በዘንድሮ የመኸር እርሻ ከ135 ሺህ በላይ ሄክታር መሬት በዋና ዋና ሰብሎችቨ መሸፈኑ የዞኑ ግብርና መምሪያ አስታወቀ።

ነሐሴ 13/2014
በዘንድሮ የመኸር እርሻ ከ135 ሺህ በላይ ሄክታር መሬት በዋና ዋና ሰብሎችቨ መሸፈኑ የዞኑ ግብርና መምሪያ አስታወቀ።

ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ አርሶአደሮች ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑንም ተገለፀ።

በዘር ከተሸፈነው የስንዴ፣ የገብስና የጤፍ ማሳ 60 በመቶ የሚሆነውን በክላስተር እየለማ ነዉ።

የዞኑ ግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ አበራ ወንድሙ በዘንድሮ የመኸር እርሻ ወቅት በዘር ለመሸፈን ከታቀደው 146 ሺህ ሄክታር መሬት ውስጥ ከ135 ሺህ በላይ ሄክታር ማሳ በስንዴ፣ በገብስ፣ በባቄላ፣ በአተርና በጤፍ ዘር ተሸፍኗል ብለዋል።

በዞኑ በዘር ለመሸፈን ከታቀደው ማሳ በላይ ለመስራት ከፍተኛ እንቅስቃሴ እየተደረገ ነው ያሉት ኃላፊው በቀጣይ የጤፍ ማሳዎችን ጨምሮ ቀሪ ማሳዎች በጓያና በሽምብራ ዘር ይሸፈናሉ ብለዋል።

እንደ ኃላፊው ገለጻ ምርትና ምትታማነትን በማሳደግ አርሶ አደሮቹ ተጠቃሚ ለማድረግ በዘር ከተሸፈነው የስንዴ፣ የገብስና የጤፍ ማሳ 60 በመቶ የሚሆነውን በክላስተር ማልማት ተችሏል።

በዘንድሮ የመኸር ወቅት አርሶአደሮች የገጠማቸውን የዩሪያ እጥረት ለመቅረፍ ከባለድርሻ አካላት ጋር እየተሰራ እንደሚገኝም ገልጸዋል።

በመሆኑም በዘንድሮ የመኸር ወቅት 146 ሺህ ሄክታር መሬት በማረስ ከ6 ነጥብ 8 ሚሊዮን በላይ ኩንታል ምርት ለማግኘት እቅድ መያዙን አመላክተዋል ።

በዞኑ በተያዘው የመኸር ወቅት ለማግኘት ከታቀደው በላይ ምርት ማግኘት እንዲቻል የግብርና ባለሙያዎች ለአርሶ አደሩ አስፈላጊውን ድጋፍ እያደረጉላቸው ይገኛሉ ብለዋል።

አርሶ አደሩ ሰብሉን ከአረምና ከተለያዩ ተባዮች እንዲጠብቅ የፀረ አረምና ተባይ ኬሚካሎችን እንዲቀርብለት እየተሰራ መሆኑን የገለፁት ኃላፊው ጤፍ አምራች አርሶ አደሮች ደግሞ ጎርፍ ከማሳቸው ማስወገድ ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።

በቀጣይ ሴቶች፣ ወጣቶችና ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች ያልታረሱ ቦታዎች በማረስ የምግብ ዋስትናቸው እንዲያረጋግጡ መልዕክት አስተላልፈዋል።

የእንደጋኝ ወረዳ ግብርና ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ክብሩ ዳጊቾ በበኩላቸው አርሶ አደሮች የገጠማቸውን የአፈር ማዳበሪያ እጥረት ለመቅረፍ የተለያዩ አማራጮች በመጠቀም እንዲያገኙ ተደርጓል ብለዋል።

አረምን ለመቆጣጠር የሚያስችል የዩሪያ እጥረት በመኖሩ ችግሩ እንዲቀረፍ ከዞኑ ግብርና መምሪያ ጋር እየሰሩ መሆናቸውን ገልጸዋል።

ወይዘሮ አምሳል ሽብሩ እና አቶ ራህመቶ መሀመድ በእንደጋኝ ወረዳ የበቻ እና ተበቼ ቀበሌ ሞዴል አርሶ አደሮች ሲሆኑ በልማት ቡድን በመደራጀት የስንዴ ምርጥ ዘር በማምረት ስራ ተሰማርተዋል።

እንደ አርሶ አደሮቹ ገለጻ የባለሙያዎች ምክረ ሀሳብ ተቀብለው የጠረጴዛማ እርከን በመስራት ዘርና የአፈር ማዳበሪያ በጎርፍ እንዳይታጠብ ረድቷቸዋል።

ባለሙያዎች የሚያደርጉላቸው የእለት ተዕለት ድጋፍ ውጤታማ አድርጎናል ያሉት አርሶ አደሮቹ ከሰብል ልማት በተጨማሪ በእንስሳት እርባታ ዘርፍ በመሰማራት የተሻለ ውጤት እንዲያገኙ አስችሏቸዋል።

በመሆኑም በዘንድሮ የመኸር ወቅት የተሻለ ምርት ለማግኘት ማሳቸው እንደሚንከባከቡ ገልጸዋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን መብግስት ኮሚኒኬሽን ነው።
በመረጃ ምንጭነት ገፃችን ምርጫዎ ስላደረጉ እናመሰግናለን!
እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub:- https://youtube.com/channel

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *