በዞኑ እየጨመረ የመጣውን የወባ በሽታ ወረርሽኝ ለመከላከልና ለመቆጣጠር የድጋፍና ክትትል ስራዎች ተጠናክሮ ቀጥሏል።

በጉራጌ ዞን ጤና መምሪያ የወባ ወረርሽኝን ለመከላከልና ያሉትን ችግሮች ፈትቶ እንዲመጣ የተመደቡ ባለሙያዎች የድጋፍ ቡድን የደረሰበት ደረጃ ተገምግሟል፡፡

የድጋፍ ቡድኑ የሰራቸው ስራዎች፣ የወባ በሽታ ወረሽኝ ወቅታዊ ሁኔታና በቀጣይ ምን ምን ስራዎች መሰራት እንዳለባቸው ሰፊ ውይይት አካሄዷል።

በክትትልና ድጋፍ ወቅት ውስንነቶች የአጎበር አጠቃቀም ችግር፣ የአካባቢ ቁጥጥር ስራዎች ማህበረሰቡ ባሳተፈ መልኩ አለመስራት፣ ጤና ኬላዎች ክፍት አድርጎ አገልግሎት ያለመስጠት ፣ የግብአት አቅርቦት ጉድለቶችን መኖራቸውን ተመልክተዋል።

በዚህም የቤት ለቤት የቁጥጥርና ግንዛቤ የማስጨበጥ በቀጣይ በልዩ ትኩረት መሰራት ይኖርበታል ብለዋል።

የጉራጌ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ አየለ ፈቀደ ከሐምሌ ወር ጀምሮ እየጨመረ የመጣውን የወባ ወረርሽኝ ለመከላከልና ለመቆጣጠር ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ ቢሆንም የመቀነስ አዝማሚያ አልታየበትም።

በመሆኑም የወባ በሽታ ወረሽኝ ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚደረጉ የድጋፍና ክትትልና የንቅናቄ ስራዎች እስከ ልማት ቡድን ድረስ በማጠናከር የመከላከሉ ስራ ማህበረሰቡ በባለቤትነት እንዲመራ ኃላፊነት መስጠት እንደሚገባ አሳስበዋል።

በተለይ የወባ በሽታ ተጋላጭ የሆኑ ወረዳዎች እና ቀበሌዎች በልዩ ሁኔታ በመደገፍ ወረርሽኙ ለመከላከልና ለመቆጣጠር ጥረት እንደሚደረግ ገልጸዋል።

በመጨረሻም የመምሪያው ኃላፊ አቶ አየለ ፈቀደ በየጊዜው እየጨመረ የሚመጣው የወባ ወረሽኝ በተገቢው ለመቆጣጠር ህብረተሰቡ በማነቃነቅ ውሃ ያቆሩ አካባቢዎች በማዳፈንና በማፋሰስ፣ የአጎበር አጠቃቀምና ተያያዥ ጉዳዮች በዘመቻ መፈጸም ይገባል።

መረጃው የጉራጌ ዞን ጤና መምሪያ ነው

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *