በየአካባቢዉ ሰላም ለማስጠበቅ እየተሰራ ያለዉን በጎ ጅምር ቀጣይነት እንዲኖረዉ ለማድረግ የሚሊሻ ሰራዊት አደረጃጀት የበለጠ አጠናክሮ ለማስቀጠል እንደሚሰራ የጉራጌ ዞን ሚሊሻ ጽህፈት ቤት አስታወቀ።

ጽህፈት ቤቱ የ9 ወር እቅድ አፈጻጸምና በተለያዩ መመሪያዎች ላይ ግንዛቤ የማስጨበጫ መድረክ በወልቂጤ ከተማ አካሄዷል።

የሚሊሻ ሀይል በጥራትና በብቃት በማደራጀት በህብረተሰቡ ተሳትፎ በመመልመል፣አሰልጥኖና አደራጅቶ በማሰማራት በዞኑ በዘላቂነት ሰላምን ለማረጋገጥ በትኩረት እየተሰራ ነዉ።

መድረኩን በንግግር የከፈቱት የጉራጌ ዞን ሰላምና ጸጥታ መምሪያ ኃላፊ አቶ መስፍን ተካ እንዳሉት ባለፉት ጊዜያት የገጠሙንን ፈተናዎች በድል ለመወጣት ትልቁ ድርሻ የወሰደዉ የሚሊሻ ተቋም ነዉ።

በዚህም ህዝባዊ ሰራዊት በማደራጀት በመምራትና በማሰልጠን ሰፊ ስራዎች ሲሰራ መቆየቱም አስታዉቀዋል።

የሚሊሻ መዋቀር መልሶ የማጥራት የማደራጀትና የማሰልጠን ስራዎቻች በመስራት የአካባቢያችንን ሰላም በዘላቂነት ማረጋገጥ ይገባል ያሉት አቶ መስፍን ህዝብን በማደራጀት በዘርፉ ተጨባጭ ዉጤት ማምጣት ይገባል ብለዋል።

የጉራጌ ዞን ሚሊሻ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አብድልሀፊዝ ሁሴን እንዳሉት የተቋሙ ተልዕኮ ለማሳካት የሁሉም ባለድርሻ አካላት ቅንጅታዊ ስራ የበለጠ ማጠናከር ይገባል።

ከጸጥታ፣ከፖሊስና ከሌሎችም ሴክተር ጋር ተቀናጅቶ በመስራት ረገድ እየታየዉ ያለዉን መልካም ልምድ አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባም ገልፀዋል።

ዜጎች በሰላም ወጥተዉ በሰላም እንዲገቡ ለማድረግ በተሰራዉ የግንዛቤ ስራ ተጨባጭ ዉጤት ማምጣት እንደተቻለም አስረድተዉ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ዉስጥ 4መቶ 12 ሺህ 9 መቶ 20 የህብረተሰብ ክፍሎች በአካባቢ ጥበቃና በወቅታዊ የጸጥታ ጉዳዮች ላይ ግንዛቤ ተፈጥሯል።

የሚሊሻ አባላትን ከደንብ ልብስ አንጻር የሚስተዋሉ ክፍተቶች በቀጣይ ለመቅረፍ እንደሚሰራም ያመላከቱት አቶ አብድልሀፊዝ በቀጣይ የሚሊሻ አባላት በአዲስ የመመልመልና የማጥራት ስራ እንደሚሰራና ከሰዉ ሀይል ግንባታ ጋር ያሉ ችግሮችም ለመቅረፍ ጥረት ይደረጋል ብለዋል።

በዞኑ 5 ሺህ 9 መቶ 43 የሚሊሻ አባላቶች የደንብ ልብስ የሌላቸዉ እና በነጻ የሚያገለግሉ እንደሆነም አስታውሰው በቀጣይ አመት የደንብ ልብስ እንዲለብሱ ለማድረግ አጽዕኖት ሰጥተዉ እንደሚሰሩም አብራርተዋል።

ከቀበሌ እስከ ዞን ድረስ ያለዉን የሚሊሻ ስራዎችን ለማጠናከር የግንኙነት አግባብን በመፍጠር ይገባል ብለዉ በዘርፉ የተሰማሩ አካላቶች ልዩ ትኩረት ሰጥተዉ ሊሰሩበት እንደሚገባም ተናግረዋል።

በሀገር የህልዉና ዘመቻ በአራቱም ዙር 1 ሺህ 7 መቶ 31 ምልምሎችን መልምሎ ወደ መከላከያ ሰራዊት እንዲቀላቀሉ መደረጉም አስታዉሰዋል።

በመድረኩ የተገኙ አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች እንዳሉት የሰዉ ሀይል በተገቢዉ በማሟላት በዘርፉ የሚፈለገዉ ዉጤት እንዲመጣ ቅንጅታዊ ስራዉ የበለጠ አጠናክሮ በማስቀጠል የተያዙ እቅዶችን ማሳካት እንደሚገባም ገልፀዋል።

የሚሊሻ አባላቱ አቀናጅቶ በመምራት በየአካባቢዉ በዘላቂነት ሰላም እንዲሰፍን ለማድረግ ከመቼዉም ጊዜ በላይ በትኩረት ሊሰራበት እንደሚገባም አስረድተዋል።

የሚሊሻ አባላት በተለያዩ አደጋዎች ምክንያቶች የሚከፈለዉ የካሳ ክፍያ በመመሪያዉ የተቀመጠዉ ገንዘብ የሚያንስና መሻሻል እንዳለበትም ተሳታፊዎቹ ጠይቀዋል ሲል የዘገበዉ የጉራጌ ዞን መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነዉ።

= ኢትዮጵያን እናልማ፣የፈረሰውን እንገንባ፣ለፈተና እንዘጋጅ!

በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:-
https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36Cx!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *