በድህረ ጦርነት ሊያጋጥሙ የሚችሉ ችግሮች በአግባቡ መፍታትና የዜጎች ደህንነት የመጠበቅ ስራ በትኩረት እንደሚሰራ የጉራጌ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት አስታወቀ።

መንግስት በድህረ ጦርነት ወቅት የሚከሰቱ ችግሮች ማረም፤ የሚዜጎች እና የሀገርን ደህንነት ለማስጠበቅ ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሰራ ተገልፀዋል።

ከህልውና ትግላችን ወደ ብልፅግና ጉዞአችን በሚል መርህ በድህረ ጦርነት ወቅት የሚያግጥሙ ችግሮች በብቃት ለመፍታት የዞንና የወረዳ ከፍተኛ አመራሮች ዛሬ በቡታጀራ ከተማ ውይይት ጀምረዋል።

በመድረኩ የተገኙት የደቡብ ክልል የመንግስት ረዳት ተጠሪ አቶ ይሁን አሰፉ እዳሉት በጦርነቱ ውስጥ ሆነን ያስመዘገብናቸውን ልማቶች ሳንዘነጋ በድህረ ጦርነቱ የሚገጥመንን የፖለቲካ ችግሮቻችን ነቅሰን በማውጣት ውጤት ላይ መድረስ አለብን።

መድረኩ ከጦርነቱ በኋላ የአመራሩ ሚና ምን ምሰል እንዳለበትና የሚገጥሙን ችግሮች በሚፈቱበት ሁኔታ በቀጣይ ቀናት በስፋት ውይይቶች ይደረጋሉ ብለዋል ።

የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ መሀመድ ጀማል በበኩላቸው በድህረ ጦርነት የፓለቲካ መዛነፍ እንዳይፈጠርና እሴቶቻችን እንዳይሸረሸሩ አመራሩ እና መላው የዞኑ ህዝብ አንድነቱን በማጠናከር ለመስራት ከስምምነት ላይ ለመድረስ ውይይቱ የላቀ አስተዋጽኦ ይኖረዋል ብለዋል።

የጉራጌ ዞን ረዳት የመንግስት ተጠሪ አቶ
አለማየሁ ገብረመስቀል ስለ ውይይቱ በሰጡት መግለጫ በጦርነቱ የደረሠውን ሠብአዊና ቁሳዊ ቀውስ ለማስተካከል የአመራር ሂደቱ ላይ መግባባት የሚፈጠርበት መሆኑ ገልፀዋል ።

አቶ አለማየሁ አክለውም በህልውና ዘመቻው የዞናችን ህዝቦች ለመከላከያ ሠራዊት ያሳዩትን ደጀንነት በድህረ ጦርነቱም መድገም አለባቸው ብለዋል።

ጦርነቱ ያደረሰብንን ጉዳት መልሶ ለመገንባት የጋራ ትብብር ሊደረግ እንደሚገባና ለዚህም በመድረኩ ለቀጣይ 3 ቀናት እንደሚቀጥልና ወሳኝ አቅጣጫዎች የሚቀመጥበት መሆኑ ገልፀዋል።

= ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!

በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36Cx

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *