ፅ/ቤቱ በ2014 በጀት አመት 1 ቢሊየን 6 መቶ 80 ሚሊየን ብር ለመሰብሰብ መታቀዱንም አመላክቷል።
የጉራጌ ዞን ገቢዎች ባለስልጣን ዋና ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ሚነወር ሃያቱ እንደገለጹት በበጀት አመቱ በመጀመሪያ ሩብ አመት ከመደበኛና ከማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት 408 ሚሊየን 3 መቶ 75 ሺህ ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ 392 ሚሊየን 973 ሺህ 9 መቶ 25 ብር መሰብሰብ መቻሉን ገልፀዋል።
በበጀት አመቱ 23 ሺህ 426 የደረጃ ‘ሐ’ ግብር ከፍዮች መኖራቸውን የጠቆሙት አቶ ሚነወር 23 ሺህ 240 ግብር ከፍዮች ግብርና ታክሳቸውን አሳውቀው የከፈሉ ሲሆን ከነዚህም 62 ሚሊየን 830 ሺህ 4 መቶ 42 ብር መሰብሰቡን ገልፀዋል።
በዞኑ 907 የደረጃ ‘ለ’ ግብር ከፍዮች ያሉ ሲሆን 898 ግብር ከፋዮች በመክፈላቸው 6 ሚሊየን 566 ሺህ 6 መቶ 26 ብር መሰብሰብ መቻሉ ተናግዋል።
አያይዘውም በበጀት አመቱ 1ሺህ 577 የደረጃ ‘ሀ’ ግብር ግብር ከፍዮች መኖራቸውን ያነሱት ኃላፊው ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ጀምሮ 227 ግብር ከፍዮች ግብርና ታክስ ሲከፍሉ ከነዚህም 994 ሺህ 71 ብር መሰብሰቡንም ተናግረዋል።
እንደ ሃላፊው ገለፃ ማህበረሰቡ ግብርን በወቅቱ እንዲከፍል በተለያዩ አማራጮች ግንዛቤ የመስጠት ስራ በትኩረት መሰራቱንም አክለው ተናግረዋል።
የታክስ መሰረት ከማስፋት አንፃር የንግዱ ማህበረሰብ ወደ ግብር ስርአቱ ከማስገባት አንፃር 1 ሺህ 105 አዳዲስ ነጋዴዎች ወደ ግብር ማዕቀፍ እንዲገቡ ተደርጓል ብለዋል።
ታክስ የሚሰውሩ አካላት ላይ ክትትል በማድረግ ህጋዊ እርምጃ እየተወሰደባቸው እንደሆነም አመልክቷል ።
ፅ/ቤቱ የታክስ ስርአቱ ለማዘመን በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝም ገልፀዋል።
አቶ ሚነወር አክለውም የውስጥ ገቢን አማጦ ለመሰብሰብ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት በመሰራቱ የተሻለ ውጤት እንደተመዘገበ ጠቁመው ከማዘጋጃ ቤታዊ አንፃር የተሰበሰበው ገቢ ውስንነት መኖሩንና በቀጣይ አሟጦ ለመሰብሰብ በመቀናጀት መሰራት እንዳለበትም ጠቁመዋል።
አቶ መሀመድ ኩምሳና በድሩ ናስር የወልቂጤ ከተማ ነዋሪዎች ሲሆኑ በጋራ በሰጡ አስተያየት ግብር ከፋዩ ማህበረሰብ ግብር በወቅቱ በመክፈል ካላስፈላጊ ቅጣት መዳን አለበት ብለዋል።
በወቅቱ ግንዛቤ አግኝተው ግብርና ታክሳቸውን መክፈላቸውን የገለፁት ነዋሪዎቹ ህብረተሰቡ ግብርን በወቅቱ በመክፈል የሀገር ኢኮኖሚ ለማሳደግና ያልተሟሉ መሰረተ ልማቶች እንዲማሉ ለማድረግ የበኩሉን ድርሻ መወጣት አለበት ብለዋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።
በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36Cx