በደቡብ ክልል እግር ኳስ ፌደሬሽን አዘጋጅነት ሲካሄድ የቆየው የእግር ኳስ ክለቦች ሻምፒዮና ውድድር ተጠናቀቀ።

ግንቦ

ቡኢ ከነማ የእግር ኳስ ቡድን የ2015ዓ.ም በደቡብ ክልል እግር ኳስ ፌደሬሽን የእግር ኳስ ክለቦች ሻምፓዮና ዉድድር ላይ ሶስተኛ ደረጃ በመያዝ አጠናቀቀ።

በዛሬዉ ዕለት የፍፃሜ ጨዋታ የቡኢ ከነማ እግር ኳስ ቡድን ከስለጤ ዞኑ ሚቶ አቻዉን ያገናኘ ሲሆን ጨዋታዉ በእልህ አስጨራሽ ፉክክር ያደረጉ ሲሆን ሳሙኤል ደበበ በመጀመሪያዉ የጨዋታው አጋማሽ አንድ ጎል በማስገባት የቡኢዎቹ እርግቦች የመጀመሪያውን አጋማሽ አጠናቀዋል ።

በሁለተኛው አጋማሽ በአቤል ታሪኩ አማካኝነት ሁለተኛ ጎል በማስቆጠር መሪነቱን ይበልጥ አጠናክሮ ከሜዳ አሸናፊነታቸው በማረጋገጥ ሶስተኛ ደረጃ በመያዝ አጠናቀዋል ።

ከሳምንታት በፊት በተካሄደው ዞናዊ የክለቦች ውድድር ቡኢ ከተማ ሶስተኛ ደረጃ በመያዝ ዞኑን በመወከል ለክልል ክለቦች መታጨቱ ይታወቃል ሆኖም በእልህ አሰጨራሽና አስደማሚ ጥበብ ከክልሉ በድጋሚ ሶስተኛ በመውጣት ክልሉን ወክሎ በሃገር አቀፍ ደረጃ ለሚካሄደው የክለቦች ሻምፓዮና ውድድር ተሳታፊ መሆኑን ማረጋገጥ ችሏል ።

በሽልማት ስነስራቱ የቡኢ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ በለጠ ጫካ ፣ የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ አሰፋ ፈይሳ እና ሌሎች የከተማው የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ተገኝተው ደስታቸውን ገልጸውላቸዋል ።
መረጃው የቡኢ ከተማ አስ/የመ/ኮ/ጉ/ጽ/ቤት ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *