በዘንድሮ የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት በአዲስና በጥገና 3መቶ 74 ቤቶች መሰራታቸው የጉራጌ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ ገለጸ

ነሀሴ 17/2014

በዘንድሮ የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት በአዲስና በጥገና 3መቶ 74 ቤቶች መሰራታቸው የጉራጌ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ ገለጸ።

በጎ ፈቃደኛነት ያለ ውጫዊ ጫና በራስ ተነሳሽነት በጎ ስራዎች መስራት ሲሆን የደጋግና ቅን ልቦች ችሮታ የሚሹ ወገኖች ከስቃያቸው የሚያርፉበት÷ በጎ አድራጊውም የህሊና እርካታ የሚያገኝበት ተግባር ነው።
በጎ አድራጎት ከልብ በመነጨ መሻት፤ ከበጎ ህሊና የሚመነጭ ፣ በፈቃደኝነት አቅም የሚችለውን ሁሉ ለሌሎች የማጋራት ፣ ራስንና የራስን የመስጠት መገለጫ ነው።

በጎ ፈቃደኞች ከማንም ምንም አቻም ይሁን ብልጫ ምላሽን ሳይጠብቁ በውስጥ መሻታቸው ለህሊና እርካታቸው ለወገናቸው አለን የሚሉ ናቸው።

ይህንን የበጎ ተግባር እሳቤ እያደገ መምጣቱን ተከትሎ የጉራጌ ዞን ወጣቶች በክረምትና በበጋ ወቅቶች የኢኮኖሚ አቅም ለሌላቸው ወገኖች በተለያዩ የበጎ ተግባራት ተጠቃሚ እያደረጉ ይገኛሉ።

በጉራጌ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ የወጣቶች ዘርፍ ኃላፊ አቶ አብዶ ድንቁ እንዳሉት በክረምትና በበጋ ወቅቶች በሚሰሩ የበጎ አድራጎት ስራዎች በርካታ አቅም የሌላቸው የማህበረሰብ ክፍሎች ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል።

በ2014 ዓ.ም በዞኑ በተሰሩ የክረምት የበጎ ፍቃድ አገልግሎት በአዲስና በጥገና 3መቶ 74 ቤቶች መሰራታቸው ገልጸዋል።

እንደ አቶ አብዶ ገለፃ በደም እጦት ምክንያት የወገኖቻችን ህይወት እንዳያልፍ በዞኑ 1ሺ3 መቶ4 ዩኒት ደም ተለግሷል።
በክረምት የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ትኩረት ከሚሰጣቸው ተግባራት ሌላኛው የአካባቢን ስነምህዳር በማስጠበቅ ምቹና ተስማሚ የአየር ንብረት እንዲኖር በዞኑ 28 ነጥብ 1 ሚሊየን ችግኝ መትከል እንደተቻለ ኃላፊው አስታውቀዋል፡፡

በዚህ በክረምት የበጎ አድራጎት ተግባራት የአካባቢ ጽዳትና ውበት፣ የሰላም እሴት ግንባታ፣ የማጠናከርያ ትምህርት ፣ የእርሻ ስራ፣ የደም ልገሳና ሌሎች ተግባራት እየተከናወኑ ሲሆን 196 ሺህ 768 ወጣቶች ተሳትፈዋል ነው ያሉት።

በዚህ በጎ ተግባር 593 ሺህ 324 የህብረተሰብ ክፍሎች ተጠቃሚ ማድረግ እንደተቻለ አቶ አብዶ ተናግረዋል።

ይህ ደግሞ በመንግስትና በህብረተሰብ ይወጣ የነበረውን 162 ሚሊየን 332ሺ 321 ብር ማዳን ተችሏል ብለዋል።

በ16ቱ ዘርፎች ህብረተሰቡ ተጠቃሚ የሚያደርጉ ስራዎች ቀጣይም ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።

መረጃዎቻችበተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub:- https://youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36CxQ
Twitter:- https://4pvf.short.gy/bTJNNn

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *