በዞኑ የመጣው አንጻራዊ ሰላም በማጠናከር የህብረተሰቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በዘርፉ ይበልጥ በቅንጅት መስራት እንደሚገባ የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ አሳሰቡ።


የጉራጌ ዞን ፖሊስ መምሪያ የ2016 ዓ.ም የማህበረሰብ አቀፍ ወንጀል መከላከል ገለልተኛ አማካሪ ምክር ቤት ምስረታና የጸጥታው ምክር ቤት የጋራ የውይይት መድረክ በወልቂጤ ከተማ ተካሂዷል።

የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ በመድረኩ ተገኝተው እንዳሉት በዞኑ የጸጥታ ምክር ቤት በማቋቋም ሰላምና ጸጥታ ለማስጠበቅ በተከናወኑ ተግባራት አንጻራዊ ሰላም በማስፈን በሁሉም ዘርፎች አበረታች ተግባራት ማከናወን ተችላል።

የሀይማኖት አክራሪነትና ጽንፈኝነት፣ ህገወጥ የመሬት ወረራ፣ ኮንትሮባንድ የጸጥታ ስጋት መሆናቸውን ያነሱት አስተዳዳሪው የጸጥታው ምክር ቤት በዘርፉ በትኩረት መስራት ይኖርበታል ብለዋል።

በዞኑ የህብረተሰቡ ሰላምና ደህንነት ለማስጠበቅ የሚሊሻ አባላት ከማጠናከር ባለፈ ህብረተሰቡ ለሰላሙ ዘብ እንዲቆም በትኩረት መስራት እንደሚገባ አስረድተዋል።

የህብረተሰቡን ሰላምና ደህንነት ለማስጠበቅ የፖሊስና የሚሊሻ አባላት ለማጠናከር መስራቱን ገልጸው በዞኑ የመጣው አንጻራዊ ሰላም በማጠናከር የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትኩረት ይሰራል ነው ያሉት።

የጉራጌ ዞን ሰላምና ጸጥታ መምሪያ ኃላፊ አቶ የህያ ሱልጣን በበኩላቸው የዞኑ የጸጥታ ምክር ቤት ለሰላምና ጸጥታ ስጋት የሚሆኑ ጉዳዮችን በመለየት የህግ የበላይነት ለማረጋገጥ በትኩረት መስራት ይኖርበታል።

የህብረተሰቡን ሰላምና ደህንነት ለማረጋገጥ ሁሉም በዘርፉ ቅንጅታዊ አሰራር በማጠናከር መስራት እንዳለበትም አመላክተዋል።

የጉራጌ ዞን ፖሊስ አዛዥ ዋና ኢንስፔክተር ገና ደገሙ እንደገለጸት ማህበረሰብ አቀፍ ወንጀል መከላከል ገለልተኛ አማካሪ ምክር ቤት መመስረቱ ለህብረተሰቡ ውጤታማ አገልግሎት ለመስጠት ሚናው የላቀ ነው። ለዚህም ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን ማገዝ እንዳለባቸውም አንስተዋል።

ከዚህም ባለፈ ለማህበረሰቡ ግንዛቤ ከመስጠት ባለፈ አደረጃጀቶችን በማጠናከር የህብረተሰቡን ሰላምና ደህንነት ለማስጠበቅ እንደሚሰሩ ጠቁመዋል።

የፖሊስ አባላት ያለባቸውን የሰው ሀይል ውስነትና የግብአት እጥረት መቅረፍና ሟሟላት ይገባል ያሉት አቶ ገና ከዚህም ባለፈ የመርማሪ ፖሊስ ውስንነትና የአቅም ማነስ ላይ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ ገልጸዋል።

የመድረኩ ተሳታፊዎች እንዳሉት የልማትና የመልካም አስተዳደር ተግባራት በተገቢው ለማከናወን ሰላም ወሳኝ መሆኑን ገልጸው በዞኑ ሰላምና ጸጥታ በዘላቂነት ለማረጋገጥ የጸጥታ መዋቅሩ ማጠናከር ይገባል።

ከዚህም ባለፈ የጸጥታ መዋቅሩ ከህብረተሰቡ ተቀናጅቶ በመስራት የህብረተሰቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ መስራት ይኖርበታል ብለዋል።

በዞኑ የጸጥታ መዋቅሩ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት በተሰራው ስራ አንጻራዊ ሰላም ማስፈን መቻሉን ገልጸው ተግባሩ በቀጣይም ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ገልጸዋል።

በዞኑ የማህበረሰብ አቀፍ ወንጀል መከላከል ገለልተኛ አማካሪ ምክር ቤት መመስረት በዘርፉ የበለጠ ስራ ለመስራት ሚናው ከፍተኛ በመሆኑ ለዚህም ሁሉም እገዛ ሊያደርግ ይገባል ብለዋል።

በመድረኩም የጉራጌ ዞን ፖሊስ መምሪያ የማህበረሰብ አቀፍ ወንጀል መከላከል ገለልተኛ አማካሪ ምክር ቤት መመስረቱንም ተመልክቷል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *