በዞኑ በህብረተሰቡና በመንግስት ትብብር ከ4 መቶ 93 ሚሊየን ብር በላይ በሚሆን ወጪ የትምህርት ልማት ስራዎች መሰረታቸው የጉራጌ ዞን ትምህርት መምሪያ ገለጸ።


የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ በአካባቢው ማህበረሰብና ተወላጅ ባለሀብቶች ከ22 ሚሊዮን 4መቶ ሺ ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገነባውን የዋድዬ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ጎብኝተዋል።

የምክር ቤቱ አባላት የ2016 በጀት አመት መጠናቀቅን አስመልክቶ በጉራጌ ዞን የተለያዩ የልማት ስራዎችን መጎብኘታቸው ይታወቃል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ ወ/ሮ መነቴ ሙንዲኖ የህዝብ ወኪሎች ወረቀት ላይ ሪፖርትን ከመገምገም ባለፈ ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ አይተው እንዲገመግሙ አላማ ያደረገ መሆኑን አስታውቀዋል።

በጉራጌ ዞን በህብረተሰቡና በመንግስት የጋራ ትብብር የተሰሩ የትምህርት ልማት ስራዎች ለሌሎችም አራያ የሚሆን ነው ብለዋል።

ወ/ሮ መነቴ አክለውም በዞኑ በማህበረሰቡ እና በመንግስት ቅንጅት የተሰሩ ስራዎች በሁሉም ዘርፎች እና በሁሉም አካባቢዎች አጠንክረን ከሰራን ሀገራችን ከድህነት የምናወጣበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም ነው ያሉት።

ትምህርት ቤቱ ሙሉ የትምህርት ግብአት የተሟላለት ሲሆን የተማሪዎች ውጤት እንዲሻሻል ያደርጋል ያሉት ምክትል አፈ ጉባኤዋ በዞኑ በጋራ እየተሰሩ ያሉ የልማት ስራዎች አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ መክረዋል።

የክልሉ ትምህርት ቢሮ ምክትል እና ኃላፊ አቶ ሳሙኤል ወ/ሚካኤል በክልሉ ትምህርት ለትውልድ በተደረገው ንቅናቄ ህብረተሰቡን በማሳተፍ ከ1 ነጥብ 1 ቢሊየን ብር በላይ ለትምህርት ልማት ስራ ተሰብስቧል።

በክልሉ ለመጽሀፍት ህትመት ስራ ከ6መቶ ሚሊየን ብር በላይ ለማሰባሰብ በተደረገው ጥረት ጉራጌ ዞን ከክልሉ ሞዴል ስራ ሰርቷል ያሉት አቶ ሳሙኤል በእዣ ወረዳ የሚገኘው የዋድየ ትምህርት ቤት ደግሞ የዚሁ ውጤት መሆኑን ገልጸዋል።

ህብረተሰቡ ደግሞ በጉልበት፣በገንዘብና በቁሳቁስ እያደረገ ያለው የትምህርት ልማት እንቅስቃሴ ለትምህርት ውጤት መሻሻል ተስፋ የሰነቀ ነው ሲሉ አብራርቷል።

የጉራጌ ዞን ትምህርት መምሪያ ሃላፊ አቶ መብራቴ ወልደ ማሪያም እንዳሉት በዞኑ ማህበረሰብ ሁለንተናዊ ተሳትፎ ፣የህዝቡን የገንዘብ፣የቁሳቁስ እና የጉለበት አቅም በመጠቀም ለትምህርት ውጤት መሻሻል በትኩረት እየተሰራ መሆኑን አስገንዝበዋል።

በመሆኑም በአመቱ በህብረተሰቡና በመንግስት ትብብር ከ4 መቶ 93 ሚሊየን ብር በላይ በሚሆን ወጪ የትምህርት ልማት ስራዎች መሰረታቸው ተናግሯል።

በዚህም አዳዲስ የመደበኛና ቅድመ መደበኛ የመማሪያ ክፍሎች፣ቤተሙከራዎች፣ቤተመፅሀፍቶች ግንባታና ጥገናዎች የአጥር፣የመጸዳጃ ቤቶች ግንባታና ሌሎችም ተግባራት ተከናዉኗል ያሁት አቶ መብራቴ የኮምፒውተር ፣የወንበር፣የመጽሀፍት ህትመት እና ሌሎች ስራዎች መሰራታቸው ገልፀው የዋድዬ 2ኛ ደረጃ ትም/ቤት አንዱ ማሳያ ነው ብለዋል ።

የእዣ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዘውዱ ዱላ በበኩላቸው ወረዳው ለትምህርት ውጤት መሻሻል ከበጎ አድራጊ ድርጅቶች፣ከማህበረሰቡ እና ከባለሀብቱ በመቀናጀት በርካታ ስራዎች መከናወናቸው ተናግሯል።

በዚህም በበጀት አመቱ ለትምህርት ልማት ስራ ብቻ ከ62 ሚሊየን ብር በላይ ሀብት ማሰባሰብ የተቻለ ሲሆን ተግባሩ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አመላክተዋል።

ዛሬ የተጎበኘው የዋዲዬ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አጠቃላይ ከ26 ሚሊየን 4መቶ ሺ ብር በላይ የፈጀ ሲሆን ሙሉ የመማሪያ ግብአት ለአብነትም አማራጭ ቴክኖሎጂዎች፣ዘመናዊ መጸዳጃ ቤቶችና ሻወር ቤት፣ላይብረሪ እንዲሁም ኮምፒውተር እና ሌሎችም የተሟሉሉት መሆኑን የትምህርት ውጤት መሻሻል ላይ ከፍተኛ ሚና እንዳለው አቶ ዘውዱ ገልጸዋል።

በመጨረሻም የምክር ቤቱ አባላት በትምህርት ቤቱ ግቢ የችግኝ ተከላ አካሂደዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *