በጉራጌ ዞን በአበሽጌ ወረዳ ስልጠናቸውን ያጠናቀቁ ከ 6 መቶ በላይ ምልምል ህዝባዊ ሰራዊት አባላት በዛሬው እለት ተመረቁ ፡፡

ምልምል ህዝባዊ ሰራዊቱ የአካባቢያቸው ሰላም ከማስጠበቅ ባለፈ ለሀገሪቱ ደጀን በመሆናቸው አደረጃጀቶችን አጠናከረው በልማት ስራው ጭምር በንቃት እንደሚሳተፉ ተናግረዋል፡፡

የምርቃት ዝግጅቱ ላይ ተገኙት የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳደሪ አቶ መሀመድ ጀማል እንዳሉት ሀገራችን በታሪኳም ብዙ ጠላቶች የፈተኗት ሀገር መሆኑዋን ገልጸው እነዚህ ጠላቶቹዋ በሚነሱባት ጊዜ መሪዎቹዋ ክተት በማወጅና ሀገር ችግር ውስጥ እንዳለች በመግለጽ ህዝቡ እንዲከተላቸው ጥሪ ያቅርቡ ነበር ብለዋል።

ህዝቡም ጥሪ ሲቀርብለት ሁሉም ያለውን ጥሎ ሀገር ለማዳን የሚወጣ ህዝብ ስለነበር ኢትዮጵያን ለማፍረስ ያለሙ እና ለማፍረስ የተነሱ ሁሉ መንካት አለመቻላቸውን ገልጸዋል፡፡

በተጨማሪም ሀገራችን አባቶቻችን መስዋአትነት የከፈሉባት ሀገር መሆኑዋንና የብሔር ብሔረሰብቦች ሀገር ስለሆነች ክቡር ጠቅላይ ሚንስተራችን የመደመር መርህ በማምጣት ህዝባችንን አንድ ማድረግ ምቾት ያልሰጣቸው ሀይላት እየወጉዋት እንደሆነም ገልጸው፤ጠቅላይ ሚንስተሩ እኛ እያለን ሀገር አትፈርስም በማልት ወደ ግንባር መዝመታቸውንም አብራርተዋል፡፡

አክለውም ይህ ምልምል ህዝባዊ ሰራዊት ከአካባቢው አልፎ ለሀገሩ ደጀንና አለኝታ እንዲሆንና ለሰላም ዘብ እንዲቆም መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

የጉራጌ ዞን ሰላምን ጸጥታ መምሪያ ሀላፊ አቶ መስፍን ተካ እንደገለጹት ለተከታታይ ሳምንታት ጸሀይና ብርድ ሳይበግራቸው ከሁሉም በላይ ሀገር ይበልጣል በማለት ክቡር ጠቅላይ ሚንስተር ዶ/ር አብይ አህመድ ግንባር እንገናኝ የሚለውን መልእክት ተቀብለው አከባቢያቸውን ከሰረጎ ገቦች ለመጠበቅ መሰልጠናቸዉን አስረድተዋል።

አክለውም ጠቅላይ ሚንስተሩ ሰራዊቱን በግንባር በመምራትና በማገዝ ድል እያደረጉ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

ጦርነት ግንባር ላይ ብቻ አይደለም ያሉት የአበሽጌ ወረዳ ዋና አስተዳደሪ አቶ መላኩ ብረሀኔ የኔ ድርሻ የትኛው ነው በማለት ሁሉም በልማቱም ዘርፍ ፣ለሰራዊቱ ሀብት በማሰባሰብ፣የደረሱ ሰብሎችን በመሰብስብ ለሰራዊቱ ደጀንነቱን ማሳየት አለበት ብለዋል።

በተጨማሪም ስልጠናው ዛሬ ብቻ የሚያበቃ አለመሆኑን ገልጸው ሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች በየደረጃው በመሰልጠን አከባቢያቸውን መጠበቅ እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡

የአበሽጌ ወረዳ ሰላምና ጸጥታ ጽ/ቤት ኃላፊ መቶ አለቃ ጸጋዬ አምዲሳ እንዳሉት ከ6 መቶ በለይ ምልምል ህዝባዊ ሰራዊቱ የሰለጠነው ስልጠና የአካል ብቃት፣መሳሪያ መፍታትና መግጠም፣አከባቢን መጠበቅ ስልት የሚያስችል ስልጠና መውሰዳቸውን አስረድተዋል፡፡

አያይዘውም የተደራጀው አደረጃጀት እንደ ወረዳ 1 ሻለቃ፣ 4ሻንበል በ16 ጋንታና በ48 ቲም መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

ያነጋገርናቸው ምልምል ህዝባዊ ሰራዊት ሰልጣኞች ወንድሙ ታደሰ እና ዘሪሁን ደረሰ ሁለቱም በሰጡት አስተያየት ማንም ሳይቀሰቅሳቸው አከባቢያቸውን ብሎም ሀገርን ለመጠበቅ መሰልጠናቸውን አብራርተዋል።

በተጨማሪም ከአካባቢያቸው ሰላም ከማስጠበቅ ባለፈ ለሀገሪቱ ደጀን በመሆናቸው አደረጃጀቶችን አጠናከረው በልማት ስራው ጭምር በንቃት እንደሚሳተፉ ተናግረዋል፡፡

በምርቃት ስነስርአት ላይ የዞኑ ዋና አሰተዳዳሪ አቶ መሀመድ ጀማል ጨምሮ የዞንና የወረዳ ከፍተኛ አመራሮች፣ የቀበሌ የስራ ሀላፊዎች፣የአካባቢው ነዋሪዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው፡፡

  • አካባቢህን ጠብቅ!
  • ወደ ግንባር ዝመት!
  • መከላከያን ደግፍ!

በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36Cx

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *