የግጭት በር ተዘግቶ የሰላም በር ተከፈተ።
በወረዳዎቹ የተነፋፈቁ ቤተሰቦች በቤሄረሰቦቹ ባህልና ወግ መሰረት እርቅ በመፈፀም ዛሬ አዲስ ቀናቸው እያከበሩ ነው።
ሶስት አመታት ያስቆጠረው የሁለቱ ወረዳዎች ማህበረሰብ የሰላም እጦትና ግጭት በጉራጌና በማረቆ ብሄረሰቦች ባህል መሰረት ወደ ቀድሞው አንድነታቸው ለመመለስ በጉዳ/ በጉርዳ ተሳስረው እርቁን ፈጽመዋል።
እለቱ እነዚህ የሁለቱ ወረዳ ህዝቦች መለያየት የማይችሉ በጋብቻ፣በሀይማኖት፣በባህልና ወግ የተጋመዱ መበጠስ የማይችል ትስስር ያላቸው ህዝቦች መሆናቸው በተግባር የተያበት እና የብሄረሰቦቹ የግጭት አፈታት ባህል ጎልቶ የታየበት ነው።
በዚህ የእርቅ ስነስርዓት የተለያዩ ባህላዊ ክዋኔዎች በመካሄድ ላይ ናቸው።
ለዚህ እርቅ ስነስርዓቱ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የወጣቶች፣ የክልሉ፣የዞኑና የወረዳዎቹ አመራሮች ሚና ከፍተኛ እንደነበረ በስፍራው ያነጋገርናቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ገልፀዋል።
= ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!
በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36Cx