በጉራጌ ዞን “በህብረት ችለናል” በሚል መሪ ቃል የታላቁ ህዳሴ ግድብ መሰረት ድንጋይ የተጣለበትን 13ኛ አመት በተለያዩ ዝግጅቶች በወልቂጤ ከተማ በድምቀት እየተከበረ ይገኛል።

የጉራጌ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና የግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ አበራ ወንድሙ በበኩላቸው ትላልቅ ፕሮጀክቶች በራሳችን ጀምረን በራሳችን መጨረስ ለአለም ህዝቦች ማሳየታችን የህዳሴ ግድብ አንዱ ማሳያ ነው ብለዋል።

በዚህም አሻራ የዞኑ ህዝቦች ከጅምሩ ጀምረው አሁን እስካለበት ድረስ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ሲያበረከቱ የቆዩ ሲሆን ድጋፉ በቀጣይም አጠናክረው እንደሚያስቀጥሉ አስገንዝበዋል።

የጉራጌ ዞን የዋና አስተዳዳሪ ልዩ አማካሪ አቶ ዳርጌ ተክሉ በመክፈቻ ንግግራቸው በ2003 ዓ.ም የተጀመረው ታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ በመላው የሀገራችን ህዝቦች ብርቱ ተሳትፎ 94 ነጥብ 5 ከመቶ ማድረስ ተችሏል።

በዞኑ የመንግስት ሰራተኞች፣ ባለሀብቶችና ነጋዴዎች፣ አርሶ አደሮችና በሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች 87 ሚሊዮን 152 ሺህ 277 ብር በቦንድና በስጦታ ተሰብስቧል።

በክብረ በዓሉም የጉራጌ ዞን ዋና አፈ ጉባኤ ክብርት ወይዘሮ ልክነሽ ስርገማ፣ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ልዩ አማካሪ አቶ ዳርጌ ተክሉ፣ የዞኑ ምክትል አስተዳዳሪና የግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ አበራ ወንድሙና የዞኑ ከፍተኛ አመራሮች፣ ባለሀብቶችና የንግዱ ማህበረሰብና ሌሎችም ተገኝተዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *