በጉራጌ ዞን ለሁለት ተከታታይ ቀናት ሲሰጥ የነበረው የ6ኛ ክፍል ዞን አቀፍ ፈተና ተጠናቋል።

በዞኑ 19 ሺህ 230 ተማሪዎች ፈተናውን መውሰዳቸውን ተጠቁሟል።

የጉራጌ ዞን ትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ መብራቴ ወ/ማርያም የፈተና መጠናቀቁን አስመልክተው በሰጡት መግለጨ እንዳሉት ዞናዊ የ6ኛ ክፍል የእርከን ማጠቃለያ ፈተና መሰጠቱ እውቀት ያላቸው በራሳቸው የሚተማመኑ ብቁ ተማሪዎች ለማፍራት የሚደረገው ጥረት ይበልጥ ውጤታማ ለማድረግ የሚያበረክተው አስተዋጽኦው ከፍተኛ ነው።

በዞኑ 377 አንደኛ ደረጃ ት/ቤቶች ሲማሩ የነበሩ 19 ሺህ 230 ተማሪዎች በ138 የፈተና መስጫ ጣቢያዎች በማደራጀት በ2ኛ ደረጃ መምህራን ማስፈተን መቻሉን ገልጸዋል።

ፈተናው በ2ኛ ደረጃ መምህራን ታርሞ የሚተነተን ሲሆን የተማሪዎቹ ማለፊያ ነጥብ በአዲሱ ስርአተ ትምህርት አቅጣጫ መሰረት በዞን ደረጃ የሚወሰን ይሆናል።

የ6ኛና የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች የሚወስዱት ፈተና ከጨረሱ በኋላ በበጎ አድራጎት እና በአረንጓዴ ልማት ስራ እንዲሳተፉ በተፈተኑባቸው ተቋማት የችግኝ ተከላ ማካሄዳቸውንና በቀጣይ በዩኒፎርም ለሚቸገሩ ተማሪዎች ለማገዝ ዩኒፎርማቸው መለገሳቸውን ጠቁሟል።

ተማሪዎች በእረፍት ጊዜያቸው በክረምት የሚሰጡ የማጠናከሪያ ትምህርት ከመማር ጎን ለጎን በየአካባቢያቸው በሚከናወኑ የበጎ ፈቃድ ስራዎች በመሳተፍ ማህበራዊ ኃላፊነታቸው እንዲወጡ በርካታ ትም/ቤቶች በፈተናዎች ማጠናቀቂያ ወቅት ከተማሪዎች ጋር ውይይት ማድረጋቸው ገለፀው ሀላፊው ተማሪዎችም በየአካባቢያቸው ይህንኑ እንዲለማመዱ ጥሪ አቅርበዋል።

በፈተና ሂደቱ ተማሪዎች ያለምንም ኩረጃ በራሳቸው ጥረት ተረጋግተው እንዲፈተኑ ፈታኝ መምህራን፣ ሱፐርፋይዘሮች፣ የፈተና ጣቢያ ኃላፊዎች፣ የጸጥታ አካላትና በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች የተሰጣቸውን ኃላፊነት በአግባቡ መወጣታቸውን የገለጹት አቶ መብራቴ ለዚህም ላቅ ያለ ምስጋናቸው አቅርበዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *