በጉራጌ ዞን በሞህር አክሊል ወረዳ በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን አስተባባሪነት በወርልድ ዶክተርስ ድጋፍ የተገነባው የኮተ ቀበሌ ንጹህ የመጠጥ ውሃ ተመርቆ አገልግሎት መስጠት ጀመረ ።

የካቲት17/2014 ዓ.ም

በጉራጌ ዞን በሞህር አክሊል ወረዳ በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን አስተባባሪነት በወርልድ ዶክተርስ ድጋፍ የተገነባው የኮተ ቀበሌ ንጹህ የመጠጥ ውሃ ተመርቆ አገልግሎት መስጠት ጀመረ ።

በጉራጌ ዞን ከሚገኙ ከፍተኛ የውሃ እጥረት ካለባቸው ወረዳዎች አንዱ የሞህር አክሊል ወረዳ ነው።

ዛሬ ተመርቆ አገልግሎት መስጠት የጀመረው የኮተ ንጹህ የመጠጥ ውህ የአካባቢው የውሃ እጥረት በከፍተኛ ሁኔታ ይቀርፋል ተብሏል።

በተያያዘም የወረዳው የንጹህ መጠጥ የውሃ እጥረት እንደሚቀርፉ የሚጠበቁ በሁለት አካባቢዎች በመቆርቆር ቀበሌ በጉራጌ ዞን አስተዳደር የበጀት ድጋፍ እንዲሁም በፉርቸ ቀበሌ በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን በእንድብር ሀገረ ስብከት አስተባባሪነት በወርልድ ዶክተርስ የበጀት ድጋፍ የሚገነባ የግንባታ የመሰረት ድንጋይ በዞኑ ዋና አስተዳዳሪ በአቶ መሀመድ ጀማል ተቀምጧል።

በምረቃ ፕሮግራሙ የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ መሀመድ ጀማል ጨምሮ የዞኑ ከፍተኛ አመራሮች፣የዞኑ የውሃ ማዕድንና ኤነርጂ መምሪያ ባለሙያዎች፣ የሞህር አክሊል ወረዳ አመራሮች፣የሀይማኖት አባቶች፣የሀገር ሽማግሌዎችና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል።

ተጨማሪ መረጃዎች ይኖሩናል እናደርሶታለን ይከታተሉን!

በመረጃ ምንጭነት ገጻችን ምርጫዎ ስላደረጉ እናመሰግናለን!!
= ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!
በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:-
https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36Cx!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *