በዞኑ በፓርቲ መሪነት ህብረተሰቡን በማሳተፍ በሁሉም ዘርፎች የተከናወኑ አበረታች ተግባራት በማጠናከር የህብረተሰቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እንደሚሰራ የጉራጌ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት አስታወቀ።


የጉራጌ ዞን ብልጽግና ፓርቲ የ2016 ዓ.ም የፓርቲ ስራዎች አፈጻጸም በወልቂጤ ከተማ ገምግሟል።

የጉራጌ ዞን የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ክብሩ ፈቀደ በመክፈቻ ንግግራቸው በዞኑ በፓርቲው መሪነት የፓርቲና የመንግስት አደረጃጀት በማቀናጀት በሁሉም ዘርፎች ሞዴል የሆኑ ተግባራት በማከናወን ህብረተሰቡ ተጠቃሚ ማድረግ ተችላል።

በተለይም ህብረተሰቡን በማስተባበር በትምህርት፣ በግብርና፣ በመንገድ ብሎም የኑሮ ውድነትን ለመቀነስ የሰንበት ገበያዎችን በማቋቃምና በማጠናከር፣ በስራ ዕድል ፈጠራ አበረታች ተግባራት ማከናወን መቻሉን ጠቁመዋል።

እንደ አቶ ክብሩ ፈቀደ ገለጻ የድጋፍና ክትትል ስራዎችና የአሰራርና የአደረጃጀት መመሪያ ተከትሎ በመሰራቱ ጠንካራ ተቋማዊ አሰራር እውን ማድረግ ተችላል ብለዋል።

በዞኑ ፓርቲ ጽህፈት ቤት እስካሁን የተከናወኑ አበረታች ተግባራት በማጠናከርና የነበሩ ጉድለቶችን በማረም በቀጣይ የህብረተሰቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ይበልጥ ለማረጋገጥ መስራት ይገባል ብለዋል።

በዞኑ የሰላምና ጸጥታ ስጋት ሊሆኑ የሚችሉ ጉዳዮችን ለይቶ በማቀድ በቀጣይ በትኩረት መስራት ይገባል ብለዋል።

የዞኑ ብልጽግና ፓርቲ የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አለማየሁ ገብረመስቀል በበኩላቸው በዞኑ የአመራሩና የአባላት አንድነት በማጠናከር በሁሉም ዘርፍ የተሰሩ ስራዎች በቀጣይም ማጠናከር ይገባል።

ከዚህ በበለጠ ለመፈጸም የአመራሩ የማስፈጸም አቅም ወጥ አለመሆን፣ ያሉ ጸጋዎች በተገቢው ለይቶ አለመጠቀም፣ የተሰሩ ስራዎች ለይቶ ቀምሮ አለማስፋትና በሚዲያ አለማጀብ እንደ ጉድለት አንስተዋል።

አመራሩና አባላሉ በተናበበ መንገድ በቀጣይ ተሞክሮ የሚቀመርበት ስራ ይበልጥ መስራት እንደሚገባ ገልጸዋል።

የዞኑ ፓርቲ ጽህፈት ቤት አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ ወይዘሮ አመተሩፍ ሁሴን እንደገለጹት በበጀት አመቱ የአመራሩና የአባላት የአስተሳሰብና የአመለካከት አንድነት በማጠናከር ውጤታማ ተግባራት ማከናወን ተችላል።

ይህም አመራሩ የተሰጠውን ተልዕኮ በተገቢው ተቀብሎ በመፈጸሙና ጠንካራ የፓርቲ ተቋም ለመገንባት በተሰራው ስራ መሆኑን ነው ብለዋል።

የመድረኩ ተሳታፊዎች እንዳሉት በዞኑ በበጀት አመቱ የተሻለ ስራ ማከናወን መቻሉና በቀጣይም አመራሩ የህብረተሰቡንና የአባላቱን አቅም በተገቢው በማቀናጀት የፓርቲው ግብና እሳቤ ለማሳካት በትኩረት መስራት ይኖርበታል ብለዋል።

በ2016 የተከናወኑ የተሻሉ ተግባራት በማጠናከርና የነበሩ ጉድለቶችን በማረም በቀጣይ በትኩረት እንደሚሰሩ ገልጸዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *