በዞኑ የሚከናወኑ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ እንቅስቃሴዎች በተለያዩ የሚዲያ አማራጮች መረጃዎችን ተደራሽ እየተደረገ እንደሚገኝ የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ገለጸ።


መምሪያው የ2015 በጀት 3ኛ ሩብ አመት አፈጻጸም ከወረዳና ከተማ አስተዳደር መዋቅሮችና ከባለድርሻ አካላት የምክክር መድረክ በወልቂጤ ከተማ አካሂዷል ።

የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ኃላፊ አቶ ቅባቱ ተሰማ በወቅቱ እንደገለጹት በዞኑ የሚከናወኑ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ እንቅስቃሴዎች በተለያዩ የሚዲያ አማራጮች መረጃዎችን ተደራሽ እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል ።

የሚዲያ ቁሳቁስ እጥረት በወረዳዎችና በከተማ አስተዳደር መኖራቸውን ገልጸው ባላቸው አቅም የተለያዩ መረጃዎችን ለማህበረሰቡ ተደራሽ ለማድረግ እየተሰራ ያለው ስራ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት የገለጹት ኃላፊው ይህን ለማሟላት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በትኩረት ይሰራል ብለዋል።

አሁን ያጋጠሙ ችግሮችን በመለየት ለቀጣይ ጊዜያት በማስተካከል በመንግስትና በማህበረሰቡ መካከል የተሳለጠ መርጃ መስጠት እንደሚገባ ተናግረዋል ።

የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ምክትል ኃላፊ አቶ ሀዲሞ ሀሰን በበኩላቸው ጥራት ያለው ወቅታዊ መረጃ ተደራሽ ለማድረግ ዘመናዊ የሚዲያ ቁሳቁስ ወሳኝ በመሆኑ ይህን ለማሳካት የኮሚኒኬሽን አመራሩ የበኩሉን ጥረት ማድረግ ይጠበቅበታል ብለዋል።

ሁሉም ወረዳዎችና ከተማ አስተዳድሮች የኮሚኒኬሽን ተቋማት ከማህበራዊ ሚዲያ ባሻገር ወቅታዊና ጥራት ያላቸዉ መረጃዎችን በህትመት ሚዲያዎች ለማህበረሰቡ ተደራሽ የማድረጉ ተግባር አጠናክረው መቀጠልም እንዳለባቸው ገልጸዋል ።

ባለው ውስን የሚዲያ ቁሳቁስና የሰው ሀይል ስራዎችን በትኩረት በመስራት መረጃዎችን ተዳራሽ በማድረግ ያሉትን ተግዳሮቶች ለመፍታት በቅንጅት እንደሚሰሩም አቶ ሀዲሞ ተናግረዋል።

የምክክር መድረኩ ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት የተለያዩ የሚዲያ አማራጮችን በመጠቀም በወረዳና ከተሞች እየተሰሩ ያሉ በርካታ ስራዎችን ለማህበረሰቡ ይበልጥ ተደራሽ ለማድረግ የሚዲያ ቁሳቁስ አለመሟላት፣የበጀትእጥረት ማነቆ እየሆነባቸው እንደሆነ ገልፀው በቀጣይ የሚመለከታቸው አካላት በትኩረት ሊያግዙ እንደሚገባም ገልጸዋል ።

ዞኑ የራሱ የቴሌቪዥን ጣቢያ እንዲኖረው በትኩረት መሰራት አለበት ያሉት አስተያየት ሰጪዎቹ በየአካባቢያቸው ያሉ ስራዎችንና ወቅታዊ የሆኑ መረጃዎች ተደራሽ ለማድረግ በትኩረት እንደሚሰሩ ተናግረዋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *