በየደረጃው ማህበረሰቡን የማያነሳቸው የልማት ጉድለቶ ለመሙላትና የዞኑ ህዝብ አንድነት ለማጠናከር የጉራጌ ልማትና ባህል ማህበር ያለው አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑ የጉራጌ ዞን አስተዳደር ገለፀ ።

የጉራጌ ልማትና ባህል ማህበር የቦርድ አመራሮች ከዞኑ አመራሮች ጋር ማህበሩን ለማጠናከርና በቀጣይ በሚከናወኑ ተግባራት ላይ ውይይት አድርገዋል።

የማህበሩ የቦርድ ሰብሳቢና የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ዴኤታ አቶ ሺሰማ ገብረስላሴ በውይይቱ ወቅት እንደገለፁት የጉራጌ ማህበረሰብ ከዚህ ቀደም የነበረውን የመረዳዳትና ተባብሮ የመስራት ባህሉን በማጠናከር ከልማት ማህበሩ ጋር ህዝቡን ማስተሳሰር ይገባል።

ጉልባማ ባለፉት አመታት አባላቱ በማጠናከርና አጋሮች በማስተባበር እንዲሁም የዞኑ ተወላጅ ባለሀብቶች በማሳተፍ የጎደሉ የልማት ክፍተቶች ሲሞላ እና ማህበራዊ ችግሮችሲፈታ ቆይተዋል ብለዋል።

አክለውም አቶ ሺሰማ ማህበሩ ከማህበረሰቡ አቅም፣ካለን ደጋግፎ የማደግ ልምድና ካሉብን የልማት ክፍተቶች አንፃር ብዙ እርቀቶች አለመጓዙና ገና ብዙ ስራ እንደሚጠብቀው አብራርተዋል።

በመሆኑም የማህበሩን አባላት ለማጠናከርና ከማደራጀት እንዲሁም ቅንጅታዊ አሰራር ለመፍጠር የንቅናቄ መድረኮች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የገለፁት አቶ ሺሰማ የልማት ማህበሩ የሚሰራቸው ስራዋች ለዞኑ እና ከዞኑ ውጭ ለሚኖሩ ማህበረሰብ ግንዛቤ በመፍጠር የተሳሳቱ መረጃና አስተሳሰብ በጋራ ማረም ይገባል ብለዋል።

በቀጣይም በልማት ማህበሩ የተጀመሩ ግምባታዎችን ለማጠናቀቅና ተጨማሪ ወሳኝ ስራዎች ለመጀመር ከህብረተሰቡ ጋር በቅንጅት እንደሚሰራ አረጋግጨዋል።

የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ መሀመድ ጀማል በበኩላቸው ልማት ማህበሩ ህዝቡን የሚመጥን ለማድረግ ትኩረት ተሰጥቶ ሊሰራ ይገባል ለዚህም ሰፊውን ድርሻ መውሰድ ያለበት ህዝቡን የሚመራው አመራር ነው ሲሉ ገልፀዋል።

አንድ ህዝብ ጠንካራ የሚሆነው ማህበረሰባዊ የሆነ ጠንካራ አደረጃጀት ሲኖረው ነው የሚሉት አስተዳዳሪው ልማት ማህበሩ ሁሉንም ጠቃሚ አስተሳሰቦች አቅፎ ሊይዝ የሚችል መሆን እንዳለበት ተናግረዋል።

አቶ መሀመድ አክለውም በቀጣይ ወቅት በህዝባችን ውስጥ ገብተን ተገቢ ንቅናቄና ግንዛቤ በመፍጠር በተጨባጭ ችግር ፈቺና ጠንካራ ስራዎች ይሰራል ብለዋል።

የጉራጌ ልማትና ባህል ማህበር ዋና ስራስኪያጅ አቶ ቅባቱ ተሰማ እንዳሉት ልማት ማህበሩ ችግር ፈቺ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ሰጥቶ የሚሰራቸው በርካታ ስራዎች መኖራቸው ገልፀው የዞኑ አስተዳዳርና የልማት ማህበሩ ያስተሳሰራቸው የህዝቡ ጥቅ በመሆኑ በቀጣይም በቅንጅት ይሰራል ብለዋል።

ልማት ማህበሩ መጠናከር እንዲችል ከዞኑ መንግስትና ህዝብ የምንሻው ድጋፍ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት የሚሉት አቶ ቅባቱ የሌሎችን የልማት ማህበራት ተሞክሮ በመውሰድ ሁሉም አካላት ለልማት ማህበሩ ተግባር መቃናት የበኩላቸውን መወጣት እንዳለባቸው ገልፀዋል።

የውይይቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው ማህበሩ ከዚህ ቀደም በርካታ ችግሮችን አልፎ እዚህ መድረሱ ተናግረው አሁን ያለው ትውልድ ተረክቦ ሊገለገልበትና ሀይሉን አሰባስቦ ሊያስቀጥለው ይገባል።

ተጨማሪ ሀብት ለማሰባሰብ የሚረዱ አማራጮችን በመጠቀም ማህበሩን በገቢና በአባላት ሊጠናከር እንደሚገባ ገልፀዋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።

በመረጃ ምንጭነት ገጻችን ምርጫዎ ስላደረጉ እናመሰግናለን!!
= ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!
በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:-
https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36Cx

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *