በዶሮ ዘርፍ ተሰማርተው በመስራታቸው ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚ ከመሆን ባለፈ ገበያ እያረጋጉ እንደሚገኙ በጉራጌ ዞን ጉመር ወረዳ በዶሮ ዘርፍ የተደራጁ ወጣቶች ተናገሩ።


በወረዳው በእንሰሳት በሁለም ዘርፎች በትኩረት በመስራት የህብረተሰቡ ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየተሰራ እንደሚገኝ የጉመር ወረዳ አስተዳዳር አስታወቀ።

አቶ አድማሱ ውርጅነና አቶ ደመላሽ በጉመር ወረዳ በዶሮ እርባታ የተሰማሩ ወጣቶች ናቸው።

አክለውም አቶ አድማሱ 150 ዶሮ በማርባት በቀን 100 እንቁላል በቀን እንደሚያገኙና አቶ ደመላሽ 200 ዶሮ በማርባት 180 እንቁላል እንደሚያነሱ ገልጸው በዚህም የምግብ ፍጆታና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚ ከመሆናቸው ባለፈ ለገበያ በማቅረብ የዋጋ ንረት እያረጋጋጉ እንደሆነ ገልጸዋል።

ሌላኛው ወጣት አቶ ይርጋለም ነጋሽ እንዳሉት በዶሮ እርባታ፣ በበግ ማሞከትና በንብ ማነብ ስራ በመሰማራት እየሰሩ መሆኑን ገልጸው በቀጣይ ይበልጥ አስፍተው በመስራት ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚ ከመሆን ጎን ለጎን ገበያ ለማረጋጋት ተግቶ እንደሚሰራ ተናግረዋል።

ወጣቶች ጊዜያቸው አልባሌ ቦታ ከመዋል በዘርፉ ተሰማርተው እንዲሰሩ መክረው ይበልጥ በስፋት ለመስራት በአካባቢው የውሃ፣ የመኖ ችግር መኖሩን ተከትሎ የሚመለከተው አካል ችግሩ እንዲፈታላቸው ጠይቀዋል።

የጉመር ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ደሳለኝ ከድር በወረዳው በእንሰሳት ዘርፍ የአርሶ አደሩና የወጣቶች ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትኩረት እየተሰራ ይገኛል።

በተለይም በሌማት ትሩፋት እየተሰሩ ያሉ ስራዎች በዝርያያ ማሻሻል፣ በማር ምርት፣ በጓሮ አትክልት በትኩረት በመሰራቱ የህብረተሰቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ከማረጋገጥ ባለፈ ገበያያ ማረጋጋት ተችላል ብለዋል።

ከዚህም ባለፈ በወረዳው የዶሮ መንደር በመመስረት ከአርሶ አደሩ ባለፈ ወጣቶች በዘርፉ በማደራጀት ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚ እየሆኑ መሆኑን ገልጸዋል።

የጉመር ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪና የግብርና ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ደገሙ አለሙ በወረዳው በሌማት ትሩፋት የዶሮ፣ የማር፣ የስጋ፣ የንብና የአሳ መንደር በመመስረት በተሰራው ስራ ውጤታማ ስራ እየተሰራ ይገኛል።

በዚህም የዶሮ መንደር ከቁጥቁጥ በመውጣት መንደር በመመስረት የአርሶ አደሩ ተጠቃሚነት ሊያረጋግጥ የሚችል ስራ እየተሰራ መሆኑን ገልጸው በወረዳው 7 መንደር በመመስረት ለእያንዳንዱ አርሶ አደር 25 ዶሮ በመስጠት ከምግብ ፍጆታቸው ባለፈ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸው ለማረጋገጥ እየተሰራ እንደሚገኝ አመላክተዋል።

በወረዳው ወጣቶች በማህበር በማደራጀት ብድር በማመቻቸትና በፕሮጀክት ድጋፍ እንዲያገኙ በማድረግ የአንድ ቀን ጫጩት በመውሰድ በኩታ ገጠም የዶሮ መንደር በመመስረት በትኩረት በመስራቱ ውጤታማ ስራ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

በንብ ማነብ በኩታ ገጠም ባህላዊና ዘመናዊ የንብ ቀፎ በማቀናጀት ሰፋ ያለ ስራ እየተሰራ መሆኑን ያነሱት አቶ ደገሙ በዚህም ህብረተሰቡ ማር በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲያገኙ አስችላል ብለዋል።

ከዚህም ባለፈ በዝርያ ማሻሻል፣ በወተት፣ በማሞከት፣ በጓሮ አትክልት እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰው በተጨማሪም በወረዳው በ3 ሀይቆች ከፍተኛ የአሳ ምርት መኖሩን ተከሎ ወጣቶች በዘርፉ በመደራጀት የአሳ ምርት ከአካባቢ አልፎ ለሌሎች አካባቢዎች እንዲያቀርቡ እየተሰራ ነው ብለዋል።

በዚህም በሁሉም ዘርፎች በተሰሩ ስራዎች የአርሶ አደሩ የምግብ ዋስትና ማረጋገጥ፣ ገበያ ማረጋጋትና የኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚ ከማድረግ ባለፈ የወጣቶች ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ እንዳስቻለ ጠቁመዋል ሲል የዘገበው የዞኑ የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *