በሴቶች አደረጃጀቶች መከላከያ ሰራዊት ድጋፍ ለ5ኛ ዙር የስንቅ ዝግጅት በዞኑ በሁሉም ወረዳና ከተሞች ተጠናክሮ ቀጥለዋል።
የደቡብ ክልል ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ክብርት ወ/ሮ ፋጤ ሶርሞሎ እንደገለፁት ለመከላከያ ሰራዊቱ እየተደረገ ያለው እገዛ ትልቅ አቅም ነው ብለዋል ።
እኛ እያለን ሀገራችን አትፈርስም ብለው በግምባር ለተሰለፉት ጀግኖቻችን እኛ ሴቶች እያለን ደግሞ ሰራዊቶቻችን አይራቡም በማለት በተግባር መሰማራታቸው ገልፀዋል ።
ዞኑ ከአይነትና ከገንዘብ ድጋፍ በተጨማሪ ልጁን በማሰለፍ ትልቅ ስራ መስራቱን ጠቅሰው አመስግነዋል።
የጉራጌ ዞን ሴቶችና ህፃናት ጉዳዮች መምሪያ ሀላፊ እና የመከለያ ሰራዊት የሀብት አሰባሰብ ንዑስ ኮሚቴ ሰብሳቢ እንደገለፁት እስከአሁን በዞኑ 1መቶ 5 ሚሊዮን ብር በላይ የተለያዩ ድጋፍ የተደረገ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 30 ሚሊዮን ያህሉ በሴቶች የተደረገ ድጋፍ ነው ብለዋል።
ዞኑ እስከአሁን በአይነትና በገንዘብ ከፍተኛ ድጋፍ እያደረገ መሆኑ የገለፁት ወይዘሮ መሰረት በዚህ ዙር 4 ሺህ 5 መቶ ኩንታል በሶ እና 3 መቶ 54 ኩንታል ስኳር አሰባስቦ ወደ ግምባር በአጭር ጊዜ ይላካል ብለዋል ።
የጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ ወደ ግምባር መዝመት ጋር ተያይዞ የተፈጠረው ከፍተኛ መነቃቃት ለማስቀጠል የተጀመሩ የተለያዩ የኪነጥበብ ስራዎችና የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራሞች ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉም ወይዘሮ መሰረት ገልጸዋል።
ለመከላከያ ሰራዊቱ የስንቅ ዝግጅት ስራ ላይ ያገኘናቸው የጉራጌ ዞን ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ክብርት ወ/ሮ አርሺያ አህመድ እና ሌሎችም ሴቶች እንደገለፁት በግንባር በሰለፍና ለሰራዊታችን ስንቅ በማዘጋጀት የሀገራችንን ሉአላዊነት እናስከብራለን ብለዋል።
የስንቅ ዝግጅቱ ለአምስተኛ ዙር መሆኑን ገልፀው ሀገራችን እስክትረጋጋ እና የተፈናቀሉት ሴቶችና ህፃናት መልሰን እስከምናደራጅ የሰላም ቀጠና ላይ ያለው የህብረተሰብ ክፍል የበኩሉን መወጣት እንዳለበት ገልፀዋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36Cx