በዘንድሮ የመኸር እርሻ 7 ሺህ 4 መቶ 14.5 ሄ/ር ማሳ በዘር መሸፈን መቻሉን በጉራጌ ዞን የደቡብ ሶዶ ወረዳ ግብርና ፅ/ቤት አስታወቀ፡፡

ነሐሴ 14/2014 ዓ.ም

በዘንድሮ የመኸር እርሻ 7 ሺህ 4 መቶ 14.5 ሄ/ር ማሳ በዘር መሸፈን መቻሉን በጉራጌ ዞን የደቡብ ሶዶ ወረዳ ግብርና ፅ/ቤት አስታወቀ፡፡

የደቡብ ሶዶ ወረዳ ግብርና ፅ/ቤት በዘንድሮ የመኸር እርሻ 7 ሺህ 2 መቶ 92 ሄ/ር ማሳ በዘር ለመሸፈን በማቀድ 7 ሺህ 4 መቶ 14.5 ሄ/ር በመፈፀም የተጣለው ግብ ማሳካት መቻሉን አስታውቋል፡፡

በዚህም ከ3 መቶ 11 ሺህ ኩ/ል በላይ ምርት እንደሚጠበቅም ተመላክቷል፡፡

በዘንድሮ የነበረን ምቹ የአየር ንብረት ለመኸር እርሻ ተግባሩ መልካም አጋጣሚ ነበር ያሉት የወረዳው ግብርና ጽ/ቤት ም/ኃላፊና የእርሻ ዘርፍ ኃላፊ አቶ መኮንን ካሳ፤ እንደ ወረዳ በበልግ አጥተናቸው የነበሩ የእርሻ ልማት ስራዎች በመኸር ማካካስ ችለናል ሲሉም ተናግረዋል፡፡

የዘር ሽፋኑ ከታቀደው በላይ ማሳካት መቻሉን የጠቀሱት አቶ መኮንን፤ በዚህ መኸር ተግባርም NPS 6 ሺህ 4 መቶ 41.5 ኩ/ል እንዲሁም ዩሪያ በእስካሁኑ አፈጻጸም 1 ሺህ 6 ኩ/ል ጥቅም ላይ መዋሉን ተናግረው፤ ከዩሪያ አፈጻጸም አንጻር በቀጣይ ቀሪ የመኸር ስራዎች በቶፕ-ድሬስ የሚሰጥ መሆኑም ተናግረዋል፡፡

ም/ኃላፊው አክለውም፤ ከቴክኖሎጂ አጠቃቀም እና ትግበራ አንጻር በትኩረት ሲሰራ እንደነበር ተናግረው፤ በዘር ከተሸፈነው ጠቅላላ ማሳ ውስጥ 4 ሺህ 1 መቶ 94 ሄ/ር ማሳ በመስመር መዘራቱን ጠቅሰው፤ በሁለት ሰብሎች ማለትም በስንዴ 1 ሺህ 7 መቶ 20 ሄ/ር ለማልማት ከታቀደው 8 መቶ 50 ሄ/ር በ17 ክላስተር በኩታ ገጠም ማልማት መቻሉን ያመላከቱ ሲሆን፤ በጤፍ ጠቅላላ ከለማው 3 ሺህ 4 መቶ 86.5 ሄ/ር ውስጥ 1 ሺህ 8 መቶ 70 ሄ/ር በክላስተር ማልማት መቻሉንም ገልጸዋል፡፡

በዘንድሮ የመኸር እርሻ ተግባር በፍራፍሬ ልማት አመርቂ ስራዎች የተሰሩ ሲሆን፤ በመደበኛ እና በ30-40-30 በድምሩ 45 ሺህ ለማልማት በማቀድ በመደበኛ ከ13 ሺህ 1 መቶ በላይ እንዲሁም በ30-40-30 ከ20 ሺህ በላይ በድምሩ 34 ሺህ 8 መቶ 30 የፍራፍሬ ችግኞች ማልማት መቻሉንም አቶ መኮንን ጠቅሰዋል፡፡

የፍራፍሬ ልማት ስራው በአርሶ አደሩ ዘንድ እያደገ የሚመጣ ሌላኛው አዋጭ ዘርፍ መሆኑን ያመላከቱት አቶ መኮንን፤በዘንድሮ መኸር እርሻ ብቻ ከመንግስት 6 ሺህ የሙዝ ተክል፤ከግሊመር ኦፍ ሆፕ እንዲሁም ከፋርም አፍሪካ የአቮካዶ እና አፕል የተክል ችግኞች መቅረባቸው መልካም አጋጣሚዎች እንደነበሩ ጠቅሰው፤ በቀጣይም የእንክብካቤ ስራዎችን በማጠናከር ሊሰራ እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡

ከዚሁ ጋር በተያያዘ አቶ መኮንን እንዳሉት፤ የዘንድሮ የመኸር እርሻ ተግባር ከሽፋን አንጻር እንደ ወረዳ አበረታች ቢሆንም፤ አሁንም በትኩረት ባለድርሻ አካላት እያገዙ የዩሪያ ቀሪ ስራዎች ብሎም የአረም ቁጥጥርና መሰል ተግባራት ተጠናክረው መሄድ እንዳለባቸው ጠቅሰዋል።

በዘንድሮ ዓመት ከበልግ ጀምሮ ተግዳሮቶች ነበሩም ብለዋል፡፡ በተለይ የበረዶ ክስተት ጉዳት ማድረሱን ጠቅሰው የመገልበጥ ስራዎች በመስራት በመኸር የማካካስ ስራ የተሰራ መሆኑን ጠቅሰው በተወሰነ መልኩ ተምች ተከስቶ የነበረ ሲሆን መከላከል ተችሏልም ብለዋል፡፡

እነዚህ ተግዳሮቶች እንዳሉ ሆነው በተለይ ከግብዓት አንጻር የዋጋ ውድነትና የአቅርቦት ችግሮች በመኸር ስራው ላይ እንቅፋቶች እንደነበሩ ጠቅሰው ይህንን ተከትሎም አርሶ አደሩ በወቅቱ ማሳውን በዘር እንዳይሸፍን ተግዳሮት ገጥሞ እንደነበርም አመላክተዋል፡፡

በመጨረሻም አቶ መኮንን ባስተላለፉት መልዕክት እንዳሉት በቀጣይ ቀሪ የመኸር ተግባራት ላይ በተለይም ሰብልን ከመንከባከብ እና የአረም ቁጥጥር ብሎም የዩሪያ ቶፕ-ድሬስ ስራዎች ላይ ባለሙያውና ባለድርሻ አካላት በተገቢው ሊደግፉና ክትትል ሊያደርጉ እንደሚገባም ማሳሰባቸው ከደቡብ ሶዶ ወረዳ መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

መረጃዎቻችበተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub:- https://youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36CxQ
Twitter:- https://4pvf.short.gy/bTJNNn

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *