በጉራጌ ዞን ማዕከል የሚገኙ የፌደራል፣ የክልልና የዞን የብልጽግና ፓርቲ አመራሮች “በመፍጠር እና በመፍጠን የወል እውነቶችን ማጽናት የብልግጽና ፓርቲ የቀጣይ የትግል ምዕራፍ ” በሚል ለ3 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና በወልቂጤ ከተማ መሰጠት ተጀምሯል።

ሰየብልጽግና ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባልና የደቡብ ክልል መንገድ ልማት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር አበባየሁ ታደሰ እንደገለጹት በባለፉት አመታት የተመዘገቡ ለውጦች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ አመራሩ በሀገር ደረጃ የሚስተዋሉ ተግዳሮቶችን ተረድቶ በጽናት ማረም ከሁሉም አመራር ይጠበቃል።

ቀጣይነት ያለው ልማትና መልካም አስተዳደር ለማረጋገጥ አሁን ላይ የሚስተዋሉ ክፍተቶችን መሙላትና የህዝቡ ተሳታፊና ተጠቃሚነትን ለማሳደግ በየደረጃው ያለው አመራር በትኩረት ሊሰራ ይገባ ተብለዋል ።

የሀገሪቱ ተለዋዋጭ ሁኔታዎች በማጠን ችግሮችን መፍታት የሚችል የፓለቲካ አመራር ለመፍጠር ሰፊ ጥረት እየተደረግ እንደሚገኝ የገለጹት ዶክተሩ ስልጠናው እስከታች ቀበሌ ድረስ የሚወርድ በመሆኑ ለሀገራዊ የብልጽግና ጉዞ እውን እንዲሆን ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረክታል ብለዋል ።

የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ በስልጠናው ማስጀመሪያ ላይ እንደገለጹት የብልጽግና ፓርቲ ወደ ስልጣን እንዲመጣ ይዟቸው የተነሳውና በምርጫው ወቅት ለህዝቡ ቃል የገባቸው የልማት ና የመልካም አስተዳደር ስራዎችን ተግባራዊ ለማድረግ ሁሉም ተቀናጅቶ መረባረብ ይኖርበታል ብለዋል።

ገዢው ፓርቲ የአመራሩና የአባላቱን አቅም ለማጎልበትና ወጥ የሆነ ግንዛቤ ጨብጦ ወቅቱን የሚመጥን ስራ እንዲሰራ ለማስቻል እየሰራ ሲሆን አመራሩም የሚሰጠውን ስልጠና በመነሻ በማድረግ የተጣለበት ኃላፊነት በአግባቡ ሊወጣ ይገባል ብለዋል።

በዛሬው ዕለት የተጀመረው ስልጠና “በመፍጠር እና በመፍጠን የወል እውነቶችን ማፅናት የብልጽግና ፓርቲ የቀጣይ ትግል ምዕራፍ የማድረግ ዓላማ ያለው ሲሆን ለተከታታይ 3 ቀናት የሚቀጥል መሆኑም ተገጿል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን መንግሥት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *