በዞኑ በህብረተሰቡና በባለሀብቱ የተሰሩ የመንገድ ልማት ስራዎች ህዝብ ከተነቃነቀ ሁሉም ልማት ማሳካት እንደሚቻል ማሳያ ናቸው ሲሉ የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ ገለጹ።


በጉራጌ ዞን በተለያዩ ወረዳዎች በህብረተሰቡ እና በባለሀብቱ ትብብር የተሰሩ የመንገድ ልማት ስራዎች የጉራጌ ዞን ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችና የመምሪያ ባለሙያዎች በተገኙበት የመስክ ምልከታ ተደርጓል።

በዞኑ የተሰሩ የመንገድ ልማት ስራዎች ከዚህ በፊት በህብረተሰቡ ይደርስ የነበረው እንግልት እና አደጋ ከማስቀረት በተጨማሪ የማህበረሰቡ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ እና የህዝቡ የእርስ በርስ ግንኙነት እንዲጎለብት አድርገዋል።

የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ እንደገለጹት በመንግስ፣ በህብረተሰቡና በባለሀብቱ የተሰሩ የመንገድ ስራዎች የድሮ የአባቶች አሻራ ያስቀጠሉና የህብረተሰቡ የልማት ተነሳሽነት ያስመሰከሩ ናቸው ብለዋል።
ይህ የመንገድ ንቅናቄ አጠናክሮ በማስቀጠል በቀጣይ አመት በዞኑ ያሉ ቀበሌዎችን እርስ በርስ የማገናኘት ስራ ላይ በትኩረት እንደሚሰራ አስታውቀዋል።

በአሁን ሰአት በዞኑ የመንገድ ተደራሽነት በመስፋፋቱ የተነሳ አርሶ አደሩ ምርቱን በቀላሉ ወደ ገበያ እንዲያወጣ እድል በማግኘቱ ያልታረሱ መሬቶችን በማረስ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚ እየሆነ እንደሚገኝ ተናግሯል።

በዛሬው እለት በእኖር፣በእኖር ኤነር መገርና በጉመር ወረዳ በህብረተሰቡ የተሰሩ ስራዎች እጅግ የሚደነቁ ናቸው ያሉት አቶ ላጫ ህዝብ ከተነቃነቀ ሁሉም ነገር ማሳካት እንደሚቻል በዞኑ በህብረተሰቡና በባለሀብቱ የተሰሩ የመንገድ ልማት ስራዎች ማሳያ ናቸው ብለዋል።

የጉራጌ ዞን ትራንስፖርት እና መንገድ ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ ሙራድ ከድር በበኩላቸው በ2016 በጀት አመት ሁሉም መዋቅሮች ለመንገድ ልማት ስራ በጀት እንዲያሲዙ በማድረግ እና እቅድ አቅዶ ንቅናቄ በመፈጠሩ በመንገድ ልማቱ እጅግ አስደናቂ ስራዎች ተሰርቷል ነው ያሉት።

በዚህም ከ2መቶ 77 ሚሊየን ብር በላይ በማሰባሰብ 2መቶ 92 ኪሎ ሜትር የአፈር ስራ የተሰራ ሲሆን 2መቶ 43 ኪሎ ሜትር መንገድ ጠጠር በማልበስ ለትራፊክ ክፍት መደረጉ አስታውቀዋል።

አቶ ሙራድ አክለውም 1መቶ 3 እስትራክቸርና በርካታ ድልድዮች የተሰሩ ሲሆን የተጀመሩ ስራዎችን በማጠናከር በቀጣይ በዞኑ ሁሉም ቀበሌዎች ከዋና መንገዶች ለማገናኘት በትኩረት እንደሚሰራ አመላክተዋል።

የተሰሩ መንገዶች እንደዳይበላሹ ህብረተሰቡ አስፈላጊውን ጥበቃ ማድረግ ያስፈልጋል ያሉት አቶ ሙራድ የአረፋና የመስቀል በዓላት ተጠቅሞ የሚሰራው የመንገድ ልማት ሀብት ማሰባሰብ ተግባር ተጠናክሮ እንዲቀጥል አሳስበዋል።

በእኖር፣በጉመር እና በእኖር ኤነር መገር ወረዳ የተሰሩ የመንገድ ልማት ስራዎች አይቻሉም የተባሉ ግን በህብረተሰቡና በመንግስት ቅንጅትና ቁርጠኝነት የተደፈሩ መሆናቸው አስገንዝበዋል።

የጉራጌ ዞን ምክር ቤት የኢኮኖሚ ዘርፍ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ኑር አህመድ አለዊ በዞናችን በህብረተሰቡና በባለሀብቱ የተሰሩ የመንገድ ልማት ስራዎች የህብረተሰቡን የልማትና የመልካም አስተዳር ጥያቄዎች የመለሱ ናቸው ብለዋል።

የመንገድ ልማት ስራው በሁሉም ወረዳዎች አበረታች ነው ያሉት አቶ ኑር አህመድ ህብረተሰቡ፣ባለሀብቱ እና መንግስት በመቀናጀት እየተሰሩ ያሉ ስራዎች አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ ጠቁመዋል።

በእኖር፣በጉመር እና በእኖር ኤነር መገር ወረዳ አግኝተን ያነጋገርናቸው የህብረተሰብ ክፍሎች እንደገለፁት ከዚህ በፊት መንገድ ባለመኖሩ ማህበራዊ እንቅስቃሴያችን የተገደበ እና ለብዙ እንግልት እንዳረግ ነበር ብለዋል።

ይህንን ችግር ለመቅረፍ ቆርጠን በመነሳት የህዝብ ለህዝብ ግንኙነታችን እንዲጨምር፣ በማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና በሁሉም ዘርፍ ጠተቃሚ እንድንሆን አስችሎናል ሲሉ ገልጸዋል።

በቀጣይም የተሰሩ መንገዶች መንከባከብ፣ቀሪ ያልተሰሩ ካሉ በመስራት ለመንገድ ስራ የጀመርነው ተግባር አጠናክረን እናስቀጥላለን ብለዋል ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *