በደቡብ ሶዶ ወረዳ ኬላ ዙሪያና ጎጌቲ ሶስት ቀበሌዎች ወጣቶች የአቅመ ደካማ ቤት ዕድሳትና የማሳ አረም የበጎ አድራጎት ተግባራት ተከናውነዋል።

ነሃሴ 27/2014

በደቡብ ሶዶ ወረዳ ኬላ ዙሪያና ጎጌቲ ሶስት ቀበሌዎች ወጣቶች የአቅመ ደካማ ቤት ዕድሳትና የማሳ አረም የበጎ አድራጎት ተግባራት ተከናውነዋል።
**
በዛሬ ዕለት በኬላ ዙሪያ ወጣቶች የቀበሌ ነዋሪ የሆኑት ረጂ ጠዋሪ የሌላቸው እናት ወ/ሮ ፉንጎ ገረሙ ቤት ጭቃ ምርጊትና በመኪና አደጋ አካሉ ላይ በደረሰበት አደጋ ምክንያት መንቀሳቀስ የማይችለውን የአቶ ጥላሁን ታምሬ የጤፍ ማሳን በትላንትናው ዕለትም የአረም ማረም ስራን ሰርተዋል።

በተያያዘም የጎጌቲ ሶስት ቀበሌ ላይ የሚኖሩ ወጣቶች የቀበሌው ነዋሪ የሆኑት አቶ መለሰ ቤት እድሳት ስራን አከናውነዋል።

የበጎ አድራጎት ስራውን በቀጣይም በስፋት አጠናክረው እንደሚቀጥሉና በተለይም መጪውን የበዓል ምክንያት በማድረግ ጠዋሪ ረጂ ለሌላቸውና አቅመ ደካማ ማህበረሰብ ክፍሎችን የበዓል መዋያ የሚሆን ድጋፍ ለማድረግ ገቢ የማሰባሰብ ስራ በመስራት ላይ እንዳሉ ያነጋገርናቸው የቀበሌ ወጣቶች ተወካዮች የቀበሌ አመራር አካላት ገልፀዋል።

የደቡብ ሶዶ ወረዳ ወጣቶች ማህበር ሰብሳቢ የሆኑት አቶ ታሪኩ ደምሴ እንደገለፁት የክረምት የበጎ አድራጎት ስራዎችን በየደረጃው ያለውን አደረጃጀቶች በጎ ልብ ያላቸው ወጣቶችን አካላትን በማስተባበርና በማጠናከር እየተሰራ ያለና በሁሉም ዘርፍ በሚባል መልኩ ተጠናክሮ እየቀጠለ መሆኑን ገልፀዋል።

የበጎ አድራጎት አገልጎሎት ተጠቃሚ የማህበረሰብ ክፍሎች የበለጠ የሚጠቀሙበት ተግባሩን በቅንነት የሚያስተባቦሩና የሚሳተፉ አካላት የመንፈስና የህልና እርካታ የሚያገኙበት እንዲሁም ብዙ ሃብት የሚያድንበት በመሆኑን ተግባራቱን ማጠናከር እንደሚገባ አሳስበዋል።

የደቡብ ሶዶ ወረዳ ወጣቶችና ስፖርት ፅ/ቤት ምክትል ኃላፊና የወጣቶች ዘርፍ አስተባባሪ የሆኑት አቶ ታጋይ ስንታየሁ እንደተናገሩት ኬላ ዙሪያ ቀበሌዎች የሚገኙት ወጣቶችንና ሌሎች የማህበረሰብ ክፍሎችን በማስተባበር በተለያዩ ምክንያት የጤና ችግር ላጋጠማቸው ለአረጋዊያንና አቅመ ደካማ የማህበረሰብ ክፍሎችን በመለየት የቤት ዕድሳት፡የአረም ማረም ስራዎችን እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል።

ተግባሩ በሌሎችም ቀበሌዎች ተጠናክሮ እየተሰራ መሆኑንና መጪው አዲስ ዓመትንና የመስቀል በዓል በማስመልከት በየቀበሌው በሚገኙወጣቶችንና የማህበረሰብ ክፍሎችን በማስተባበር ለበዓል መዋያ የሚሆን ገቢ የማሰባሰብ ስራ እየተሰራ መሆኑን አመላክተዋል።

የደቡብ ሶዶ ወረዳ ወጣቶችና ስፖርት ፅ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ አወቀ ገራቸው የክረምት የበጎ አድራጎት ስራዎች ሰውን መሰረት ያደረጉ ስራዎችን የመንግስት አደረጃጀቶች በመጠቀም በአስራ ስምንቱም ቀበሌዎች ወጣቱን በማስተባበር እንዲሁም ማህበረሰብን በማሳተፍ የአረንጓዴ አሻራ የቤት ዕድሳት የማሳ አረምና ሌሎችም ተግባራት እየተሰሩ መሆኑን ገልፀዋል።

በተለይም የክረምት ስፖርት ውድድር በመጠቀም ወጣቱን በማሰባሰብ ከስፖርቱ ጎን ለጎን የበጎ አድራጎት ስራውን እያሳለጡ መሆኑን አመላክተዋል።

በመጨረሻም ኃላፊው የቀበሌ አመራር አካላት የወጣት አደረጃጀቶችና ማህበረሰቡ ከወረዳው በመቀናጀት ተግባሩን በተሻለ ሁኔታ እየመሩ በመሆኑ ምስጋና ያቀረቡ ሲሆን በቀጣይም ቀሪ ተግባራትን በተገቢው መፈፀምና የበዓል መዋያ ድጋፍ ስራዎችን ተጠናክሮ መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል።

ዘገባው የደቡብ ሶዶ ወረዳ መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *