ከማረቆ ወረዳ ተፈናቅለው የቆዩ ነዎሪዎች ዛሬ ወደ ማረቆ ቆሼ ከተማ ሲገቡ በርካታ አመራሮችና የህብረሰብ ክፍሎች ተገኝተው ደማቅ አቀባበል ያደረጉላቸው ሲሆን በተመሳሳይ ሁኔታ ከመስቃን ወረዳ ተፈናቅለው የቆዩ ነዋሪዎች ወደ እንሴኖ ከተማ ሲገቡ ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
በቀጣይም የአካባቢው ሰላም የማረጋገጥና ቀሪ የተፈናቀሉ ወገኖች ወደ ቄያቸው በመመለስ ወደ ልማት የማስገባት ስራ ተጠናክሮ የሚቀጥል ሲሆን ለስራው መሳካት የአካባቢው ማህበረሰብ፣ የፀጥታ አካላትና በየደረጃው ያለው አመራሩ ተቀናጅተው መስራት ይጠበቅባቸዋል ተብለዋል።
በሁለቱ ማህበረሰቦች መካከል የተፈጠረውን አለመግባባት ለመቅረፍ የሀገር ሽማግሌዎችና ሌሎችም የሚመለከታቸው አካላት በማወያየት የእርቅ ስነስርዓት ለማከናወን ጥረቶች ሲደረጉ መቆየቱ ይታወቃል።
በዛሬው የሽኝትና አቀባበል ሲደረግ የደቡብ ክልል፣ የዞን፣ የወረዳ፣ የከተማ አመራሮች፣የወረዳዎቹና ከተማ ነዋሪዎች፣ወጣቶች፣የፀጥታ አካላትና ሌሎችም እንግዶች ተገኝተዋል።
ፎቶ ከምስራቅ መስቃን እና ማረቆ ወረዳዎች የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት የተገኘ ነው።
= አካባቢህን ጠብቅ!
= ወደ ግንባር ዝመት!
= መከላከያን ደግፍ!
በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36Cx