደሚገኙ አመላክተዋል።

በአበባ ልማቱ ለ8መቶ ወጣቶች የስራ እድል መፍጠሩን ገልጸው ምርቱም ለአውሮፖ፣ ለሚድል ኢስትና ደቡብ ኮሪያ ያቀርባል ብለዋል።

በአካባቢው በርካታ የልማት ስራዎች የሚሰሩ ሲሆን ከ3ሺህ በላይ አባወዎች የጉድጓድ ውሃ ከማስጠቀም ባለፈ በመንገድ፣ በትምህርት እገዛ እያደረጉ እንደሚገኙ ጠቅሰዋል።

ፋብሪካው በቀጣይ 54 ሄክታር መሬት በማልማት ለተጨማሪ 1ሺህ 2 መቶ ዜጎችን የስራ ዕድል በመፍጠር ከ10 ሚሊዮን ዶላር ገቢ እንዲያገኙ እንደሚሰሩና እያደረጉት ያለው የማህበራዊ ልማት ስራዎችን በቀጣይም አጠናክረው እንደሚሰሩ ተናግረዋል።

በመንግስት እየተደረገላቸው ያለው ድጋፍ አመስግነው በቀጣይ የበለጠ ለመስራት የመብራት መቆራረጥ ማነቆ እንደሆነባቸው ጠቁመዋል።

ወጣት አቶ ዳንኤል ሺፈታ እንዳሉት በቸሃ ወረዳ ያሚኒ የመስኖ ቡድን 5 ወጣቶች በ1ሄክታር መሬት በበጋ መስኖ ስንዴ፣ በመደበኛ መስኖ ስንዴ የጀመሩት ስራ አሁን ላይ 30 ሄክታር መሬት እያለሙ መሆኑና በዚህም ለ2 መቶ ዜጎች በቋሚና በጊዜያዊነት የስራ ዕድል ከመፍጠር ባለፈ በ28 ሺህ መነሻ ካፒታል የጀመሩት ስራ አሁን ላይ 6 ሚሊዮን ብር ማደጉንም ገልጸዋል።

ወጣቶቹ የሚያለሙት ቲማቲም፣ ዝኩኒ፣ ቃሪያ፣ ኪያር፣ ጎመኖችና ሌሎችም አትክልቶች በስፋት በማልማት ለገበያ እያቀረቡ እንደሚገኙ ጠቅሰው አሁን ላይ ወደ ኢንቨስትመንት ዘርፍ እየተሸጋገሩ እንደሚገኙ ጠቅሰዋል።

ወረዳው እያደረገላቸው ያለው ድጋፍ አመስግነው ያመረቱት ምርት ወደ ገበያ በማውጣት ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ተናግረዋል።

ሌላኛው የተጎበኘው ቹፑድ ፋብሪካ ሲሆን ፋብሪካው ለዜጎች የስራ ዕድል ከመፍጠሩም ባለፈ ምርቶችን በማምረት ለገበያ በማቅረብ አበረታች ስራዎችን እየሰራ ሲሆን የበለጠ ለመስራት የመብራት መቆራረጥ ችግር ማነቆ እንደሆነባቸው በጉብኝቱ ወቅት አመላክተዋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *