በጉራጌ ዞን በሚገኙ ት/ቤቶች በሙሉ የ2014 ትምህርት መስጠት መጀመራቸውን የጉራጌ ዞን ትምህርት መምሪያ አስታወቀ፡፡

በዞኑ የሚገኙ የመንግስት ት/ቤቶች ከ419 ሺ በላይ ተማሪዎችን ተቀብለው የመማር ማስተማር ስራቸውን በትናንትናው እለት መጀመራቸው ትምህርት መምሪያው ገልፀዋል፡፡

መማሪያው ለመላው የትምህርት ቤት ማህበረሰብ እና ተማሪዎች እንኳን ለ2014 የትምህርት ዘመን በሰላም አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፏል፡፡
የጉራጌ ዞን ትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ተሸመ ንዳ ዛሬ በሰጡት መግለጫ በዞን ደረጃ የ2014 የትምህርት ልማት ስራው እንዲጀመር እና ውጤታማ ለማድረግ ከመላው ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆኑ የንቅናቄ ስራ ተሰርቶ ወደ ተግባር መገባቱን ተናግረዋል፡፡
ለትምህርት የደረሱ ተማሪዎች ሁሉ እንዲመዘገቡ በተደረገው ርብርብ በቅድመ መደበኛ 84 ሺ 714 ተማሪዎች ለማስመዝገብ ታቅዶ 63 ሺ 8 መቶ 88 ተማሪዎችን ፣በ1ኛ ደረጃ 3 መቶ 33 ሺ 524 ለማስመዘገብ ታቅዶ 2 መቶ 54 ሺ 132 ተማሪዎችን፣ በ2ኛ ደረጃ ደግሞ 86 ሺ 3 መቶ 63 ታቅዶ 43 ሺ 2 መቶ 18 ተማሪዎችን በጥቅሉ 4 መቶ 19 ሺ 8 መቶ 87 ተማሪዎችን መመዝገባቸውና በትምህርት ገበታቸው ላይ ከጥቅምት 1 ጀምሮ ተገኝተው የመማር ማስተማሩ ስራ መጀመራቸው ተናግረዋል፡፡
በዞኑ ልዩ የትምህርት ፍላጎት ያላቸው ተማሪዎች 10 ሺህ 16 ለመቀበል ታቅዶ 4 ሺ 7 መቶ 52 ተማራዎች መመዝገባቸውን ተናግረዋል፡፡
በቅድመ ዝግጅት ስራው በተለይም በክረምት በጎ ፍቃድ በትምህርት ሴክተር ብቻ ከ7 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር የሚገመት ድጋፍ መደረጉን ያስታወሱት አቶ ተሾመ ንዳ የ4 የአረጋዊያን ቤት ጥገና፣ 2 መቶ 71 ዩኒት ደም ልገሳ፣ 14 ሺ 5 መቶ 17 ደርዘን ደብተር በርካታ እስክብርቶ አቅም ሌሌላቸው ተማሪዎች ድጋፍ መደረጉ፣ ከ1 ነጥብ 3 ሚሊዮን በላይ ችግኞች መተከላቸውን ከ1 ሺ 6 መቶ 20 በላይ አልባሳት እንዲሁም የማጠናከሪያ ትምህርት መሰጠቱን አስታውቀዋል፡፡
በህብረተሰቡ ተሳትፎ በተገኘ ከ67 ሚሊዮን 2 መቶ 66 ሺ 6 መቶ 71 ብር በማሰባሰብ ከ4 መቶ 41 በላይ የመማሪያ ክፍሎች መሰራታቸውን፣ ከ6 መቶ 24 በላይ ክፍሎች ደግመ ጥገና እንደተደረገላቸው ተናግረዋል፡፡
በተያያዘም ከ30 ሺ 24 በላይ ወንበሮች መጠገናቸውንና ከ2 መቶ 73 በላይ ሰሌዳዎች ተገዝተው ለት/ቤቶች ተደራሽ መደረጋቸው አሳውቀዋል፡፡
በተማሪዎች አቀባበል በተለይም በ2ኛ ደረጃ ውስንነት መኖሩን የገለፁት ኃላፊው መላው ህብረተሰብ ለትምህርት የደረሱ ልጆች ወደ ት/ቤት በመላክ የበኩሉን እገዛ ማድረግ እንዳለበት ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፡፡
የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ዳግም ያገረሸበት ወቅት ላይ በመሆኑ ተማሪዎች እና መምህራኖች ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለባቸው ያሳሰቡት የመምሪያው ኃላፊ ወላጆች ማስክ ገዝተው ለተማሪዎች በመስጠት ትብብር እንዲያደርጉ ጠይቀዋል፡፡ አቅም የሌላቸውን ደግሞ ተለይቶ ት/ቤቶች ማቅረብ እንዳለባቸው ተናግረዋል፡፡
በአንድ ወንበር 2 ተማሪዎች በ1 ክፍል 40 ተማሪዎች ብቻ መሆን እንዳለበትም አሳስበዋል፡፡
በ2013 የትምህርት ዘመን የ8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና የተሻለ ያሳለፉ ቀቤና፣99.3%፣ገ/ጉ/ወ/ወ/99.2%፣ቡኢ 97.8%፣ደ/ሶዶ 97.4%፣ሶዶ 92%፣እኖር 90.2%፣መስቃን 87.6%፣ቡታጅራ 85%፣ወልቂጤ 78.4%፣ም/መስቃን 71.2%፣አበሽጌ 70.6%፣ እኖሞር 69.2%፣ ማረቆ 68.6%፣ እንደጋኝ 67.8% እንደሆነ ያብራሩት አቶ ተሾመ ንዳ ጥቅምት 1/2014 ዓ.ም ትምህርት የጀመሩ በ1ኛ ደረጃ ት/ቤቶች 5 መቶ 97 እና በ2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች ደግሞ 87 መሆናቸው ገልፀዋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።

በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36Cx

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *