በጉራጌ ዞን በቀቤና ወረዳ በሌንጫ ቀበሌ በፈረጀቴ ጎጥ ውስጥ በእሳት አደጋ ቤት ንብረታቸው ለወደመባቸው 42 አባወራዎች ከዞኑ ማህብረሰብ የተሰበሰቡ ቁሳቁሶች የጉራጌ ዞን ሴቶችና ህጻናት መምሪያ ከጉራጌ ዞን አስተዳዳር ጋር በመሆን አስረከበ።

የጉራጌ ዞን ሴቶችና ህጻናት ጉዳይ መምሪያ ኃላፊ ወይዘሮ መሰረት አመርጋ የደረሰው ጉዳት እጅግ አሳዛኝና ልብ የሚሰብር አደጋ ሲሆን በአደጋው ለብዙ አመታት ለፍተው በከፍተኛ በጀት የገነቡት ቤትና በዙሪያው የሚገኙ ሰብሎችም ጭምር መውደማቸውን ተናግረዋል።

አክለውም በእሳት ቃጠሎው 42 ቤቶች ሙሉ ለሙሉ እንደወደሙና በተጨማሪም የመንደሩ አርሶ አደሮች አመት ለፍተው ያከማቹት ብዛት ያለው እህል፣ የቤት ውስጥ ቁሳቁስ፣ አልባሳት፣ የጓሮ አትክልትና ሰብሎች ሙሉ በሙሉ ሲወድሙ፣ በእሳቱ ጉዳት የደረሰባቸው የተወሰኑ ሰዎች እንዳሉና ቤት ውስጥ ታስረው የነበሩ ከብቶች ላይም ጉዳት መድረሱንም ገልፀዋል።

በእሳት አደጋ ቤት ንብረታቸው ለወደመባቸው ዜጎች የዞኑ ሴቶችና ህፃናት መምሪያ ከዞኑ አስተዳደር ጋራ በጋራ በመሆን ከ 1መቶ ሺህ ብር በላይ የሚገመት የአልባሳት፣ የቤት ውስጥ ቁሳቁስና የስንዴ ቅንጬ፣የምግብ ዘይትና የፍርኖ ዱቄት ድጋፍ ማድረጋቸውን ገልፀው የተበረከተላቸው ድጋፍ ችግሮቻቸውን በዘላቂነት ባይቀርፍም የዞኑ መንግስትናገመምሪያው ከጎናቸው እንደሆነና እንኳን ህይወታችሁን አተረፋቹ ለማለት እንደሆነም ተናግረዋል ።

አያይዘውም ጉዳት የደረሰባቸው ወገኖች በዘላቂነት ለማቋቋም ትልቅ ስራ የሚጠይቅ በመሆኑ መንግስት፣ማህበረሰቡና ሌሎችም በጋራ በመሆን ድጋፍ ሊያደርጉላቸው ይገባል ብለዋል።

በተጨማሪም አንድም እቃ ሳያወጡ ንብረታቸው እንደ ወደመና የመንግሥት ተቋምና ማህበረሰቡ ማንኛውንም ድጋፍ ትንሽ ትልቅ ሳይል ማድረግ እንዳለበት ገልጸዋል።

በዞኑ በተለያዩ አከባቢዎች በተመሳሳይ ወቅት ብዙ ንብረቶች እንደወደመ ጠቁመው ሁሉም ማህበረሰብ ለእሳት አደጋው መንስኤ የሚሆኑ ነገሮችን ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባ አሳስበዋል።

አቶ ተማም ሀጂ አህመድና አቶ አባዚድ ጀማል ከተጎጅዎች መካከል የድጋፍ አሰባሰብ ጊዜያዊ አስተባባሪ ሲሆኑ እስካሁን የተወሰነ የቤት ውስጥ ቀሳቁስ፣ የመጠለያ ድንኳንና ሸራ፣ለዕለት ለምግብነት የሚውሉ ድጋፍ እንደተደረገላቸውም ገልጸዋል።

አክለውም ለተደረገላቸው ድጋፍ አመስግነው በዘላቂነት መንግስትና ማህበረሰቡ ድጋፍ እንዲያደርግላቸው ጠይቀዋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።

= ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!
በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:-
https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36Cx!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *