በየደረጃው ህዝቡ የሚጠይቃቸው የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች በመፍታት ተጠቃሚነቱን ለማረጋገጥ የአቤቱታና ቅሬታ ሰሚ አካላት በትኩረት ሊሰሩ እንደሚገባ የኢትዮጵያ የህዘብ እምባ ጠባቂ ተቋም ገለፀ ።

ተቋሙ ከአለም ባንክ ጋር በመተባበር በደቡብ እና በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልሎች ውስጥ ለሚገኙ የአቤቱታ እና ቅሬታ ሰሚ አካላት የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና በወልቂጤ ከተማ መስጠቱን ተመልክቷል ።

በኢትዮጵያ የህዘብ እምባ ጠባቂ ተቋም የህግ እና ይግባኝ ምርመራ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ደነቀ ሻንቆ በስልጠናው ወቅት እንደተናገሩት የመልካም አስተዳደር ስርዓት መስፈን ለማህበራዊ፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ እድገት መሰረት ነው።

በመሆኑም በየደረጃው ህዝብ የሚያነሳቸው ጥያቄዎች በፍጥነትና በጥራት ምላሽ እንዲያገኙ የታችኛው መዋቅር ከፍተኛ አበርክቶ ያላቸው በመሆኑ የአቤቱታና ቅሬታ ሰሚ አካላት አቅም ለማጎልበት ተቋሙ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል ።

መንግስት ህብረተሰቡ ተጠቃሚ ለማድረግ እያከናወናቸው ያሉ የልማት ስራዎች ውጤታማ ለማድረግ ህዝቡ በማሳተፍ በሚተገበረው የልማት ፕሮጀክት እቅድና የሚያስፈልገው በጀት እንዲያውቅ ግንዛቤ ሊፈጠርለት ይገባል።

ይህ ደግሞ የአሰራር ግልጸኝነት ከመፍጠር ባሻገር ህብረተሰቡ በሚያደርገው ክትትል ፕሮጀክቶቹ ጥራት እንዲኖራቸውና ዘላቂ አገልግሎት እንዲሰጡ ያስችላል ብለዋል።

እንደ ዳይሬክተሩ ገለፃ በከፍተኛ ወጪ የሚገነቡ ልማቶች የሚፈለገውን አገልግሎት ሳይሰጡ ሲበላሹ ህብረተሰቡ በየደረጃው ለሚገኙ የአቤቱታና ቅሬታ ሰሚ አካላት መረጃ በሚሰጡበት ወቅት ችግሮቹ በፍጥነት በማረም የግልጽነትና የተጠያቂነት አሰራር ሊጠናር ይገባል ።

በደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር የመልካም አስተዳደርና አካባቢያዊ ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ኑርዬ ሱሌ ስልጠናው የህዝብን ጥያቄ ለመመለስና የባለሙያዎች የውሳኔ ሰጪነት አቅም ለማሳደግ ያግዛል ብለዋል።

ከየትኛውም አገልግሎት ሰጪ ተቋማት የሚቀርቡ አቤቱታና ቅሬታዎች ተቀብለው ውሳኔ እንዲሰጡና የአሰራር ብቃት ለማሳደግ ያግዛል።

አያይዘውም አቶ ኑሪ ገለፃ ገለፃ ይህ ስልጠና በመልካም አስተዳደር ችግሮች ምክንያት የሚከሰቱ ግጭቶች በማጣራት ፈጣን ውሳኔ እንዲያገኙና በሚሰጠው አገልግሎት ባለጉዳዮች ለማርካት እንዲሁም የአፈጻጸም ጥራት በብቃት ለመከወን ያግዛል።

የህዝብ እምባ ጠባቂ ተቋም የሚቀርቡለትን አቤቱታና ቅሬታዎች አጣርቶ ውሳኔ ከመስጠት ባሻገር አፈጻጸሙ በመከታተል ረገድ አበረታች ውጤቶች አስገኝቷል።

የስልጠና ተሳታፊዎች ስልጠናው ከህዝብ የሚነሱ ቅሬታዎች ለመፍታት እና የቅሬታ አቀራረብ ስርዓት ህግን የተከተከ እንዲሆን ያስችላል ብለዋል።

ተቋሙ ህዝቡ የሚያነሳቸው የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ለመመለስ ከአስፈጻሚ አካላት ጋር በቅንጅት መስራት ይጠበቅበታል ብለዋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።

= ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!

በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36Cx

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *