በጉራጌ ዞን ቀቤና ወረዳ አንድ እናት 3 ህጻናት በሰላም ተገላገለች።

ህዳር 1 /2015 ዓ.ም

በጉራጌ ዞን ቀቤና ወረዳ አንድ እናት 3 ህጻናት በሰላም ተገላገለች።

በቀቤና ወረዳ ቆላ ከባዳ ቀበሌ አንዲት እናት ሶስት ህጻናትን በሰላም ተገላገለች።

እናትየውን ጨምሮ ሶስቱም ልጆች በመልካም ጤንነት ላይ ይገኛሉ።

ሶስቱን ህጻናት በሰላም የተገላገችዉ ወላጅ እናት መሁባ ጀማል ትባላለች ትውልዷ በቀቤና ወረዳ ቆላከባዳ ቀበሌ ሲሆን ትዳር መስርታ በወልቂጤ ከተማ ትኖራለች።

ከአሁን በፊት አንዲት ሴት ልጅ የነበራት ይቺ እናት በሁለተኛው እርግዝና ወቅት ሶስት ልጆችን በወልቂጤ ዩኒቨርስቲ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በቀዶ ጥገና ተገላግላለች።

እናትየውን ጨምሮ ሶስቱም ልጆች በመልካም ጤንነት ላይ ይገኛል።

የጉራጌ ዞን ሴቶችና ህፃናት ጉዳይ መምሪያ ለእናትየው እና ለህፃናቱ የሚሆን የወተት ፣ የአልባሳት እና የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁስ ድጋፍ አድርጎላቸዋል።

የመምሪያው ሀላፊ ወይዘሮ መሰረት አመርጋ ድጋፉን በሚያበረክቱበት ወቅት እንደተናገሩት የመደጋገፍና የመረዳዳት ባህላችን እንዲጎለብትና እናቶች በወሊድ ምክንያት ለከፋ ችግር እንዳይጋለጡ ማህበረሰቡ እርስ በርስ የመረዳዳት ባህሉን ሊያጠናክር ይገባል።

ይቺ እናት ከገጠማት የኑሮ ችግር የተነሳ ምንም እንዳይሰማት እስካሁን የቻሉትን ሁሉ ለደገፏት የቀበሌው ማህበረሰብ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

መምሪያውም ከያዘው 1 በመቶ በጀት ላይ ከ5 ሺህ ብር በላይ ወጪ በማድረግ ወተትን ጨምሮ አልባሳት፣ የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁስና ለእናትየው የሚሆን አጃ ድጋፍ አድርጎላታል ሲል የዘገበዉ የጉራጌ ዞን መንግስት ኮሚኒኬሽን መምሪያ ነዉ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *