በዞኑ የሚገኙ የአርሶአደሮች ፣ የወጣቶችና የሴቶችን አቅም በመጠቀም በግብርና ዘርፍ የሚፈለገዉን ዉጤት እንዲመጣ በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ የጉራጌ ዞን ግብርና መምሪያ አስታወቀ።

ጥቅምት 29/2015 ዓ.ም

በዞኑ የሚገኙ የአርሶአደሮች ፣ የወጣቶችና የሴቶችን አቅም በመጠቀም በግብርና ዘርፍ የሚፈለገዉን ዉጤት እንዲመጣ በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ የጉራጌ ዞን ግብርና መምሪያ አስታወቀ።

በጉራጌ ዞን በእኖር ወረዳ ገረንቦ ቀበሌ በሞዴል አርሶአደሮች፣ በሴቶችና በወጣቶች በኩታ ገጠም የለማ የጤፍ ማሳ ተጎብኝቷል።

የጉራጌ ዞን ግብርና መምሪያ ሀላፊ አቶ አበራ ወንድሙ እንዳሉት በዞኑ ከ38 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በ8 ወረዳዎችና በ135 ቀበሌዎች ፣ በ1ሺህ 2 መቶ ክላስተሮች ከ25 ሺህ ሄክታር በላይ ማሳ በኩታ ገጠም ማልማት ተችሏል።

አብዛኛዉ አርሶአደሮች ፣ሴቶችና ወጣቶች ተደራጅተዉ በሜካናይዜሽን በማረስ ተጠቃሚ እየሆኑ እንደሚገኙ አስታዉቀዋል።

በዞኑ 8 ወረዳዎች ላይ ኤቲአይ ያለባቸዉ ሲሆን በዚህም በስንዴና በጤፍ ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር የአርሶአደሩ ኢኮኖሚያዉ እድገት እንዲረጋገጥ እየሰራ እንደሆነም አስታዉቀዋል።

የአርሶአደሩ ችግርን መሰረት በማድረግ ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ በዞኑ የሚገኙ የአርሶአደሮች ፣ የወጣቶችና የሴቶችን አቅም በመጠቀም በግብርና ዘርፍ የሚፈለገዉን ዉጤት እንዲመጣ ከመቼዉም ጊዜ በላይ መሰራት አለበት ብለዋል።

በዘንድሮ አመት ከ148 ሺህ ሄክታር መሬት በላይ በመኽር እንደለማ ያስታወሱት ኃላፊው በዚህም 26 ፐርሰንትቱ በጤፍ እንዲሁም 25 ፐርሰንቱ በስንዴ ማሳ መሸፈኑም ተናግረዋል።

ከዚህ በፊት በዞኑ ከፌደራል እስከ ወረዳ ያሉ የስራ ኃላፊዎች የመስክ ጉብኝት መደረጉ ያስታወሱት አቶ አበራ አርሶአደሩን በተገቢዉ ከተደገፈ፣ ከግብርና ባለሙያተኞች የሚሰጣቸዉ ምክረ ሀሳብ ከተተገበረ፣አመራሩ በአግባቡ ካስተባበረ በግብርና ዘርፍ የሚፈለገዉን ዉጤት ይመጣል ብለዋል።

በጉብኝቱ የተገኙ የደቡብ ክልል የኤቲአይ አስተባባሪ አቶ የኋላእሸት አስጨናቂ እንዳሉት የግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቱትዩት (ኤቲአይ) የአርሶአደሩን ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ አርሶአደሩ የተሻለ ህይወት እንዲኖረዉ ለማድረግ እየሰራ ይገኛል።

በግብርና ስራዎች ያሉት ችግሮችንና ማነቆዎችን በመለየት የመፍትሄ አሳቦችን ለሚመለከተዉ አካል በማቅረብ፣ ፕሮጀክቶችን ቀርጾ ከግብርና ሴክተሮች በማስተሳሰር የግብርና ዘርፉ ለማዘመን ጥረት እየተደረገ እንደሆነም አስረድተዋል።

የእኖር ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ መብራቴ ተክሌ በጉብኝቱ ተገኝተዉ እንዳሉት እንደ ሀገር በተፈጠረዉ ዉስብስብ ችግር ምክንያት በግብርና ዘርፍ የሚፈለገዉን ዉጤት እንዳይመጣ የግብአት እጦት ፈተና ሆኖ መቆየቱ አስታዉሰዋል።

ከረሃብ ጋር የተጀመረዉን ጦርነት ለማሸነፍ በወረዳዉ በሁሉም አካባቢዎች የአርሶአደሩ ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ ሰፊ ስራዎች እየተሰራ እንደሆነም አመላክተዋል።

አቶ መብራቴ አክለውም በበልግና በመኸር እርሻ ከ11 ሺህ ሄክታር መሬት በላይ ማልማት መቻሉም አስታውሰው 75 ፐርሰንቱ ማሳ በኩታ ገጠምና በሜካናይዜሽን የተዘጋጀ እንደሆነም አስታዉቀዋል።

በዛሬዉ እለት የተጎበኘዉ የጤፍ ማሳ ጨምሮ በወረዳዉ በመኸር 3 ሺህ 1 መቶ ሄክታር መሬት በጤፍ ሰብል መሸፈኑም አብራርተዋል።

አርሶ አደር ዝያድ መካ እና ወጣት ጅላሉ ዱባም በገረንቦ ቀበሌ ጤፍን በኩታ ገጠም ያለሙ ናቸው።

በጋራ በሰጡት አስተያየትም በኩታ ገጠም ተደራጅተዉ በመስራታቸው ምርትና ምርታማነታቸዉ እንደጨመረላቸው ተናግረዋል።

በጉብኝቱም ከክልል ፣ከዞንና ከየወረዳዉ የተዉጣጡ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎችና የግብርና ባለሙያተኞች ሌሎችም ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል ሲል የዘገበዉ የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነዉ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *