በዞኑ በ9 ወሩ የተሰሩ የልማት እና የመልካም አስተዳደር ስራዎች አጠናክሮ በማስቀጥል በቀጣይ ባልተሰሩ ቀሪ ተግባራት ላይ በትኩረት መስራት እንደሚገባ ተገለጸ።


የጉራጌ ዞን የካቢኔ አባላት የ2016 ዓ.ም የ9 ወር እቅድ አፈጻጸም በዛሬው እለት የገመገሙ ሲሆን በቀጣይ በሚሰሩ ስራዎች ላይም አቅጣጫ አስቀምጧል።

በዚህም በ2016 ዓ.ም በግብርና፣በመንገድ፣በውሃ፣በጤና፣ በስራ እድል ፈጠራ፣በሰላምና ጸጥታ እና በሌሎችም የስራ መስኮች በርካታ ስራዎች ሲሰሩ እንደነበር እና አመርቂ ውጤቶች መታየታቸው ተገልጿል።

ለአብነትም በግብርና ዘርፉ በተሰሩ የልማት ስራዎች የኑሮ ውድነቱ እንዲረጋጋ የተሰሩ ተግባራት የሚበረታቱ መሆኑን እና በሰላምና ጸጥታ በተሰራው ስራ ደግሞ በዞኑ አንጻራዊ ሰላም መታዩቱ ተመላክቷል።

የበጋ መስኖ ስንዴ፣40-30-40 የፍራፍሬ መንደር፣የሌማት ትሩፋት ስራዎች በአጠቃላይ በጥምር ግብርና ስራዎች ላይ የተሰሩ ስራዎች የህብረተሰቡን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ አድርገዋል።

በትምህርት ዘርፍ ደግሞ የተማሪዎች ውጤት እንዲሻሻል ህብረተሰቡንና መንግስት በጋራ በመቀናጀት እየተሰራ ያለው የመጽሀፍት ህትመት ስራ እና የጉራጊኛ ቋንቋ በተመረጡ በ1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መጀመሩ የሚበረታታ ተግባር መሆኑ ተጠቅሷል።

በዞኑ አንድ አንድ አካባቢዎች በተለይ በወልቂጤ ከተማ የታየው አንጻራዊ ሰላም አጠናክሮ ማስቀጠልና የስጋት አካባቢዎች ላይ ልዩ ትኩረት በመስጠት የህብረተሰቡ የአካባቢው ሰላም እንዲጠበቅ መስራት እንደሚገባ ተመላክቷል።

በመንገድ ዘርፍ ህብረተሰቡንና መንግስት በመቀናጀት እየተሰሩ ያሉ የመንገድ ስራዎች የህብረተሰቡን ጊዜ፣ጉልበትና ገንዘብ በመቆጠብ ተጠቃሚነቱ ይበልጥ እንዲረጋገጥ እያደረገ በመሆኑ በትራንስፖርት ዘርፍ የተጀማመሩ ስራዎችን በማጠናከር በዘርፉ የሚታዩ ችግሮችን ማረም እንደሚገባ ተገልጿል።

የተጀማመሩ የውሃ ፕሮጀክቶች እንዲጠናቀቁ በማድረግ ህብረተሰቡ የንጹህ መጠጥ ውሃ ተጠቃሚ እንዲሆን መስራት እንዲሁም በጤናው ዘርፍ የእናቶችና ህጻናት ሞት እንዲቀንስ እና በጤና ተቋማት የመድሀኒት እጥረት እንዳይስተዋል በትኩረት መስራት ያስፈልጋል ተብሏል።

በሌሎች በወጣቶች የበጎ ፍቃድ አገልግሎቶች፣በሴቶች ተጠቃሚነት፣ በባህልና ቱሪዝም፣በኢንቨስትመንት፣በገቢ አሰባሰብ፣በወጣቶች ስራ አድል ፈጠራ፣በሳይንስና ቴክኖሎጂ ዘርፍ እና በሌሎችም የተጀማመሩ አበረታች ስራዎችን አጠናክሮ ማስቀጠልና ከዚህ በፊት ይገጥሙ የነበሩ ችግሮችን በመለየት በአመቱ የታቀዱ እቅዶች በቀጣይ ተፈጻሚ እንዲሆኑ በትኩረት መስራት ያስፈልጋል ነው የተባለው።

በቀጣይ ያልታረሱ መሬቶች እንዲታረሱ ማድረግ፣የገቢ አቅማችን ማሳደግ ፣የተማሪዎች ውጤት እንዲሻሻል የተጀመረው የማጠናከሪያ ትምህርት ማስቀጠል፣የተጀማመሩ የመንገድ፣የውሃ ፕሮጀክት ስራዎች እንዲጠናቀቁ ማድረግ፣በከተሞች የሚሰሩ የመሰረተ ልማት እንቅስቃሴዎች ማጠናከርና፣ለወጣቶች የስራ እድል እንዲፈጠር በማድረግ በሌሎችም በሁሉም ዘርፎች ላይ በትኩረት እንደሰራባቸው ተጠቁሟል።

ባለፉ ዘጠኝ ወራት ውስጥ የተሰሩ አበረታች የልማት እና የመልካም አስተዳደር ስራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉና ባልተሰሩ እንዲሁም ያጋጠሙ ችግሮች በመለየት የህብረተሰቡ ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ያስፈልጋል ተብሏል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *