በጉራጌ ዞን ቀቤና ወረዳ የዘቢሞላ ሐድራ መውሊድ ለ112ኛ ጊዜ በድምቀት እየተከበረ ይገኛል።

የዘቢሞላ ሀድራ ድንቁርናን እና መሐይምነት በማስወገድ እውቀትን በማስፋፋት ረገድ ከፍተኛ ሚና እንዳለው ተጠቁሟል፡፡

የዘቢሞላ አስተዳዳሪ ሼህ መሀመድ አሚን ሼህ በድረዲን ሀድራው ከመቶ አመታት በላይ ለሙስሊሙ ማህበረሰብ ሐይማኖታዊ አገልግሎት በመስጠት በርካታ ምሁራኖችን አፍርቷል ብሏል።

በማዐዕከሉ የሚገኙ ጥንታዊ መዛግብቶችን፣ የሚንቀሳቀሱና የማይንቀሳቀሱ ቅርሶች በማሠባሠብና በማደራጀት በቀጣይ የምርምር ማዕከልና የቱሪስት መዳረሻ ለማድረግ በትኩረት እየሰሩ መሆኑን አብራርተዋል ።

በዓሉ ከተለያዩ አካባቢዎች ተሰባስቦ ስለ ሀይማኖታቸው የሚመካከሩበት፣የሀገራችንና ህዝቧቿ ሠላም እንዲሆኑ ፀሎትት የሚደረግበት፣የነብዩ መሀመድ (ሰ.ዐ.ወ) የህይወት ታሪክ በተለያየ መልኩ ለምዕመኑ የሚቀርብበት ነው ብለዋል።

በተቋሙ ውስጥ የሚገኙ እድሜ ጠገብ ሀገር በቀል ዛፎች ሀድራው ለተፈጥሮ ሀብት እንክብካቤ ልዩ ትኩረት ተሠጥቶ እየተሠራ መሆኑን ያመለክታል።

ተጨማሪ መረጃ ይኖረናል ከስፍራው ተከታትለን እናደርሶታለን !

በመረጃ ምንጭነት ገጻችን ምርጫዎ ስላደረጉ እናመሰግናለን!!

= ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!
በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:-
https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36Cx!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *