በድሬዳዋ ከተማ ከ4ሺ በላይ የጉልባማ አባላት “ማህበራዊ እሴት ለዘላቂ ልማት” በሚል መሪ ቃል ሲያካሄዱት የዋለው የንቅናቄ መድረክ በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል።


በንቅናቄ መድረኩ በከተማ አስተዳደሩ ከሚገኙ የጉራጌ እድሮች መካከል 18 ቱ የጉራጌ እድሮች ፎረም የመሠረቱ ሲሆን ዛሬ በይፋ መመስረታቸውን ባሳወቁበት መድረክ በድሬዳዋ ከተማ የሚገኘውን የጉልባማ መሬት ለማልማት መነሻ 3.2 ሚሊየንብ ያበረከቱ ሲሆን በርካታ ተወላጆች ለግንባታው ድጋፍ የሚሆን ገንዘብ ለመለገስ ቃል የገቡ ሲሆን: በከተማው የሚኖሩ ኢንጅነሮች ለህንፃው የሚያስፈልገውን ዲዛይን ባጭር ግዜ ሰርቶ በማስረከብ በግንባታው ሂደት የሚጠበቅባቸውን ሀላፊነት ለመወጣት ቃል ገብተዋል: በተጨማሪም በከተማ አስተዳደሩ ለመጀመሪያ ግዜ የጉራጌ ብሄረሰብ የባህላዊ ዳኝነት ሽማግሌዎች ተቋቁመው መሠረታዊ የመተዳደሪያ ደንቦቻቸውን ለተሳታፊው እንዲያውቋቸው አድርገዋል:: በመድረኩ በአጠቃላይ የጉራጌ ብሄረሰብ: የጉልባማ አሁናዊ ገፅታና የጉራጌ ብሄረሰብ በድሬዳዋ ከተማ ልማትና አስተዳደር የነበረውና ያለው አስተዋፅኦ ፅሁፍ ቀርቦ ውይይት የተደረገ ሲሆን ለአብነት ያስገነቡት ድልድይ በስማቸው የሚጠራው አልፈሪድ ሻፊ “አልፈሪድ ሻፊ ድልድይ” ተነስቷል:: በመድረኩ ተሳታፊ የነበሩት የጉልባማ የቦርድ ሰብሳቢ አቶ ሺሰማ ገ/ስላሴ የጉራጌ ዞኖች አስተዳደሮችና የጉልባማ ም/ቦርድ ሰብሳቢዎች አቶ ላጫ ጋሩማና አቶ ሙስጠፋ ሀሰን ስለጉልባማ ስለ ጉራጌ ዞኖች አሁናዊ ሁኔታ መልክት በማስተላለፉ ተወላጁ በየአካባቢው ሰላማዊ ሁኔታ እንዲሰፍንና አካባቢውን በማልማት ሂደት እንከዚህ ቀደሙ ከመንግስት ጎን በመሆን እንዲሳተፍ: አንድነቱን እንዲያጠናክር የጉልባማ በመሆንና ሌሎችንም አባል በማድረግ በትውልድ አካባቢያቸው የልማት ስራ አንዲሳተፉ አሳስበዋል:: የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር በተወካዩ በኩልና የአካባቢ አባገዳዎች የጉራጌ በድሬዳዋ ከተማ ሰላምና ልማት የሚያበረክተውን አስተዋፅኦ አጠናክሮ እንዲቀጥል ያሳሰቡ ሲሆን የከተማ አስተዳደሩ በሚፈልጉት ድጋፍ በሙሉ ከህዝቡ ጎን መሆኑን አረጋግጠዋል: በመጨረሻም መድረኩ በካርታ ርክክብና በከተማው ለበርካታ አመታት ተወላጆችን ለተለያዩ ማህበራዊ ጉዳዮች በማስተባበርና በመምራት በዛሬው እለት የዘጋጀው ፕሮግራም በዚህ መልክ ደምቆ እንዲካሄድ ላስተባበሩ አካላት የካባ ማልበስና እውቅ በመስጠትና በተለየ መልኩ ሁሌም በድሬዳዋ ከተማ የተወላጆችና የጉልባማን ስራ በማስተባበር ለመራው አቶ አበበ ዋልጋ ተጨማሪ እውቅና በመስጠት ከተሳታፊዎች ጋር የኢትዮጵያን ብሄራዊ መዝሙር በጋራ በመዘመር ፕሮግራሙ ተጠናቋል:: ጠንካራ አንደነት ለዘላቂ ልማት!

መረጃው የልማትና ባህል ማህበር ድህረ ገጽ ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *